Monday, March 20, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየፀጥታው ምክር ቤት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ  ስብሰባ ሊያካሂድ መሆኑ ተጠቆመ

የፀጥታው ምክር ቤት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ  ስብሰባ ሊያካሂድ መሆኑ ተጠቆመ

ቀን:

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት ከታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ስብሰባ ሊያደርግ እንደሚችል ተነገረ፡፡ ምክር ቤቱ ተሰብስቦ ቢወያይም ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ የገጠማቸውን አለመግባባት በውይይት ወይም ወደ ድርድር እንዲመለሱ ከማበረታት ውጪ፣ ሊያደርግ የሚችለው ነገር እንደሌለ ተጠቁሟል፡፡

የምክር ቤቱ የወቅቱ ሰብሳቢ በተመድ የፈረንሣይ አምባሳደር ነኮላስ ዴ ሪቪዬር ለውጭ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፣ ምክር ቤቱ ሦስቱን አገሮች ወደ ስምምነት ሊያደርስ ወደሚችል ድርድር እንዲመለሱ ከማድረግ ውጪ የጎላ ሚና አይኖረውም፡፡

ምክር ቤቱ ግድቡን በተመለከተ ወይይት ሊያደርግ እንደሚችል ያስታወቁት ሰብሳቢው፣ ሦስቱን አገሮች በመጥራትጋታቸውን እንዲገልጹና ከስምምነት ሊያደርሳቸው ወደሚችለው ድርድር እንዲመለሱ ከማበረታታት ውጪ ሊያደርግ የሚችለው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ምክር ቤቱ ከዚያ የበለጠ ነገር ማድረግ ይችላል ብዬ አላስብም፤›› ሲሉም አስተያየታቸውን አጠናክረዋል፡፡

ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን በተደጋጋሚ ወደጥታው ምክር ቤት በመውሰድ፣ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ምክር ቤቱ በግድቡ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ሱዳን፣ ግብፅና የዓረብ ሊግ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ኢትዮጵያ ግን፣ ‹‹የአፍሪካውን ችግር በአፍሪካውያን መፈታት አለበት›› በሚለው መርህ አቋም ሲኖራት፣ በቅርቡም ለፀጥታው ምክር ቤት በላከችው ደብዳቤ ይህንኑ ማሳወቋ ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ዜጎች የተፈተኑበት የኑሮ ውድነት

በኢትዮጵያ በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ዜጎችን አቅም...

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸውና በተቀናጀ መልኩ...

ወደ ኋላ የቀረው የሠራተኞች ደኅንነት አጠባበቅ

በአበበ ፍቅር ለሠራተኞች የሚሰጠው የደኅንነት ትኩረት አናሳ በመሆኑ በርካታ ዜጎች...