Thursday, September 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየክብር ዶ/ር አበበች ጎበና በኮረና ቫይረስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

  የክብር ዶ/ር አበበች ጎበና በኮረና ቫይረስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

  ቀን:

  የአበበች ጐበና ህፃናት ክብካቤና ልማት ማህበር መስራች የሆኑት የክብር ዶ/ር አበበች ጎበና በ85 ዓመታቸው ዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2013 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

  ወ/ሮ አበበች ሕፃናት ክብካቤና ልማት ማህበሩን የመሰረቱት በ1972 ዓ.ም ለመንፈሳዊ ጉዞ በሄዱበት በወቅቱ ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሁለት ህፃናትን በመያዝ ነበር ፡፡ ላለፉት 41 ዓመታት በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናትን ተንከባክበው ለቁምነገር ያበቁ ሲሆን፣ በተለያዩ የድህነት ቅነሳ ፕሮግራሞችም ከ1.5 ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ መስጠታቸውም ይነገራል።

  ወ/ሮ አበበች ላደረጉት የሰብአዊነት አገልግሎቶች በተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ታላላቅ ሽልማቶችና እውቅናዎችን እንዲሁም ከጅማ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ድግሪ አግኝተዋል።

  ወ/ሮ አበበች በቅርቡ በኮሮና በሽታ ምክንያት በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ህሙማን ክፍል ሲረዱ እንደነበር ይታወሳል።

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img