Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአዲስ አበባ ከአሥር የምርጫ ክልሎች ውጭ እንደገና ቆጠራ እየተካሄደ ነው

በአዲስ አበባ ከአሥር የምርጫ ክልሎች ውጭ እንደገና ቆጠራ እየተካሄደ ነው

ቀን:

-ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በስድስት የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ እንዳልተደረገ ተገለፀ

-ቦርዱ በደቡብ ክልል በቁጫ ምርጫ ክልል የሚደረገው የድምፅ ቆጠራ እንዲቆም ወሰነ

በአዲስ አበባ አሥር የምርጫ ክልሎች የምርጫ ውጤታቸውን ይፋ ከማድረጋቸው ውጭ የሌሎቹ የምርጫ ክልሎችን ውጤት ለማረጋገጥ እንደገና እየተቆጠረ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2013 ዓም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ በስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት፣ እስካሁን በምርጫ ክልል ደረጃ 221 የምርጫ ክልሎች ውጤቶችን ጨርሰው ይፋ አድርገዋል።

በሌሎቹ የምርጫ ክልሎች የምርጫ ውጤቱን ይፋ ለማድረግ በተለያዩ ምክንያቶች እንዳልቻሉ ጠቁመው በየክልሎቹ ያሉትን ሂደቶች ገልጸዋል። በአማራ ክልል በምርጫ ክልል ደረጃ ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየበት መሆኑን ተናግረው፣ በጠቅላላው ካሉት 125 የምርጫ ክልሎች 40 የሚሆኑትን ውጤት ብቻ ይፋ ማድረጉን አውስተዋል።

ኦሮሚያ ክልል በ125 የምርጫ ክልሎች ላይ ውጤት በማሳወቅ የተሻለ እንቅስቃሴ እንዳሳየ የገለጹት ወ/ት ሶሊያና፣ በድሬዳዋ ስድስት ጣቢያዎች ላይ ለክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዳልተካሄደባቸው ቦርዱ ማረጋገጡንና ይኸም የሆነው በጣቢያዎቹ ለክልል ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምረጫ ወረቀት ስላልደረሳቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል ። መረጃው ለቦርዱ የደረሰው በዛሬው ዕለት እንደሆነ ያስታወቁት አማካሪዋ፣ የምርጫ ክልሉ ሃላፊ “የድምፅ መስጫ ሳይደርሰን ቀርቶ ስላላዳረስን ነው” የሚል ምላሽ የሰጡ ቢሆንም፣ለቦርዱ ግን ቀደም ብሎ ሪፖርት እንዳልተደረገለት ገልፀዋል ።

የጣቢያዎቹን ሁኔታ ቦርዱ እንደመረመረና በጣቢያዎቹ ላይ አንድ ፓርቲ እንደሚወዳደር በመረጋገጡ በክልል ምክር ቤት ደረጃ የሚኖረውን ውጤት ስለማይቀይረው ምንም አይነት ተጨማሪ ምርጫ አያስፈልግም የሚል ውሳኔ ላይ መድረሱንም አስታውቋል።ከስድስቱ ጣቢያዎች በአንዱ ላይ የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ አለመካሄዱን ያስታወቁት ወ/ት ሶሊያና፣ ይህ አለመሆኑ በአጠቃላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውጤት ታይቶ ወጤት የሚቀይር ከሆነ ቦርዱ ተጨማሪ ውሳኔእንደሚወስን ገልፀዋል ።

በደቡብ ክልል፣ የቁጫ ምርጫ ክልል ላይ የሚደረገውን የድምፅ ቆጠራ ቦርዱ እንዲቆም የወሰነ መሆኑን የተናገሩት ወ/ት ሶሊያና፣ ይህም የሆነው በርካታ ቅሬታዎችና በምርጫ አስፈፃሚዎች የስጋትና የፀጥታ ቅሬታ ስለተነሳ መሆኑን አሳውቀዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...