Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

እኔ የምለዉየፖለቲካ አለመረጋጋት ባስከተላቸው መዘዞች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምን ያህል ተጎድታል?

የፖለቲካ አለመረጋጋት ባስከተላቸው መዘዞች የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ምን ያህል ተጎድታል?

ቀን:

 በሀብታሙ ግርማ ደምሴ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ፣ የውጭ ግንኙነትናብሔራዊ ደኅንነት ዓውዶች እየተስተዋለ ካለው ያለ መረጋጋት ሁኔታ መነሻዎች በተለያዩ አስረጅ አመክንዮዎች መግለጽ (መተንተን) ይቻላል፡፡ በዚህ መጣጥፍ አሰናጂ የውስጥ ፖለቲካ አስተዳደር ችግሮች ለነበርንበትወይም ላለንበት የውስጥና የውጭ ችግሮቻችን ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ የፖለቲካ አለመረጋጋቱ ቀዳሚ ተጠቂ የአገሪቱዝብ ውድይወት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተደጋጋሚ እንደታየው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተለያዩ የውጭ ኃይሎች ለመደፈር የበቃው፣ የውስጥ ፖለቲካችን በተናጋባቸው ወቅቶች ነው፡፡ 1969 ዓ.ም. ሶማሊያ ኢትዮጵያን የወረረችው የወቅቱ መንግሥት የውስጥ ፖለቲካን መቆጣጠር ባለመቻሉ፣ የተለያዩ የፖለቲካይሎች ነፍጥ አንስተው አገር በተዳከመበት ወቅት ነው፡፡ ዘንድሮም የሱዳን መንግሥት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቶ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ሊደፍር የበቃው፣ በውስጥ ፖለቲካ ሽኩቻ አገሪቱ ስለተዳከመች ክፍተቱን ተጠቅሞ ነው፡፡ እንደ ግብፅይነት ቋሚ የኢትዮጵያ ጠላቶች በውስጥ ጉዳያችን እንዳሻቸው እንዲገቡ እየፈቀድንላቸው ያለው፣ አሁንም ውስጣዊ ፖለቲካችንን በአግባቡ ማስተዳደር እያቃተን ስለሆነ ነው፡፡

ምዕራባዊያን አገሮች የፖለቲካ አለመረጋጋት በገጠሙን ወቅቶች ሁሉ ጫናቸውን ለማሳረፍ ሲሞክሩ ነው የተስተዋለው፡፡ ፖለቲካችን አለመረጋጋቱ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በውጭ ዕርዳታና ድጋፍ ጥገኛ እንድንሆን ከማድረጉ ባለፈ፣ የአገራችንን ክብርና ሉዓላዊነት ዝቅ ሲያደርግ ኖራል፡፡ ዛሬም እንደገርናዝብ እየተፈታተነን ያለ ሁነት ነው፡፡

- Advertisement -

በዚህ መጣጥፍ የፖለቲካ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያደረሰውን፣ እያደረሰ ያለውንና ወደፊት የሚያደርሰውን ኢኮኖሚያዊ ውድመት ለማሳየት በሁለት የተፅዕኖ መስመሮች (Channels) ክፍሎች ለመፈተሽ ተሞክሯል፡፡ የመጀመርያው የፖለቲካ አለመረጋጋቱ ለጦርነትናግጭቶች በመዳረግ በሚያደርሰው ውድመት ነው፡፡ ሁለተኛው መስመር ደግሞ የፖለቲካ አለመረጋጋቱ የመንግሥትን ቅቡልነት በመቀነስ፣ ሙስናንና መልካም አስተዳደርጦትን ከማስከተል አንፃር በሚኖረው ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ነው፡፡

ጦርነትና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶቹ

የፖለቲካ አለመረጋጋትና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣው ግጭት የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ላይ ከሚያደርሰው በተጨማሪ፣ በኢኮኖሚ አስተዳደር ላይ የሚያመጣው ጫና አለ፡፡ ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ በመካከለኛና ረዥም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶች ሳይሆን፣ በጣም በአጭር ጊዜ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩር ስለሚያስገድድ ነው፡፡ የፖለቲካ አለመረጋጋቲ አንዱ ነፀብራቅ የሆነው የኢኮኖሚ ቀውስ ለማከም በሚወሰዱ የፖሊሲ ዕርምጃዎች መለዋወጥ የማክሮ ኢኮኖሚ ከባቢውን ያልተረጋጋ ስለሚያደርገው፣ የኢኮኖሚውይሎች በሚወስዱት ቁልፍ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውሳኔዎች፣ ማለትም የፍጆታና ኢንቨስትመንት ውሳኔዎች (Consumption and Investment Decisions) ላይ ከባድ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ በውጤቱም አሁናዊ የኢኮኖሚድገትን መግታቱ ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊት የኢኮኖሚውን የማደግ አቅም መሠረቶችን ስለሚያወድም ተፅዕኖውም ጊዜ ተሻጋሪ ያደርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ታሪክ እንደሚነግረን የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ በውስጥ ፖለቲካ ከባቢ መረጋጋት የተወሰነ ነው፡፡

የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በተለይ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ነበረው የተሳሳተ ፖሊሲ፣ አገሪቱ በገጠማት የፖለቲካ ቀውስ ከፍተኛ ዋጋ ከፍላለች፡፡ በአፄው አገዛዝ የመጨረሻዎቹ ዓመታት ለጦርነት ይወጣ ነበረውን የወቅቱን ጥቅል አገራዊ ምርት 1.9 በመቶ ነበር፡፡ ይህ የመከላከያ ወጪ እየጨመረ መጥቶ በወቅቱ የዕድገት ተስፋ እያሳየ የነበረውን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት ለመግታት ችሏል፡፡ በዚህም የአፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የቀረፃቸው ሁለት የአምስት ዓመታት (1958 እስከ 1962 እና 1963 እስከ 1967 ዓ.ም.) የልማት ዕቅዶች ተፈጻሚ መሆን አልቻሉም፡፡ እንዲያውም ሁለተኛው ዕቅድ ዘመን ሳያልቅ ነበር ንጉሡ በወታደራዊው ደርግ ከሥልጣን የተወገዱት፡፡

በደርግ ዘመንም እንዲሁ ፖለቲካዊ ቀውሱ በርክቶ አገሪቱ በሁሉም ማዕዘናት ነፍጥ ባነገቡ ፖለቲካ ቡድኖች ተወጥራ ቆይታለች፡፡ 17 ዓመታት የደርግ ሥልጣን ወቅት ኢትዮጵያ በዓመት ለጦርነት ያፈሰሰችው ገንዘብ ከአገሪቱ ጥቅል አገራዊ ምርት በአማካይ ሦስት በመቶ ይሆናል፡፡ ከመንግሥት ዓመታዊ በጀት ደግሞ በአማካይ 17 በመቶ የሚሆነው ለጦርነቱ የሚውል ነበር፡፡ 1969 እስከ 1971 .ም. በዘለቀው የኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት ወቅት ዓመታዊ የጦርነት በጀቱ ወደ 26 በመቶ አሻቅቦ እንደነበር በጥናት የተደገፉ ማስረጃዎች አሉ፡፡

በደርግ የአገዛዝ ዘመን ከነበረው አውዳሚ ጦርነት ኢኮኖሚው በወጉ ሳያገግም 1990 .ም. ገደማ አገሪቱ ወደ ሌላ ጦርነት ለመግባት የበቃችው እንዲሁ በፖለቲካ አስተዳደር ድክመት ነበር፡፡ 1990 እስከ 1992 .ም. የዘለቀው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት አገሪቱን 2.9 ቢሊዮን ዶላር አስወጥቷታል፡፡ በጦርነቱ ዓመታት ለመከላከያ ይውል የነበረው ዓመታዊ በጀት ከመንግሥት ጠቅላላ የመደበኛ በጀት 49.8 በመቶ ነበር፡፡ አገሪቱ ከውጭ የፋይናንስ ምንጮች ታገኝ የነበረው ብድርና ዕርዳታ ከጦርነቱ በፊት ከነበረው 700 ሚሊዮን ዶላር አማካይ ዓመታዊ ፍሰት ወደ 500 ሚሊዮን ዶላር ወርዷል፡፡ ይህም በጦርነቱ ምክንያት የውጭ ዕርዳታ 28.6 በመቶ እንዲቀንስ ሆኗል ማለት ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓመታዊ በጀቱን በኢሕአዴግ ዘመነ ሥልጣን የፖለቲካው ጉድለቱ አንዱ ገጽታ የሆነው፣ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ባለመፍታታቸው አገሪቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ ውስጥ ገብታለች፡፡ በኢሕአዴግ መንግሥትተቀረፁት ሁለቱ የአምስት ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች (GTP-I እና GTP-2) በተግባር ሳይውሉ የቀሩበት ምክንያት፣ ይኸው የፖለቲካ አለመረጋጋቱ ባመጣው መዘዝ ነው፡፡ በተለይም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን (GTP-2) የፖለቲካ አለመረጋጋቱ በርትቶ፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በጣም ጎድቶት እንደነበር የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡

የዓለም የገንዘብ ድርጅት እ.ኤ.አ. 2018 ያሳተመው ጥናታዊ ሪፖርት አንዱ ነው፡፡ በጥናቱ መሠረት 2008 . (..አ. 2015) በአገሪቱ የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስና የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎች የኢኮኖሚ ዕድገቱ ከባለሁለት አኃዝ ወደ 7.7 በመቶ እንዲወርድ አድርጎታል፡፡ (Shumete A. and Waltaji, M.D. 2019) በኢትዮጵያ በተለይ 2008 .ም. ወዲህ በተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት በኢንተርፕራይዝ ልማት ላይ ያለውን ተፅዕኖ ‹‹Effect of Corrupption and Political Instability on Enterprise Innovativeness in Ethiopia: Pooled Data Based›› በሚለው ጥናታቸው ለመመርመር ችለዋል፡፡ በጥናታቸው ግኝት መሠረት የፖለቲካ አለመረጋጋት በአገሪቱ በሁሉም የኢንተርፕራይዝ ደረጃዎች ያሉ ቢዝነሶች (በማይክሮ፣ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች) የመፍጠር አቅም (Enterprise Innovativeness) እና ትርፋማነት ትርጉም ያለው አሉታዊ ተፅዕኖ (Significant Negative Effect) አሳድሯል፡፡

በአዲሱ የለውጥ መንግሥት ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ የገባው የኢትዮጵያ የአሥር ዓመት ብሔራዊ ዕቅድ (ፍኖተ ብልፅግና) ተፈጻሚነቱ አገሪቱ በሚኖራት የወደፊቱ ፖለቲካ መረጋጋት ላይ ይወሰናል፡፡ ዕቅዱ የመጀመርያ ዓመት በሆነበት 2013 .. የፖለቲካ አለመረጋጋቱ በወለደው ግጭት ኢኮኖሚው ፈተና ውስጥ ገብቷል፡፡ ከኅዳር ወር 2013 .ም. ጀምሮ በትግራይ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ምን ያህል እየጎዳው እንዳለ አየኖርን ያለነው እውነት ነው፡፡

እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስፈጸም፣ እንዲሁም በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ፍጆታዎችን ለማቅረብ አገሪቱ በወር በአማካይ አንድ ቢሊዮን ብር (20 ሚሊዮን ዶላር) እያወጣች ትገኛለች፡፡ የትግራይ ኢኮኖሚ እቅስቃሴ በአጠቃላይ ቆሟል ማለት ይቻላል፡፡ በዚህም ከክልሉ ሊሰበሰብ የሚገባ የነበረ ዓመታዊ ግብር የለም፡፡ ክልሉ የአገሪቱን ሃያ በመቶ የኢንዱስትሪ/ማኑፋክቸሪንግ የማምረት አቅም ያለው ነው፡፡ በመሆኑም በአገር ውስጥ ምርት አቅርቦት ላይ በሚፈጥረው ጫናና ተያያዥ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶቹ (በዋጋ ግሽበት፣ በንግድና አገልግሎት ዘርፎች መቀዛቀዝ፣ ሥራ አጥነት እንዲጨምር) በተጨማሪ ከኢንዱስትሪው ዘርፍ ይገኝ የነበረ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ቀንሳል፡፡

 በትግራይ ባለው ግጭት ሰበብ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ አገሪቱ ከውጭዕርዳታ ምንጮች ታገኝ የነበረውን 240 ሚሊዮን ዶላር ገደማ አጥታለች፡፡ አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለመስጠት ብላ የነበረውን 130 ሚሊዮን ዶላር በጀት ድጎማ አግዳለች፡፡ የአውሮፓ ኅብረትም እንዲሁ 109 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አግዷል፡፡

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ባወጣው ሪፖርት መሠረት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ጉዳት እየተንገዳገደ ያለው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ጦርነት ተጨምሮበት የሚጠብቀው ከባድ ፈተናን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ እ.ኤ.አ. 2021 የኢኮኖሚ ዕድገት ዜሮ በመቶ እንደሚሆን ትንበያ አውጥቷል፡፡

በአጠቃላይ ጦርነት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ የመረመሩ የጥናት ውጤቶች እንዳስቀመጡት፣ አገሪቱ በጦርነት ውስጥ ባለፈችባቸው ጊዜያት ሁሉ ኢኮኖሚው ቁልቁል ወርዷል፡፡ በድኅረ ጦርነት ዓመታት ደግሞ ኢኮኖሚው የተሻለ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡ በመሆኑም በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ያለው ጦርነት በአጭሩ ሊቋጭ የሚችልበት መንገድ ካልተመቻቸ በቀጣዮቹ ወራትና ዓመታት ኢኮኖሚያችን ክፉኛ መጎዳቱ አይቀሬ ነው፡፡

የመንግሥት ቅቡልነት፣ መልካም አስተዳደርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ

 ከዚህም ባለፈ የፖለቲካ አስተዳደሩና መንግሥት የነበራቸው ቅቡልነት መውረድ፣ እንዲሁም የተንሰራፋው ሙስና በድምሩ ከአገር ውስጥ የሚሰበሰበው ግብር አነስተኛ እንዲሆን አድርጓል፡፡ የምርት ኃይሎች የሆኑት እንደ ሰው ኃይል፣ መሬትና ካፒታል ከአቅማቸውእጅጉ ባነሰ ሁኔታ እንዲሠሩ ሆኗል፡፡ የፖለቲካ አስተዳደሩ አፋኝና ለዜጎች በነፃ ለማሰብና ለመሥራት አሜኬላዎችን የፈጠረ ስለነበር፣ ዜጎችመፍጠር አቅማቸውን (Entrepreneurial Skills) ተጠቅመው በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ላይ እንዳይሳተፉ፣ በዚህም ራሳቸውን ጠቅመው ሌሎችን እንዳይጠቅሙ አድርጓል፡፡

የፖለቲካ አስተዳደሩ አሳታፊ አለመሆኑ ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ ሊገኝሚችለውን ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪና የዕውቀት/ቴክኖሎጂ ሽግግር አቅም አጥታለች፡፡ ለአብነትም በሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግሥት ላይ የነበራቸውን ተቃውሞ ከገለጹባቸው መንገዶች አንዱ በሕጋዊ መንገድ በባንኮች የሚልኩትን ገንዘብ በማቆም፣ በሕገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪ አካላት በመላካቸው ሊገኝ ይችል የነበረው ውጭ ምንዛሪ በእጅጉ ቀንሷል፡፡ ገንዘቡ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ መሆኑ ካደረሰው ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ በላይ፣ በአገሪቱ ደኅንነትም ላይ ቀጥተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ አድርሷል፡፡ በዚህም የተለያዩ ፀረ ሰላም ኃይሎች እነዚህ ሕገወጥ ፋይናንስ ምንጮችን ተጠቅመው በሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ የጥፋት ዓላማቸውን ለማሳካት የሚያስችላቸውን እንቅስቃሴዎች ለማሳለጥ ችለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የደኅንነት ተግዳሮቶች ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ረገድ የነበራቸው ሚና የላቀ ነበር፡፡

 2010 .ም. የመጣውን አገራዊ ለውጥ ተከትሎ ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት አሁንም የፖለቲካ አስተዳደሩን በአግባቡ ባለመምራቱ፣ አያሌ የተቃውሞ ኃይሎች በአገር ቤትና በውጭ አገር ሆነው ሰላማዊ ያልሆነ የትግል መስመር እንዲከተሉ ምክንያት እንዳይሆን ያሠጋል፡፡ እነዚህ ኃይሎች በዳያስፖራው ማኅበረሰብ ውስጥ ባላቸው ተፅዕኖ ከዳያስፖራ ሊገኝ የሚችለውን የውጭ ምንዛሪ፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደ ቀደሙት ዓመታት ባክኖ እንዲቀር እያደረገ ይገኛል፡፡ ሌላው ቢቀር በሰሞኑ የምዕራባውያኑ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ጫና ጀርባ እነዚህ በመንግሥት ላይ ያኮረፉ የፖለቲካ ኃይሎች እጅ ረዥም እንደሆነ ከማናችንም የተሰወረ አይደለም፡፡

የፖለቲካ አለመረጋጋቱ ከፈጠራቸው ተግዳሮቶች ሌላኛውአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት መዳከም ነው፡፡ አገሪቱ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ቀርቶ ያላትን የኢንቨስትመንት ሀብቶች አስጠብቃ መቆየት አልቻለችም፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ አለመረጋጋቱ ውጤት በሆኑ የተለያዩ ግጭቶች የወደመው የኢንቨስትመንት ሀብት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በዚሁ ምክንያት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ምክንያቶች ሥራቸውና ኑሯቸው የወደመባቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር የትየለሌ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የፖለቲካውን ጉዳይ መፍታት አገሪቱ ያላትን የሰው ኃይል፣ የተፈጥሮ ሀብትና የካፒታል አቅም በአግባቡ አስተባብራ እንድትጠቀም መንገዱን ይጠርጋል፡፡ በእርግጥ የፖለቲካ መረጋጋቱ ለኢኮኖሚው ዕድገት መሠረት የሆኑትን ቅቡልነት ያለው መንግሥት ለመመሥረት ያስችላል፡፡ በዚህም አገሪቱ የሚተገበሩ የልማት ፖሊሲዎች ይኖሯታል፡፡ በውጤቱም የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት የሚቻልበት ዕድል ይሰፋል፡፡

ቅቡልነት ያለው መንግሥት ሲኖር ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን በአምራች ዕድሜ ያለ ሕዝባችን ወደ ምርት ኃይል በቀላሉ የመቀየር ዕድል ይኖራታል፡፡ ዜጎች በተሰማሩበት ሥራ ሁሉ በአገራዊ ስሜት ይንቀሳቀሳሉ፣ ለአገር ተቆርቃሪ የሆነ የሰው ኃይል ካለ በምርት ሒደቱ ሁሉ የሥራ ዲሲፕሊን የተጠበቀ ይሆናል፣ የሥራ ሰዓት ይከበራል፣ የሥራ ሒደትና የሥራ አመራሩ ከሙስና የራቀ ይሆናል፡፡ በድምሩ ለምርትና ምርታማነት እጅግ ወሳኝ የሆኑ ባህሪያዊና ተቋማዊ መደላድሎችን ይፈጥራል፡፡ በውጤቱም ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ማኅበረሰባዊ ለቁሳዊና መንፈሳዊ ለውጥ ለማምጣት ይቻላል፡፡

በተረጋጋ የፖለቲካ ዓውድ የተመሠረተ መንግሥት ከአገሪቱ ኢኮኖሚ መሰብሰብ የሚችለውን ግብር ማግኘት ይቻላል፡፡ ይህም ዜጎች የግብር ግዴታቸውን በወቅቱና በታማኝነት የመክፈል ተነሳሽነታቸው ስለሚጨምር ነው፡፡

የፖለቲካ መረጋጋት ካለ መንግሥት ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ለአገራቸው ማበርከት የሚችሉትን ዕምቅ አቅም አውጥተው ሕዝባቸውን ለሚጠቅሙ የልማት ሥራዎች ማዋል እንዲችሉ ይደረጋል፡፡ በዚህም ከዳያስፖራው የሚገኝ የውጭ ምንዛሪን ፍሰት ቢያንስ በሁለት መንገዶች እንዲጨምር ይሆናል፡፡ አንደኛው በሕጋዊ መንገድ በባንኮች በመላክ ሲሆን፣ በተጨማሪም የሚልኩትን የነፍስ ወከፍ ገንዘብ መጠን እንዲጨምር ከማበረታት አንፃር ባለው በጎ ሚና ነው፡፡ በተጨማሪም የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት ካለ ጥቅል አገራዊ ኢንቨስትመንት (በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት) ይጨምራል፡፡ በዚህም ለማክሮ ኢኮኖሚው መረጋጋት ቁልፍ የሆኑትን የኢኮኖሚ ዕድገትና የሥራ ዕድል፣ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ግኝት በተሻለ ሁኔታ ማሳካት ይቻላል፡፡

የፖለቲካ መረጋጋት ሲሰፍን በተሻለ ሁኔታ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት መንግሥታዊ ሥርዓትን መመሥረት ይቻላል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ መንግሥታዊ ሥርዓት ዕውን ሲሆን፣ ሙስናን ለመከላከል ተቃማዊ አቅም መገንባት ይቻላል፡፡ በዚህም በሙሰኛ ባለሥልጣናት ከአገር የሚኮበልለውን የውጭ ምንዛሪ ሀብት ማዳን ይቻላል፡፡

የፖለቲካ መረጋጋት ሲኖር መንግሥት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና የማኅበረሰብ አቀፍ ልማትን ሊያጎለብት ይችላል፡፡ ዜጎችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማሳተፍ ጉልበት፣ ገንዘብ ወይም ዕውቀት ያላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች ለሌሎች በማካፈል ፍትሐዊ የማኅበረ ኢኮኖሚ ልማትን ማሳለጥ ይቻላል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽንኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...