Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትውዝግብ ባልተለየው የውኃ ስፖርት ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ የሚወክለው ማነው?

ውዝግብ ባልተለየው የውኃ ስፖርት ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ የሚወክለው ማነው?

ቀን:

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በብስክሌትና በዋና ትወከላለች፡፡ ኦሊምፒኩ ለአንድ ዓመት መራዘሙን ተከትሎ አትሌቶች ዝግጅታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ለታዳጊ አገሮች ባመቻቸው ዕድል (ዩኒቨርሳሊቲ) በውኃ ስፖርቶች አንድ ሴትና አንድ ወንድ እንደሚሳተፉ ያስቀምጣል፡፡

ምንም እንኳን ዕድሉ ኢትዮጵያ ከምትታወቅበት አትሌቲክስ ባሻገር በሌሎች ስፖርቶች ያላትን ተሳትፎ የሚያነቃቃ ዕድል ሲገኝ፣ ዕድሉን ከመጠቀም ባሻገር በስፖርት ውስጥ ባሉ አመራሮች እሰጣ ገባ ሲታጀብ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡

በተለይ ውድድሮች በተቃረቡ ቁጥር ሽኩቻውና እንካ ሰላንቲያው ማዳመጥ አዲስ አይደለም፡፡ ሐሙስ ሰኔ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. የኦሊምፒክ ዝግጅትን በተመለከት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያ የምትወከልበት አራቱም ስፖርቶች ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውንና በዋና ስፖርትም አገራቸውን የሚወክሉ አንድ ሴትና አንድ ወንድ አክርዴሽን እንደመጣላቸው አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ምንም እንኳን ኦሊምፒክ ኮሚቴው ሁለቱ ዋናተኞች አክርዴሽን አግኝተዋል ቢልም፣ የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን በበኩሉ፣ የመምረጥ ሥልጣኑ የእሱ እንደሆነ ሁለት ስፖርተኞች መርጦ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማዘጋጀቱን ይገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በሆኑት አቶ ቀልቤሳ ኤባ አስተያየት ከሆነ፣ እ.ኤ.አ በ2019 በደቡብ ኮርያ በተደረገው የዓለም ዋና ሻምፒዮና ላይ ከተሳተፉት ዋናተኞች ውስጥ ለአንድ ወንድና አንድ ሴት እንዲሳተፉ ዕድል መስጠቱን አሳውቆ፣ ለኦሊምፒክ ኮሚቴ ቢያሳውቅም ተቀባይነት እንዳላገኘ ለሪፖርተር አስረድቷል፡፡

ከዚህ ቀደም መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም.  በቢሾፍቱ በተደረገው ማጣሪያ የተለዩት  በወንድ አብዱልመሊክ ቶፊክ እንዲሁም በሴት ሊና ዓለማየሁ ባስመዘገቡት ሰዓት ተመርጠው በኦሊምፒክ ኮሚቴ ሙሉ ወጪ በግዮን ሆቴል መደበኛ ዝግጅት እያደረጉ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም ሐሙስ ሰኔ 24 ቀን ዓለም አቀፉ ዋና ፌዴሬሽን በወንድ አብዱል መሊክ ቶፊክ በ50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ 29.39 በሆነ ውጤት፣ እንዲሁም በሴቶች ራሔል ፍሥሐ 50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ 32.36 በሆነ ውጤት ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ዋናተኞች መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

በኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽንና በኦሊምፒክ ኮሚቴ መካክል በጋራ ተመካክሮ ከመሥራት ይልቅ፣ ሁለቱን ተቋማት የሥራ ድርሻቸውን አለማውቃቸው ኢትዮጵያ እስከማገድ ሊያደርስ እንደሚችል በርካቶች አስተያየት ይሰጣሉ፡፡

እንደ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አስተያየት ከሆነ፣ ፌዴሬሽኑ አሠልጣኝም ሆነ ስፖርተኛ የመምረጥ ኃላፊነቱ የእኔ ሆኖ፣ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ከፌዴሬሽኑ ዕውቅና ውጪ መምረጡ አግባብ እንዳልሆነ ይጠቅሳል፡፡

ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ተሾመ ሶርሳ በተደጋጋሚ የፌዴሬሽኑን መተዳደሪያ ደንብና ሥነ ምግባር መመርያ መጣሳቸውን ተከትሎ የሥራ አስፈጻሚው ባደረገው ስብሰባ ከኃላፊነታቸው ታግደው  እንዲቆዩና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በአንጻሩ በጠቅላላ ጉባዔው ላይ ከኃላፊነቱ እንዲነሳ ተወስኖ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፕሬዚዳንት አቶ ተሾመ፣ ከፌዴሬሽኑ ዕውቅናና ውሳኔ ውጪ ቡድን መሪ ሆነው መመረጡ ተገልጿል፡፡

በየዓመቱ ውዝግብ የማያጣው የኢትዮጵያ ስፖርት፣ በተለይ ውድድር በተቃረበ ወቅት ንትርክና ክስ አያጣውም፡፡ በ2016 ሪዮ ኦሊምፒክ በዋና የተፈጠረው ውዝግብ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር መተቸቷ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽንና ተወዳዳሪው አባትና ልጅ መሆናቸውና ምርጫው ላይ አድሎ ተፈጥሯል የሚለው ከፍተኛ ክርክር ማስነሳቱ ይታውሳል፡፡ ዘንድሮም ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ሁለቱም ተቋማት ተደማምጠው መሥራት ይገባቸዋል የሚለው የብዙኃኑ አስተያየት ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...