በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ አንድ የምርጫ ክልል ስር የሚገኘው የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ እያከናወኑ ይገኛሉ። በአምቦ ከተማ 31 የምርጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ ከነዚህም ውስጥ በሆራ አይቶ ቀበሌ እና አምቦ ቁጠር አንድ ያሂ ገዳ ቀበሌዎች ላይ በርካታ መራጮች ከሌሊቱ 11:30 ጀምሮ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በማምራት ምርጫ እያደረጉ ይገኛሉ።
በተለይ በያሂ ገዳ ቀበሌ 03 ቀበሌ የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰሃሉ ድሪብሳ ብልፅግና ፓርቲ ን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ድምፃችውን ሲሰጡም ሪፖርተር አስተውሏል። በምርጫ ጣቢያዎቹ ከብልፅግና ፓርቲ ፣ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን ፣የአምቦ ከተማ ወጣቶች ፌዴሬሽን እና ሴቶች ፌዴሬሽን በታዛቢነት ተሰይመዋል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ምርጫ ክልል አንድ ስር 94 የምርጫ ጣቢያዎች 69696 መራጮች ተመዝግበወዋል። በ31 የአምቦ ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ 30,491 መራጮች ተመዝገበዋል።
- Advertisement -
- Advertisement -