Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናብልጽግና ተጨማሪ 39 የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸነፈ

ብልጽግና ተጨማሪ 39 የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸነፈ

ቀን:

በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብና በሲዳማ ክልሎች ይፋ በተደረጉ ውጤቶች ብልጽግና ፓርቲ ካሁን ቀደም ካሸነፋቸው አሥር የፓርላማ መቀመጫዎች በተጨማሪ 39 መቀመጫዎችን ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ ከገለጻቸው ውጤቶች መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍተሕ (ኢዜማ) ፓርቲ እያንዳንዳቸው አንድ አንድ የፓርላማ መቀመጫዎችን እግኝተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ኢዜማ በደቡብ ክልል አንድ የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፍ ችሏል፡፡

የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽንስ አማካሪ ወ/ሪት ሶልያና ሽመልስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት፣ ምርጫ የተከናወነባቸው የምርጫ ክልሎች ሙሉ ለሙሉ ውጤታቸውን ወደ ማዕከል ልከዋል፡፡ ይሁንና ውጤቶች ሲመጡ የጎደሉ ሰነዶች ሊኖሩ ስለሚችሉ እነርሱን ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

የምርጫ ቦርድ ቅሬታ ከቀረበባቸው 165 የምርጫ ክልሎች መካከል በደቡብ 40፣ በኦሮሚያ ሁለት፣ በድሬዳዋ አንድ፣ በአፋር 21፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ስድስት፣ አዲስ አበባ 23፣ ሲዳማ ስምንት፣ አማራ 49 እና ጋምቤላ 3 የምርጫ ክልሎች ይገኙበታል፡፡

ቅሬታዎችን አደራጅቶና የሕጋዊ ሰነድ ቅርጽ አስይዞ ለማቅረብ ሦስት የሕግ ድርጅቶች ተቀጥረው በ30 ሰዎች በሦስት ቡድኖች ተከፍለው እየሠሩ እንደሚገኙም ወ/ሪት ሶልያና አስታውቀዋል፡፡ ቦርዱ እነዚህን ቅሬታዎች እስከ ሐሙስ ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓም ድረስ አጠናቅቆ ውሳኔ እንደሚሰጥም ጠቁመዋል፡፡

በፓርቲዎች እየቀረቡ ያሉ ቅሬታዎች “በምርጫ ጣቢያዎች መግባት የማይገባቸው ሰዎች ገብተዋል” እና “አስተዳደራዊ ውሳኔ ይሰጥልን፣ የምርጫ ማዳመር ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎች ሳይገኙ ተከናውኗልና እንደገና ቆጠራ ይከናወን ወይንም ውጤት ተሰርዞ ድምጽ በድጋሚ ይሰጥ” የሚሉ እንደሚገኙበት ወ/ሪት ሶልያና ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...