Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየደቡብ አፍሪካው አስፒን ለአፍሪካ አገሮች የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት ጀመረ

የደቡብ አፍሪካው አስፒን ለአፍሪካ አገሮች የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት ጀመረ

ቀን:

የ600 ሚሊዮን ዩሮ የረዥም ጊዜ ብድር አግኝቷል

የደቡብ አፍሪካው የመድኃኒት አምራች ኩባንያ አስፒን ለአፍሪካ አገሮች ፍጆታ የሚውል የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት ጀመረ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ማምረት የጀመረው አስፒን፣ ምርቱን እንዲያፋጥን ከአሜሪካና አጋሮቿ የ600 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 10 ቢሊዮን ራንድ የረዥም ጊዜ ብድር አግኝቷል፡፡

አሜሪካ በአፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ላይ የምታደርገውን ድጋፍ አስመልክቶ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በተደረገ የበይነመረብ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ገንዘብ ትብብር ዋና ኦፊሰር ዴቪድ ማርሼት እንዳሉት፣ ተቋማቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በአፍሪካ የክትባት ምርትና ሥርጭት ላይ የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡

ኮቪድ-19 በአፍሪካውያን ሕይወትና አኗኗር ላይ ሥጋት እየጣለ መሆኑን፣ እስካሁንም 4.7 ሚሊዮን አፍሪካውያን ቫይረሱ እንደተገኘባቸው አስታውሰዋል፡፡ ቁጥሩ ከዚህ ሊልቅ እንደሚችል የገለጹት ሚስተር ማርሼት፣ በአፍሪካ በቂ የማምረቻ የአቅርቦት ሰንሰለትና ክትባት ለማምረትም ይሁን ለማግኘት በቂ ሀብት አለመኖር ችግር መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በመሆኑም ተቋማቸው ከዓለም ባንክ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ትብብር፣ ከፈረንሣይ እንዲሁም ከጀርመን ጋር በመተባበር የረዥም ጊዜ ብድር በደቡብ አፍሪካ ለሚገኘው አስፒን መድኃኒት አምራች እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡

አስፒን መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሚያገኘው ብድር ተቋሙን ከማጠናከር ባለፈ ለአኅጉሪቱ ለዘንድሮና ለቀጣይ ዓመት ክትባት ለማምረት ይውላል ተብሏል፡፡

አስፒን የክትባት ምርቱን መጨመር የአፍሪካ ኅብረት ለኮቪድ-19 400 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ለማግኘት ያስቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

አፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባትን ለሕዝቦቿ በመከተብ በዝቅተኛ ደረጃ እንደምትገኝ፣ በአኅጉሪቱ ከሚገኙ 1.1 ቢሊዮን ያህል አፍሪካውያን ክትባቱን ያገኙት አንድ በመቶ ያህሉ ብቻ እንደሆኑም አስታውሰዋል፡፡

ሚስተር ማርቬት እንዳሉት፣ አስፒን በረዥም ጊዜ ብድር የሚከፍለው 600 ሚሊዮን ዩሮ የሚያገኝ ሲሆን፣ የረዥም ጊዜ ብድር መሆኑም በረዥም ጊዜ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለማለፍ ያስችላል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት በዓለም የሚያስፈልገው የክትባት መጠን አምስት ቢሊዮን ዶዝ ያህል ነበር፡፡ ይህም ኢንፍሉዌንዛን፣ ቢጫ ወባን፣ ኩፍኝንና ፖሊዮን ጨምሮ ነው፡፡ ነገር ግን ኮቪድን ብቻ ለመከላከል 11 ቢሊዮን ዶዝ ያስፈልጋል፡፡ 11 ቢሊዮን ዶዝ ያስፈልጋል ቢባልም አንድ ሰው ክትባቱን ከወሰደ በኋላ በድጋሚ የሚሰጠው ማጠናከሪያ (ቡስተር) ምን ያህል ጊዜ መወሰድ እንዳለበት አለመታወቁ ለአስፒን የረዥም ጊዜ ብድር ለመስጠት ምክንያት ከሆኑት ይጠቀሳል፡፡

ዋና ቢሮውን በደቡብ አፍሪካ ደርባን ያደረገው አስፒን፣ ከወር በፊት በአፍሪካ የክትባት ተደራሽነትን ለማጠናከር የምርት ማስፋፊያ ዕቅድ እንዳለው አሳውቆ ነበር፡፡

አፍሪካ 99 በመቶ የሚሆኑ ክትባቶችን ከውጭ ማስገባቷን የሚገልጸው አስፒን፣ ኮሮና ክትባትን በተመለከተ ብቻ ከሰሃራ በታች የሚገኙ አገሮች ከሁለት በመቶ ያነሰ ሕዝባቸውን ብቻ የከተቡት ክትባቱ ከውጭ የሚመጣ በመሆኑ እንደሆነ አስታውቋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...