Wednesday, March 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ሆኖ ተመዘገበ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. የዋጋ ግሽበት 24.5 በመቶ በመሆን በግንቦት ወር ከነበረው የ19.7 በመቶ ግሽበት የላቀ በመሆን መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበሩት ወራቶች የነበረውና ዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በሰኔ ወርም እንደቀጠለ የተገጸ ሲሆን፣ በተጨማሪም ሥጋ፣ የምግብ ዘይት፣ ቅቤ፣ ቅመማ ቅመም፣ በርበሬና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው፣ ለዋጋ ግሽበቱ ምጣኔ በፍጥነት መጨመር አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ19 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንና ከምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች ደግሞ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ ማለቱን መረጃዉ ያመላክታል፡፡

ዋጋው ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ ልብስና ጫማ፣ አነቃቂዎች (ጫት)፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት መሥሪያ ዕቃዎች (የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶና የቤት ክዳን ቆርቆሮ)፣ ሕክምናና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች