Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኦዲት ክፍተት የሚታይባቸው ተቋማት ኃላፊዎች ጠንካራ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተገለጸ

የኦዲት ክፍተት የሚታይባቸው ተቋማት ኃላፊዎች ጠንካራ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተገለጸ

ቀን:

በመንግሥት ተቋማት የሀብት ብክነትና የኦዲት ክፍተት የሚስተዋልባቸውን የሥራ ኃላፊዎች ጠንካራ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎች ሰበቦችን በመፍጠር፣ ኦዲት ለመደረግ ፈቃደኛ ያለመሆን አዝማሚያ እያሳዩ መሆኑን ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ሐሙስ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በተገኙበት የ2014 ዓ.ም. ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የፓርላማ አባላቱ በመንግሥት ተቋማት ላይ የሚታየው የሀብት አጠቃቀም የደሃ አገር ሀብት ስለማይመስል መንግሥት ቁጥጥር ያድርግ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት ከኦዲት ግኝት ጋር በተገናኘ እየታዩ ያሉ ክፍተቶችን አስመልክተው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ በፊት በተገኙ የኦዲት ግኝቶች አንዳንዶቹ ጥሬ ገንዘብ እንዲመልሱ፣ በሌላ በኩል በጀት ያዝ በማድረግ፣ የበርካታ የመንግሥት ኃላፊዎችን ደመወዝ በመቅጣት፣ እንዲሁም የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጣቸው እንደሆነ በመጥቀስ፣ ከዚህ በኋላ ለሚታዩ አዲስ የኦዲት ችግሮች ኃላፊዎችን በመቅጣት፣ መልክ የማስያዝ ሥራ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

ነገር ግን በኦዲት ክፍተት የተነሳ የተቋማት በጀት እንደማይከለከል በመግለጽ፣ በጀት በመከልከል በመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማቆም ኅብረተሰቡን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌለ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ2014 በጀት ዓመት በቀረበው የ561 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡ በጀቱ የሰኔ ወር ከመጠናቀቁ በፊት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይሁን እንጂ የመጪው ዓመት በጀት በአገሪቱ እየታዩ ያሉ ምክንያታዊ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎችን ለማስተካከል የሚኖረው ሚና፣ እንዲሁም ገበያውን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ዝቅተኛ መሆኑን አቶ ደጊሶ ጊና የተባሉ የምክር ቤት አባል ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ከዓመት በፊት በተገበረው አገራዊ ኢኮኖሚ ሪፎርም ምንም እንኳን የተጀመሩ መልካም ሥራዎች ቢኖሩም፣ በኑሮ ውድነቱ ላይ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን ወ/ሮ ብርቱካን ሰብስቤ የተባሉ የምክር ቤት አባል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የቀጣዩ ዓመት በጀት የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ ምን ያህል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ከፓርላማ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፣ መንግሥት በንግድ ሥርዓቱ ውስጥ በርካታ ተዋናዮችን በማስገባት፣ የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን፣ አገራዊ ምርቱን በማሳደግ፣ የብድር ሥርዓቱን በማጠናከርና ሌሎች ምቹ የንግድ ሁኔታዎችን በመፍጠር የኑሮ ውድነቱን ለማርገብ ይሠራል ብለዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አላስፈላጊ የግብይት ሥርዓት እንዳይኖር መንግሥት የጀመረውን ሪፎርም አጠናክሮ በመቀጠል፣ የግብርና ምርታማነትን ለመጨመር መንግሥት የሁለት ቢሊዮን ብር የማዳበሪያ ግዥ ድጎማ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...