Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየምርጫ ዥንጉርጉር ገጽታ

የምርጫ ዥንጉርጉር ገጽታ

ቀን:

በምርጫና ዴሞክራሲ ስም ብዙ ማጭበርበርና ግፍ የተፈጸመውን ያህል ግርታን የሚፈጥሩና የሚገርሙ ትክክለኛ ምርጫዎችም በየጊዜው ተካሂደዋል፡፡ ዓይን ያወጡ የአምባገነኖች ምርጫዎችንና በተለያዩ ሁናቴዎች የሚከሰቱ አስደናቂ ምርጫዎችን ስናይ ኖረናል፡፡ ለነገሩ ምርጫ በትክክለኛ መንገድ ቢካሄድም ውጤቱን በትክክል መተንበይ የማይቻልበት ሁኔታ ብዙ ነው፡፡ በአጭሩ ምርጫ መልከ ብዙና ዥንጉርጉር ነው እንደ ሰው ልጅ ባህሪ ሁሉ፡፡ ለማንኛውም የሚከተሉን ዥንጉጉር ጉዳዮች እንመልከት፡፡

የላይቤርያው ጉድ

የዓለማችን እጅግ በጣም የተጭበረበረ ምርጫ በመባል በ‹‹ጊነስ ቡክ ኦቭ ወርልድ ሬኮርድስ›› የተመዘገበው ምርጫ እ.ኤ.አ. በ1927 ላይቤርያ የተካሄደው ምርጫ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ የላይቤርያ ሕዝብ ብዙ አልነበረም፡፡ በመሆኑም በድጋሚ ለፕሬዚዳንትነት የተወዳደረው ቻርልስ ዲ ቢ ኪንግ በ234,000 ድምፅ መመረጡ ሲገለጽ ግርታን ፈጠረ፡፡ ምክንያቱም በአገሪቱ ለምርጫ የተመዘገበው መራጭ ብዛት 15,000 ብቻ ነበር!

በድጋሚ የተመረጠው ፕሬዚዳንት አስገራሚውን ድል በማጣጣም ላይ ሳለ ግን የተቀናቃኙ ፓርቲ መሪ የባርያ ንግድ በአገሪቱ እንዲካሄድ በመፍቀድና ሌሎችንም መሠረተ ልማቶች በባሮች በማሠራት ወነጀለው፡፡ በጉዳዩ ጣልቃ የገባው ሊግ ኦቭ ኔሽንም (የአሁኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት) ጥናት በማካሄድ ፕሬዚዳንት ኪንግንና ፓርቲውን ተጠያቂ በማድረግ ወነጀሉ፡፡ በዚህም የተነሳ አጭበርባሪው ፕሬዚዳንት በዓመቱ ሥልጣኑን በፈቃዱ ለቀቀ፡፡

ጀግና ሲሸነፍ

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርቺል አገሩ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊ ሆና እንድትወጣ ፋሺስት ጀርመንና መሪዋ ሒትለርን በማንበርከክ ከዓለም ታላላቅ መሪዎች ተርታ የሚጠቀስ ጀግና ነው፡፡ በመሆኑም በ1945 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ እንደሚያሸንፍ ሁሉም ሰው ደምድሞ ነበር፡፡ ቸርቺል በጣም የተወደደና የተከበረ ከመሆኑ የተነሳ 83 በመቶ የሕዝብ ድጋፍ ነበረው፡፡ በርግጥም ቸርቺል አሁንም ድረስ በዓለም ታሪክ ከሚጠቀሱት ዝነኛ ሰዎች አንዱ ነው፡፡ በዚያ ላይ ብሩህ ፖለቲካዊ አዕምሮ ያለውና አንደበተ ስል ነበር፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን በዚያኑ ዓመት በተደረገው ምርጫ ተሸነፈ፡፡ ማመን የማይቻል ነገር ነበር፡፡

አገሪቱን በዚያ አሰቃቂ ጦርነት አሸናፊ ሆና እንድትወጣ ያደረገውን ጀግና በ1945ቱ ምርጫ ክሊመንት አትሊ በሰፊ ልዩነት አሸነፈው፡፡ የቸርቺል ፓርቲ ደጋፊዎች ሕዝቡ የቸርቺልን ጀግንነት እያደነቀ አትሊን በመምረጡ ተገርመው ነበር፡፡

አንዳንዶች እንደሚሉት የቸርቺል አወዳደቅ የሚያስተምረን ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ቀደም ሲል በተመዘገቡ ስኬቶች፣ የግለሰብ ክብርና ዝና ላይ የተመሠረቱ አለመሆናቸውን ነው፡፡ ይልቁንም በመጪዎቹ አራትና አምስት ዓመታት ሊፈጽሟቸው በሚያቀርቧቸው አሳማኝና በተግባር ሊተረጎሙ በሚችሉ መርሐ ግብሮች እንጂ፡፡ በመሆኑም አሸናፊ ፓርቲዎች ወይም ዕጩዎች ለመራጮች ጭንቀቶችና ሥጋቶች ምላሽ የሚሰጥ ራዕይ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

****

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...