Monday, December 4, 2023

የትግራይ ቀውስና የአሜሪካ መንግሥት ምልከታ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

ያለፉትን ስምንት ወራት የፈጀው የትግራይ ክልል ቀውስ በተጠናቀቀው ሳምንት ወደ ሌላ ምዕራፍ የተሸጋገረ ቢሆንም፣ በቀጣይ ምን እንደሚፈጠር ማስተማመኛ ነገር የለም።

በተጠናቀቀው ሳምንት መጀመሪያ ከመንግሥት የተሰማው ድንገተኛ ዜና፣ በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁን የሚያመለክት ነበር። 

ይህንንም ተከትሎ በትግራይ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር ላለፉት ስምንት ወራት በውጊያ ውስጥ የነበረው የሕወሓት ኃይልየመከላከያ ሠራዊት ከመቀሌና ከሌሎች የትግራይ አካባቢዎች ለቆመውጣቱ የመቀሌ ከተማን ተቆጣጥሯል። 

በቀጣይቹ ቀናትም ዓድዋ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ሽሬና ሌሎች ከተሞችን እንደተቆጣጠረ ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። 

የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል የተናጠል ተኩ ለማወጅና ከክልሉ ለመውጣት የወሰነበትን ምክንያቶች የዘረዘረ ሲሆን፣ ምክንያቶቹም የተለያዩ ነገር ግን ቁርኝት የሚታይባቸው ናቸው። 

የፌዴራል መንግሥት የተናጠል ተኩስ ለማወጅና ተቆጣጥሯቸው ከነበሩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ለመውጣት የወሰነባቸውን ምክንያቶች ሲዘረዝርም፣ በቅድሚያ የሚያስቀምጠው የክልሉ አርሶ አደሮች ተረጋግተው የክረምቱን ወቅት ለእርሻ መጠቀም እንዲችሉ መሆን ይገልጻል። 

በኢትዮጵያ ላይ የተደቀኑ ሌሎች ሉዓላዊጋቶች በመኖራቸውና የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ለመመከት የሚያስችል ዝግጅት እንዲያደርግ ታስቦ መሆኑም ተገልጿል።

የተኩስ አቁም እንዲደረግ ምክረ ሐሳቡን ያቀረበው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (/) ለሚዲያዎች በሰጡት ገለጻ፣ ‹‹የተኩስ አቁም ስምምነቱ ገበሬው ተረጋግቶ እንዲያርስ፣ ለችግረኞች የሰብዓዊ ድጋፍና የዕርዳታ ቁሳቁስ ለማድረስ፣ የተፈናቃዮችን ቤት ጠግኖ ወደ ቦታቸው ለመመለስ ነው፤›› ብለዋል።

የጊዜያዊ አስተዳሩን ጥያቄ በአዎንታ መቀበሉን በመግለጽ የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁን ይፋ ያደረገው የፌዴራል መንግሥት ደግሞ፣ ከላይ ከተጠቀሱት መነሻ ምክንያቶች በተጨማሪ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችንም እንደተመለከተ ካወጣው መግለጫ መመልከት ይቻላል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ከተጠቀሱት ዝርዝር ምክንያቶች ባሻገር የክልሉን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት፣ በኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ወዳጆች ሲቀርቡ የነበሩ የመፍትሔሳቦችን የፌዴራል መንግሥት ሲያጤናቸው መቆየቱን ገልጿል። 

‹‹ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተከታታይ ያቀረበውን ጥያቄ መንግሥት ከተለያየ አቅጣጫ ተመልክቶታል፡፡ በአንድ በኩል አካባቢው ከሚመራ አካል የቀረበ በመሆኑ፣ በሌላ በኩል ጥያቄው ከመቅረቡ በፊት በተለያየ ጊዜ ከክልሉ ተወላጆች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት የተደረገበት መሆኑን ከግምት ውስጥ አስገብተናል፤›› በማለት የፌዴራል መንግሥት መግለጽ አይዘነጋም፡፡

በተጨማሪም፣ ‹‹በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያዝብና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከመቼውም በላይ ለአገራችን ሰላም የሰጡት ልዩ ትኩረት ከግምት ውስጥ ገብቷል፡፡ ይህንንም ሰላም የኢትዮጵያ አንዱ አካል የሆነውን የትግራይ ሕዝብ ተቋዳሽ ሊሆን ይገባል ተብሎ ስለሚታመን፣ የትግራይም ሕዝብ ሰላምና ለውጥ ፈላጊ መሆኑ በተለያዩ መንገዶች ሲገልጽ የቆየ መሆኑን ስለሚታወቅ፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ከውጭ ኃይሎች ከተሰነዘሩ ትንኮሳዎች ለመከላከልና ሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ ለመሙላት ትኩረት መስጠት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ በመሆኑ›› የተናጥል የተኩስ ማቆም ውስኔውን ለማሳለፍ ምክንያት እንደሆነ፣ የፌዴራል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ዘርዝሯል።

ነገር ግን መሠረታዊ ምክንያቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያነሳቸው በክልሉ ሕዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ መከራዎች መሆኑን ይገልጻል።

‹‹መላው ሕዝብም እንደሚረዳው፣ የተበተነው የሕወሓት ኃይል በመሸገባቸው አካባቢዎች ገበሬው ተረጋግቶ ወደ እርሻ ሥራ መግባት አልቻለም፡፡ ባለፈው ዓመት የአንበጣ መንጋ በስፋት ያጠቃው ክልል በመሆኑ የግብርና ሰብል ምርት በበቂ ሁኔታ አላገኘም፡፡ ከአንበጣ የተረፈውን መሰብሰብ እንዳይችል በመሰብሰብያዜውአካባቢው የግጭት ቀጣና ሆነ። በዚህ ሁኔታ ይኼንን ክረምት ያለ እርሻ ሥራ የሚያሳልፍ ከሆነ፣ ለገበሬው በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆንበታል፤›› ብሏል።

በማከለም፣ ‹‹የሕወሓት ኃይል በሚነዛው የሽብር መረጃ›› የተነሳ ሕዝቡ የጦርነት ጋሻ ሆኖ እየተማገደ እንደሆነና ከዚሁ ጋር ተያይዞም ‹‹ሲዋጋ ሚሊሻ፣ ሲጠቃ ሲቪል›› የሚሆን ኃይል እየተፈጠረና በዚህም ምክንያት ቤታቸው የፈረሰባቸው፣ እርሻቸው የተስተጓጎለባቸው፣ አካባቢያቸውን ለቅቀው የተፈናቀሉ ሁሉ የተረጋጋ ኑሮ ለመኖር አለመቻላቸውን ይጠቁማል፡፡

በዚህም መሠረት ገበሬው ተረጋግቶ የእርሻ ሥራውን እንዲከውን፣ የዕርዳታ ሥራው ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነፃ ሆኖ እንዲሠራጭ ሲባል ይህ የእርሻ ወቅት እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቆይ ያለ ቅድመ ሁኔታ በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረተ በተናጠል የሚተገበር የተኩስ አቁም ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ መታወጁን የፌዴራል መንግሥት አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት ስለትግራይ ቀውስ ያለው ምልከታ

የፌዴራል መንግሥት የተናጠል ውሳኔውን ባሳለፈ በማግሥቱ የተሰበሰበው የአሜሪካ ኮንግረንስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ቀውስን አጀንዳውን አድርጎ የመከረ ሲሆን፣ በዚህ ምክክር የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ተጠሪ ሮበርት ጎዴክና የአሜሪካ መንግሥት ተራድዶ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ኃላፊ በአስረጂነት ተገኝተው ነበር። 

የአሜሪካ ኮንግረንስ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባላት ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ ለሆኑት ጎዴክ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ፣ የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ላይ እንዴት ሊደርስ እንደቻለ የሚጠይቅ ነበር። 

ይሁን እንጂ የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊው ለጥያቄው እርግጠኛ የሆነላሽ ለመስጠት እንደማይችሉ በመግለጽ፣ ሁለት ነገሮችን ግን በግምት አንስተዋል።

የሕወሓት ኃይል ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በተወሰኑ የመካከለኛው የትግራይ አካባቢዎች ምናልባት ወታደራዊ የበላይነት ማግኘቱን፣ በተመሳሳይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ብሎ የትግራይ ክልል ግጭትን በተለየ መንገድ ለመፍታት እንዳቀደና የተኩስ አቁም ውሳኔ ለማሳለፍም ነገሮችን እያጤነ እንደነበርይህንንም ከምርጫው በኋላ ተግባራዊ ለማድረግ ስለመወያየቱ ይታወቃል ብለዋል።

በመሆኑም እርግጠኛ ምክንያቱን ለመናገር ባይቻልም፣ ሁለቱም ምክንያቶችተኩስ ማቆም ውሳኔው አስተዋጽኦ ሊኖራቸው እንደሚችል ግምታቸውን ተናግረዋል።

አሁን የተኩስ ማቆም ውሳኔው ከአንድ ወገን ብቻ የመጣ ከመሆኑ አንፃር በትግራይ ያለው ቀውስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በተከታይነት ተነስቶም ነበር። ጥቀያቄውን ያነሱት የኮንግረንስ አባል ሕወሓት መሣሪያውን ዝቅ አላደርግም ብሎ ከወሰነ፣ በክልሉ ብሎም በኢትዮጵያ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ጠይቀዋል።

ለጉዳዩ ምላሽ የሰጡት ጎዴክ አሜሪካ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ቀውስ በፍጥነት ሊቆም እንደሚገባ፣ ችግሩም በውይይት እንዲፈታ ያለማቋረጥ ለሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ማሳሰቧን ገልጸውሕወሓትም ሆነ የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት የወሰደውን ዕርምጃ መከተልና ለዚህም ተገዥ ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል። 

‹‹የሕወሓት አመራሮች በጦርነቱ መቀጠል እንደማይፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ በእነሱ በኩልም ተመሳሳይ የተኩስ አቋም ውሳኔ ይኖራል፡፡ ከኤርትራ በኩልም ይህ ይጠበቃል፤›› ብለዋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት የትግራይ ክልል ቀውስን ለመፍታት ከሚሹ እንደ አፍሪካ ኅብረትና ተመሳሳይ አቋም ካላቸው የአውሮፓ አገሮችና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር እየሠራ መሆኑን፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋርም ያልተቋረጠ ግንኙነት በማድረግ ላይ መሆናቸውን የገለጹት የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊው፣ አሜሪካ ችግሩን ሊፈቱ ይችላሉ ብላ ያመነችባቸውን የመፍትሔ አማራጮችንም ለኢትዮጵያ መንግሥት እንዳቀረበች ተናግረዋል። 

በትግራይ ክልል ያለው ቀውስም ሆነ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሊፈታ የሚችለው፣ ሁሉን አቀፍ በሆነ ብሔራዊ ውይይት መሆኑን የአሜሪካ መንግሥት እንደሚያምን የገለጹት ኃላፊው ይህንን ውይይት ለማመቻቸትም አሜሪካ ጥረት በማድረግ ላይ እንደምትገትኝ አስታውቀዋል።

‹‹የትግራይ ክልል ጉዳይን በተመለከተ የተለያዩ የተለያዩ ሞዴሎችን በመፍትሔነት ለኢትዮጵያ መንግሥት አቅርበናል። የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን አማራጮች ያጤናቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤›› ብለዋል። 

‹‹በመሆኑም አሁን ለአጭር ጊዜ የታወጀው የተኩስ አቁም ዘላቂ እንዲሆን ጥረት እናደርጋለን፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

የሕወሓት ኃይል የተኩስ ማቆም እንደማያደርግና የኤርትራና የአማራ ልዩ ኃይል ያሉበት ድረስ በመሄድ አካባቢውን እንደሚያስለቅቅ መግለጹን የጠየቁ ሌላ የኮንግረንሱ አባል፣ አሜሪካ ይህ በዚህ መንገድ እንዳይቀጥል ምን ልታደርግ እንደምትችል ጠይቀዋል።

በማከልም ይህ ሁኔታ ተባብሶ ከሄደ የትግራይ ክልልን ከኢትዮጵያመገንጠል የሚችል ከመሆኑ አኳያ የአሜሪካ መንግሥት አቋም በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እንደሆነ ተጠይቋል። 

በአጭሩ አሜሪካ አሁን ያለው ኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ተጠብቆ መቆየቱ ይጠቅማታል? ወይስትግራይ መገንጠል በአሜሪካ ጥቅም ላይ ምንም ጉዳት አያስከትልም? የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸዋል።

የአሜሪካ መንግሥት ይህ እንዳይፈጠር የተቻለውን እንደሚጥር የተናገሩት ሮበርት ጎዴክ፣ የአሜሪካ መንግሥት ፍላጎት የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ መሆኑን አስረድተዋል።

የትግራይ ክልል ጦርነትን ማን እንደቀሰቀሰውና የትኛው አካል አጥቂ የትኛው የተሰነዘረበትን ጥቃት ተከላካይ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ከወታደራዊ ግጭቱ አስቀድሞ ወደ ግጭት ሊወስዱ የሚችሉ ፖለቲካዊ ችግሮች እንደነበሩ፣ ነገር ግን ወደ ለየለት ጦርነት ለመግባት የመጨረሻ ምክንያት የሆነው የሕወሓት ኃይል ትግራይ ይገኝ በነበረው የመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ የወሰደው ጥቃት እንደሆነ ተናግረዋል። 

ይህንን ተከትሎም የአገሪቱ ጦር፣ የኤርትራ ጦርና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የተቀናጀ ውጊያ በሕወሓት ላይ መክፈታቸውን የተናገሩት ጎዴክ፣ በዚህም በንፁኃን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጥሰትና ቀውስ ማጋጠሙን በመግለጽ ማንም ይጀምረው ማንም ይህ ሰብዓዊ ጥስት ተገቢ እንዳልሆነና ሁሉም የተጦርነቱ ተሳታፊ ኃይሎች ለዚህ ድርሻ እንዳላቸው አስረድተዋል።

የሶማሊያ ወታደሮች በትግራይ ክልል ግጭት ውስጥ መሳተፋቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች መኖራቸውን መሠረት በማድረግ የአሜሪካ መንግሥት ይህንን በተመለከተ ያጣራው መረጃ፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ የሚያመለክቱ ዘገባዎችም እንዲሁ በአሜሪካ መንግሥት ተጣርተው እንደሆነም ተጠይቀዋል።

በሰጡት ምላሽም የኬሚካል ጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ የወጣውን የሚዲያ ዘገባ እንደተመለከቱ፣ ነገር ግን በአሜሪካ መንግሥት እንዳልተረጋገጠ ገልጸዋል።

የሶማሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያ መታየታቸውን ማረጋገጥ የተቻለ ቢሆንም፣ በጦርነቱ መሳተፋቸውን ግን በእርግጠኛነት መናገር እንደማይቻል አስረድተዋል፡፡ 

የሶማሊያ ወታደሮች እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ እንደቻሉ እንዲያብራሩ በተከታይነት ለቀረበላቸው ጥያቄየሶማሊያ ወታደሮች ኤርትራ ውስጥልጠና ይወስዱ እንደነበር ወደ ኢትዮጵያ የገቡትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

የአሜሪካ መንግሥት በትግራይ ክልል የጦር ወንጀል፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል ብሎ የሚያምን ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥትን በወንጀሎቹ ለምን እንዳልፈረጀም ተጠይቀዋል።

በሰጡት ምላሽም ከፍተኛና የተለያዩ ሰብዓዊ ጥሰቶች መፈጸማቸውን እንደሚያምኑ፣ ነገር ግን የፍረጃ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንን የወንጀል ፍረጃና ቃላቱን ለመፈጸም መረጃ ማሰባሰብና ከዓለም አቀፍ አንፃር ተንትኖ መወሰን የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት ጎዴክበአሁኑ ወቅት ሥራው እየተገባደደ እንደሚገኝና የመጨረሻ ውሳኔውን የማሳለፍ ኃላፊነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን ገልጸዋል።

የአሜሪካ መንግሥት በትግራይ ክልል ቀውስ ተጠያቂ ናቸው ባላቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት፣ የኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናትና በሕወሓት አመራሮች ላይ የጉዞና የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣሉ ያስገኘውን ውጤት እንዲያብራሩ ከኮንግረሱ አባላት የተነሳው ሌላው ጥያቄ ነበር። 

ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ጎዴክ፣አሜሪካ መንግሥት ማዕቀቡን ከጣለ ገና አጭር ጊዜ በመሆኑ ውጤቱን ለመለካት ወይም ለማመላከት እንደማይቻል ገልጸዋል።

ነገር ግን የትግራይ ክልል ጉዳይን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ሁለት መንገዶች እንደነበሩትአንድም ለችግሩ መፍትሔ ማበጀት ሌላው ደግሞ በግጭቱ መቀጠል እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ በግጭቱ መቀጠል የሚሆን ከሆነ፣ የአሜሪካ መንግሥትም ያሉትን የውጭ ፖሊሲ መሣሪያዎች በሙሉ መጠቀሙ እንደማይቀር ገልጸዋል። 

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -