በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው አገራዊ ምርጫ አጠቃላይ የምርጫ እንቅስቃሴው ከማለዳው 11:40 አካባቢ ነበር አንዳንድ ጣቢያዎች የተከፈቱት ነገር ግን በአብዛኛዎቹ ጣቢያዎች መራጮች ተገኝተው በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ አስፈፃሚዎችና ታዛቢዎች ከ12 ሰአት ቀድመው አልተገኙም።
በከተማው 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚወዳደሩ ሲሆን በሁለት የምርጫ ክልሎች በሚገኙት 220 የምርጫ ጣቢያዎች ከ157,000 በላይ መራጮች ተመዝግበዋል።
መራጩ ህዝብ በደመናማው የጎንደር ማለዳ በበርካታ የምርጫ ጣቢያዎች በብዛት ወጥቷል ረጃጅም ሰልፎች ይታያሉ። በበርካታ የምርጫ ጣቢዎች ድምፅ እየሰጡ የሚገኙ መራጮች በአብዛኛው በጎልማሳ እድሜ ላይ ያሉ እና በእድሜ ገፋ ያሉ ይበዛሉ።