Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትበዘንድሮ ኦሊምፒክ ወደ ስታዲየም የሚገቡ ተመልካቾች ቁጥር ላይ ገደብ ተጣለ

በዘንድሮ ኦሊምፒክ ወደ ስታዲየም የሚገቡ ተመልካቾች ቁጥር ላይ ገደብ ተጣለ

ቀን:

የዘንድሮውን የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ለመመልከት ወደ ስታዲየም የሚገቡ ተመልካቾች ቁጥር ጋር በተያያዘ ውይይት ተደረገ፡፡ የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን በተመለከተ የጋራ መግለጫ የሰጡት፣ የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ)፣ ዓለም አቀፉ ፓራኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ቶኪዮ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ የቶኪዮ ሜትሮፖሊታን መንግሥትና የጃፓን መንግሥት በጋራ በመሆን ነው፡፡

የኦሊምፒክ ጨዋታዎችን ለመመልከት ወደ ስታዲየም የሚያመሩ ተመልካቾች ብዛት ወሰን ላይ ለመወያየት ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ፓራ ኦሊምፒክና  ሦስቱ የጃፓን ተቋማት የተስማሙበት ወሳኔዎች  አስተላልፈዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ የመጀመሪያው መንግሥት በሕዝባዊ ዝግጅቶች ላይ ከጣለው ገደብ አንፃር፣ ለኦሊምፒክ ጨዋታዎች የተመልካቾች ወሰን በሁሉም ሥፍራዎች  ቀድሞ ከነበረው ቁጥር 50 በመቶ እንዲሆን፣ ቢበዛ እስከ 10,000 ሰዎች ድረስ  ብቻ  በአንድ ስታዲየም በአንድ ጊዜ ማስተናገድ እንደሚቻል አስቀምጥዋል፡፡

- Advertisement -

ይኼ ውሳኔ ግን በጨዋታው ላይ ተመልካቾችን የሚቆጣጠሩና ለተወዳዳሪዎች ድጋፍ ለመስጠት የሠለጠኑ ተማሪዎች ከግምት የማይገቡ በመሆናቸው ተመልካች ባለመሆናቸው በተናጠል ይታያሉ ተብሏል፡፡

ወሳኔው የተላለፈው የኮሮና ወረርሽኝን ለመቆጣጠር እንዲያስችልና ማንኛውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወይም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዕርምጃዎች ገደቦችን ለመጣል ባስፈለገ ጊዜ፣ የተመልካቾች ቁጥር ከግምት ውስጥ ማስገባት ወሳኝነት እንዳለው ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህም በሻገር ተቋማቱ ወረርሽኙን የመከላከልና ደኅንነቱ የተጠበቀ የኦሊምፒክ ጨዋታ ለማከናወን የተለያዩ መመርያዎችን ማስቀመጣቸውን አሳውቀዋል፡፡

በተለይ ተመልካቹ በስታዲየም ውስጥ ሲታደም የአፍና አፍንጫ ጭምብል መልበስ፣ ድምፅን ከፍ አድርጎ መናገር ወይም መጮህ የተከለከለ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡

በተጨማሪም ተመልካቾች ሲወጡና ሲገቡ የኮሮና ወረርሽኝ ፕሮቶኮልን ከግምት ወስጥ በማስገባት መንቀሳቀስና በርካታ ተመልካች የሚሰበሰብባቸው ሥፍራዎች ላይ ክትትል ማድረግ፣ የተለያዩ ዝግጅቶች መጠን መቀነስ የሚሉት መሥፈርቶች በውስጡ አካቷል፡፡

ስታዲየሞቹ ለውጭ ዜጎች በራቸውን ዝግ ያደረጉ ሲሆን፣ በስታዲየሙ መታደም የቻሉ የአገሪቷ ተመልካቾች ደግሞ ወደ አትሌቱ ሄዶ ደስታን መግለጽ እንደማይቻል ይደነግጋል፡፡

የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከመከፈቱ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የፓራ ኦሊምፒክ ጨዋታዎችን የሚያስተዳድሩ ተመጣጣኝ ፖሊሲዎች እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ እንደሚዘጋጁ ይጠበቃል፡፡

ጃፓን አስተማማኝና ደኅንነቱ የተጠበቀ ጨዋታዎችን ለማካሄድ ከላይ የተጠቀሱትን መመርያዎችመከተልለማረጋገጥ፣ የአዘጋጆች ኮሚቴ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና ትብብር እንደሚሠራ ተብራርቷል፡፡

ጃፓን የተመልካቾችን ቁጥር ግማሽ በግማሽ የምትቀንስ ከሆነ 73.4 ቢሊዮን የጃፓን የን ወይም ከ28 ቢሊዮን ብር በላይ እንደምታጣ ይገመታል፡፡ ይኼም የገቢ ማሽቆልቆል የተሰላው የትኬት ሽያጭ ዝቅተኛ መሆኑና ተያያዥ የሆኑ ሽያጮችን ማከናወን ባለመቻሏ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በጃፓን የኮሮና ወረርሽኝ ተጠቂዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ አገሮች ላይ ከፍተኛ ፍራቻ መፈጠሩ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በጃፓን እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 780 ሺሕ በላይ መድረሱንና 14421 ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸው ተገልጿል፡፡

በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ለሚሳተፉ ስፖርተኞች ክትባት መስጠት እንዲሁም በውድድሩ ወቅት ክትባቶቹን ማዘመን የሚለው ከውሳኔ ጋር የተካተቱ አንኳር ጉዳዮች  ናቸው፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከአምና ወደ ዘንድሮ የተዘዋወረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ፣ ከሐምሌ 16 ቀን እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ይከናወናል፡፡ የፓራ ኦሊምፒክ ከነሐሴ 18 እስከ ነሐሴ 30 ድረስ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ሊካሄዱ 25 ቀናት ሲቀረው ፓራ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለመግባት 27 ቀናት ይቀራሉ፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...