Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመንግሥት ከሕወሓት ይልቅ ለአገሪቱ ሥጋት የሆኑ ሌሎች ችግሮች አሉብኝ አለ

መንግሥት ከሕወሓት ይልቅ ለአገሪቱ ሥጋት የሆኑ ሌሎች ችግሮች አሉብኝ አለ

ቀን:

ላለፉት ስምንት ወራት በትግራይ ክልል ከሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ጋር ሲደረግ የነበረውን ጦርነት በመተው ከክልሉ መውጣቱ ሲዋጋው ከነበረው ሕወሓት ይልቅ የአገሪቱ ሥጋት የሆኑ ሌሎች ችግሮች አሉና በእነሱ ለማተኮር ነው ሲል መንግሥት አስታወቀ፡፡

ሰኔ 23 ቀን 2013 .. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለጋዘጠኞች መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን (አምባሳደር) እና የመከላከያ ሠራዊት፣ የሠራዊት ግንባታ አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ አሁን ኢትዮጵያ ሕወሓት ባለበት አቅም የብሔራዊ ደኅንነት ሥጋት ስላልሆነና ለሌሎች ሥጋቶች ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል በማለም ሠራዊቱ ከትግራይ እንዲወጣ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በተለይቐለ አስቀድሞ የነበራትን የስህበት ማዕከልነት አሁን ላይ አጥታለችናቐለ መቆየትም ሆነ መልቀቅ ከወታደራዊ ጠቀሜታው አንፃር ሌሎች አካባቢዎችን ከመያዝ የተለየ አይደለም ያሉት ሌተናል ጄኔራል ባጫ፣ አስፈላጊ ከሆነ በሦስት ሳምንታት ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ተመልሰንቐለ አንገባለን ብለዋል፡፡ ይሁንና፣ ጥፋቱና የሚወሰደው ዕርምጃ ከመጀመርያው የበለጠ ይሆናልም ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ጄኔራሉ በሰጡት ማብራሪያ የሚፈለጉት ጄኔራሎች 17 የሲቪል አመራሮች ደግ 12 አይበልጡም ያሉ ሲሆን፣ ለእነዚህ ደግሞ የተሰማራው ኃይል 50 ሺሕ በላይ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ስለዚህም ይኼ ወታደሩን ለማስወጣት የተላለፈው ፖለቲካዊ ውሳኔ ከወታደራዊ ትርፍና ኪሳራ አንፃር ዋጋው ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሥጋት እንዳይሆን ተደርጓል የተባው ሕወሓትም ከትግራይ እንደይወጣ ይደረጋል ያሉት ጄኔራሉ፣ የሠራዊቱ ትኩረት አሁን ወደ ሌላ ሥጋቶች እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

‹‹ሕወሓት ኢትዮጵያን የሚያሠጋ ጉዳት አያደርስም፤›› በማለትም ተናግረዋል፡፡ አምባሳደር ሬድዋን በበኩለቸው ጦርነቱ ለስምንት ወራት ሲካሄድ 100 ቢሊዮን ብር ገደማ ወጪ እንደተደረገ በመግለጽ፣ ይኼም አገራዊ የኢኮኖሚ አቅማችን ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

‹‹የወደመው ሀብት በጣም ብዙ ነው፡፡ የወጣው ወጪም የመከላከያን ወጪ ሳይጨምር ነው፡፡ ይኼም የትግራይን ዓመታዊ በጀት ለአሥራ ምናምን ዓመታት መሸፈን የሚችል ነው›› በማለት፣ የትግራይ ክልል ዓመታዊ በጀት ስምንት ቢለዮን ብር መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለውጭ ጥቃት የተጋለጠችበት ሁኔታ መፈጠሩን የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን፣ በምዕራብ በኩል ድንበር ተወርሯል፣ የኢትዮጵያን ውስጣዊ ችግር በማየትም ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ጦርነት እየተደገሰላት እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡  

ከዚህ በመተጨማሪም፣ ከዚህ በላይ ከተቆየ የሚጎዳው ሲቪሊያንና ሕፃናት ናቸውና ይኼ እንዳይሆን ሠራዊቱ ከትግራይ እንዲወጣ መወሰኑን ጠቁመዋል፡፡

‹‹የሠራዊቱ መኖር ለሰብዓዊ ዕርዳታዎች እንቅፋት ፈጥሯል ሲሉ የነበሩ አካላትም፣ አሁን ሠራዊቱ ወጥቷልና ድጋፋቸውን ያድርሱ፡፡ መንግሥትም እነዚህ አካላት ዕውን ድጋፍ ማድረግ ነው ፍላጎታቸው አልያስ ሌላ የሚለውንም የሚያይበት አጋጣሚ ይሆናል›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...