Saturday, March 2, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሥጋት ሆኖ የቀጠለው በጎርፍ መጥለቅለቅ

ሥጋት ሆኖ የቀጠለው በጎርፍ መጥለቅለቅ

ቀን:

አብዛኞቹ ሰቀቀን ውስጥ ገብተዋል፡፡ በተለይም ገደል አፋፍና ቁልቁለታማ ቦታ ላይ ኑሯቸውን ያደረጉ ሰዎች የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሲሆኑ በተደጋጋሚ ይታያል፡፡ ይኼም የሆነበት ዋነኛ ምክንያት ክረምት በመጣ ቁጥር ከባድ ዝናብ በሚዘንብ ጊዜ ጎርፍ ተንደርድሮ በመግባቱ ነው፡፡ ችግሩ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮችን አካሏል፡፡

በዚህም የተነሳ በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኬንያና ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ አገሮችም ከባድ ዝናብ ከመከሰቱ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ የጎርፍ አደጋ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ መሆናቸው የማይዘነጋ ነው፡፡ ኢትዮጵያም በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ውጥረት ውስጥ ከገቡ አገሮች መካከል አንዷ ሆናለች፡፡

በዚህም የተነሳ ክረምት በመጣ ቁጥር ለጎርፍና ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ከቀያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል፡፡ ንብረታቸውን አጥተዋል፡፡ ይኼንንም ችግር በከፊልም ቢሆን ለመቅረፍ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከሌሎች ተቋሞች ጋር በቅንጅት እየሠራ ይገኛል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሐምሌና ነሐሴ ውስጥ በሚኖረው ከፍተኛ ዝናብ በንብረትም ሆነ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ የሚከሰትባቸውን ቦታዎች የመለየት ሥራ እንደተሠራ የገለጹት ዳይሬክተሩ የቅፅበታዊ ጎርፍና የወንዝ ሙላት የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የጎርፍ ማፍሰሻ ግንባታ እንዲሁም ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በጎርፍ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየተሠራ እንደሚገኝ አቶ ደበበ አስረድተዋል፡፡

በጎርፍና በመሬት መንሸራተት ሥጋት ውስጥ ያሉትን አካባቢዎች በተመለከተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ለማኅበረሰቡ በማሠራጨት ላይ እንደሚገኙና ከተከሰተ በኋላም አፋጣኝ የሆነ ምላሽ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል፡፡

የብሔራዊ ሚቲሪዮሎጂ ኤጀንሲ የክረምት ወቅትን በተመለከተ ባደረገው ትንበያ፣ መደበኛ የሆነ ዝናብ እንደሚጥል አስታውቋል፡፡ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አማራ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ድሬዳዋ፣ አዲስ አበባና ሐረር ለጎርፍ አደጋ ተጠቂ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በእነዚህም ቦታዎች ላይ ከሁሉም የክልል መስተዳድሮች ጋር የጎርፍ አደጋውን ለመከላከል በቅንጅት እየተሠራ እንደሆነና የመሬት መንሸራተት የሚደርስባቸው ቦታዎች መለየታቸውን አክለዋል፡፡

የመሬት መንሸራተት ከሚከሰትባቸው ቦታዎች መካከልም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰብና ትግራይ ክልሎች እንደሚገኙ፣ አብዛኛውን ጊዜም ደቡብ ክልል ለዚህ አደጋ ተጋላጭ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያም በአርሲ ዞን ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ2000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቦታውን ለቀው ወጥተዋል የሚለው መረጃ እንደሌላቸው፣ ይሁን እንጂ ክልሉ ለኮሚሽኑ መረጃውን ከሰጠ አፋጣኝ የሆነ ድጋፍ እንደሚደረግለት አብራርተዋል፡፡

በቅድመ መከላከል ደረጃም የሚወጣው መዋለ ንዋይ አነስተኛ መሆኑን ነገር ግን የጎርፍ አደጋው ሲከሰት ማኅበረሰቡን መልሶ ለማቋቋም ከባድ ወጪ እንደሚጠይቅ ይኼም ቅድመ መከላከሉ ላይ መሥራት እንደሚገባ እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡

ዓምና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ 7.5 ሚሊዮን ዜጎች በየስድስት ወሩ በዓመት ሁለት ጊዜ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ሪፖርተር መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ድጋፉም የተከናወነው በሦስት አካላት ሲሆን፣ መንግሥት፣ 60 በመቶውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ደግሞ 22 በመቶውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መያዛቸው የሚታወስ ነው፡፡

ባለፉት ዓመታትም በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ በአማራ፣ በጋምቤላና በሶማሌ ክልሎች ውስጥ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ እንደነበር፣ 1,095,350 ዜጎች ላይ የጎርፍ አደጋ እንደደረሰና ከእነዚህም ውስጥ 313,179 ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...