Sunday, April 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናብልጽግና ተጨማሪ ስምንት የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸነፈ

ብልጽግና ተጨማሪ ስምንት የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸነፈ

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል ስምንት የምርጫ ክልሎች በብቸኝነት የተወዳደረው ብልጽግና ፓርቲ ስምንቱንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች አሸነፈ፡፡የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሔደውን የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ውጤቶች በማረጋገጥ መግለጹን በመቀጠል ሐሙስ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በኦሮሚያ ክልል በተገለጹ ስምንት የምርጫ ክልሎች ብልጽግና አሸንፏል፡፡

በእነዚህ ስምንት የምርጫ ክልሎች ብልጽግና ብቸኛው ተወዳዳሪ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ሳቢያ የኦሮሚያ ክልል ውጤቶችን የማጣራት ሒደት ቀላል አድርጎታል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በአማራ ክልል በአንድ የምርጫ ክልል ከተወዳደሩ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ ብልጽግና እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትኅ (ኢዜማ) ዕጩዎች መካከል የአብን ዕጩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መቀመጫ አሸንፈዋል፡፡ይሁንና በምርጫ ክልል ደረጃ የማዳመር ሥራዎች በመዘግየታቸውና በትራንስፖርት ምክንያት የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች በተለይም ከአፋር፣ ከጋንቤላና ከደቡብ ክልሎች ውጤት መድረስ ስላልቻለ ምርጫው ከተደረገ አሥር ቀናት ቢሆነውም የሁሉንም የምርጫ ክልሎች ጊዜያዊ ውጤት መግለጽ አልተቻለም ተብሏል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ፣ በአፋር ክልል ሰባት የምርጫ ክልሎች፣ በአዲስ አበባ ስምንት የምርጫ ክልሎች፣ በኦሮሚያ አራት የምርጫ ክልሎች፣ በደቡብ ሁለት የምርጫ ክልሎች እዲሁም በጋምቤላ አንድ የምርጫ ክልል ውጤታቸው አልደረሰም ብለዋል፡፡ነገር ግን፣ ለቦርዱ የደረሱና በማጣራት ሒደት ላይ የሚገኙ 73 የምርጫ ክልሎች ውጤት  ይፋ ይደረጋልም ብለዋል፡፡ከዚህ ውጪ ከቦርዱ ዕውቅና ውጪ ተከፍተው ከነበሩ 79 የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለት፣ እንዲሁም በድሬዳዋ የሚገኙ ስድስት የምርጫ ክልሎች ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲመርጡ የተደረገ ሲሆን፣ ይኼም ተጨማሪ የማንነትና የዕድሜ ማጣራት ሥራ ከተደረገ በኋላ መሆኑን ወ/ሪት ብርቱካን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በቁጫ የምርጫ ክልል እንዲከፈቱ ተብለው የነበሩ ሦስት የምርጫ ጣቢያዎች፣ እንዲከፈቱ ቁሳቁስ ተልኮላቸው የነበረ ቢሆንም፣ ባለመከፈታቸው ሳቢያ የምርጫ ክልል ኃላፊው ከሥራ እንዲባረሩ የተደረገ ሲሆን፣ በምርጫው ቀን መራጮች እየተመዘገቡ ምርጫውንም ጎን ለጎን እንዲደረግ ተደርጎ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

ለዚህም በእያንዳንዱ ጣቢያ ሦስት ተጨማሪ አስፈጻሚዎች ተጨምረው ምዝገባውን ሲያከናውኑ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡በአዲስ አበባና በድሬዳዋ እንዲሁም በደቡብ ክልል ሳይፈቀድላቸው የምርጫ ክልል የከፈቱ አስፈጻሚዎች ውላቸው ተቋርጧል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኦቲዝምን ለመቋቋም በጥምረት የቆሙት ማዕከላት

ከኦቲዝም ጋር የሚወለዱ ልጆች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ...

አወዛጋቢው የወልቃይት ጉዳይ

የአማራና ትግራይ ክልሎችን እያወዛገበ ያለው የወልቃይት ጉዳይ ዳግም እየተነሳ...

ተጠባቂው የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የውድድር መለኪያ የሆነው የሞባይል ገንዘብ ዝውውር በኢትዮጵያ

የሞባይል ገንዘብ ዝውውር የሞባይል ስልክን በመጠቀም ሊገኙ የሚችሉ የፋይናንስ...

የአማራና ደቡብ ክልሎች ለሠራተኛ ደመወዝ መክፈል መቸገራቸውን የፓርላማ አባላት ተናገሩ

በአማራና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት...