Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምርጫ ቦርድ በያዝነው ሳምንት ውስጥ የምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እንደሚያደርግ ታወቀ

ምርጫ ቦርድ በያዝነው ሳምንት ውስጥ የምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እንደሚያደርግ ታወቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ ውጤት በአራትና አምስት ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግ ታወቀ፡፡

ቦርዱ ውጤት አዳምረው ለማዕከል የሚያስረክቡ የምርጫ ጣቢያዎችን ውጤቶች እያጣራና እየተቀበለ እንደሚገኝ ዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ለተወሰኑ የመገናኛ ብዙሃን አባላት የውጤት ቅበላና  ርክክብ ሂደትን በማስጎብኘት ያሳየው ቦርዱ፣ እስካሁን ድረስ የ378 የምረጫ ክልሎች ውጤት ለቦርዱ ተጠቃልሎ መግባቱን  አስታውቋል፡፡

ይሁንና፣ የእነዚህ የምርጫ ክልሎች ውጤቶች ተጣርተው ሲጠናቀቁ የመጨረሻ ውጤት ተደርገው የሚቆጠሩ ሲሆን፣ ቦርዱ የምርጫ ክልሎች በአምስት ቀናት ቆጥረው ያመጡትን ውጤት አጣርቶ ጊዜያዊ ውጤት ደግሞ በቀናት ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳውቅ ተገልጿለ፡፡

የምርጫ ክልሎች የየምርጫ ክልላቸውን ውጤት ለቦርዱ ምርጫው ከተከናወነ ከአምስተኛው ቀን ጀምሮ እያስረከቡ ሲሆን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫውን ዘግይተው የጀመሩ የምርጫ ክልሎች ግን እስከ ሁለት ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡

እስከካሁን በተደረጉ የውጤት ርክክብ ሒደቶች ያጋጠሙ ችግሮች ዋነኛው የውጤት ማዳመር ስህተት እንደሆነ ከጉብኝቱ በኋላ ማብራሪያ የሰጡት የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ፣ ከእያንዳንዱ የምርጫ ክልል የምርጫ ክልል ኃላፊዎች ውጤት ይዘው ይመጣሉ ብለዋል፡፡ ይሁንና፣ እነርሱ ያመጡት ውጤት ስህተት ያለበት ሆኖ ከተገኘ በምርጫ ክልሉ የሚሠሩ ሌላ ሁለት ሰዎች ስላሉ እነርሱ ጋር በስልክ ተደውሎ የማጣራት ሥራው ይሠራል ብለዋል፡፡

የምርጫ ውጤት ከምርጫ ክልል ወደ ማዕከል ሲጓጓዝ በአጀብ የሚመጣ ሲሆን፣ በምርጫ ቦርድ የውጤት ማጣሪያ ጣቢያ በርካታ ፖሊሶች ውጤት አጅበው መጥተው እየጠበቁ ይታያሉ፡፡

እያንዳንዱ ክልል የየራሱ የውጤት ማጣሪያ ጠረጴዛ ያለው ሲሆን፣ አንድ ውጤት ለማጣራት ስህተት ካልተገኘበት ከ45 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት፣ ችግር ካለበት ግን እስከ ግማሽ ቀን ድረስ ሊፈጅ የሚችል ሒደት አለው፡፡ የምርጫ ክልላቸው ብዙ የሆኑት የደቡብ ክልል፣ የአማራ ክልልና የኦሮሚያ ክልሎች ሁለት ሁለት የውጤት መረከቢያ ጠረጴዛዎች አሏቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...