Sunday, April 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አቢሲኒያ ባንክ ከዓምናው የ1.8 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ትርፍ አስመዘገበ

ተዛማጅ ፅሁፎች

አቢሲኒያ ባንክ በተጠናቀቀው የ2013 የሒሳብ ዓመት ከታክስና ሕጋዊ ተቀናሾች  በፊት 2.87 ቢሊዮን ብር ማትረፉንና አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ከ88.7 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱን ገለጸ፡፡

ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ ያስመዘገበው የትርፍ መጠን ከቀዳሚው ዓመት የትርፍ ምጣኔው ጋር ሲነፃፀር ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው መሆኑ ታውቋል፡፡ ባንኩ በ2012 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት አስመዝግቦት የነበረው የትርፍ መጠን 1.08 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

ባንኩ የ2013 የሥራ አፈጻጸሙን አስመልከቶ እንዳስታወቀው፣ በሒሳብ የዓመቱ እሰበስባለሁ ብሎ ካቀደው 21.38 ቢሊዮን ብር በላይ ማከናወን የቻለ ሲሆን፣ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ብቻ 41.6 ቢሊዮን ብር አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ ማለትም ከዕቅዱ አንፃር 193 በመቶ ማሳካት መቻሉን ያሳያል፡፡ በ2013 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ላይ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ88.7 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ በ2012 መጨረሻ ላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 47.6 ቢሊዮን ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ በተመሳሳይ በጀት ዓመት በግል ባንኮች ከተሰበሰበው ተጨማሪ የተቀማጭ ገንዘብ አንፃር ሲመዘን ከፍተኛ የሚባል መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

በሒሳብ ዓመቱ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ አስቀማጭ ደንበኞችን ማፍራት ስለመቻሉ የሚያመለክተው የባንኩ መረጃ፣ አጠቃላይ የባንኩን የአስቀማጭ ደንበኞችቁጥር 5.1 ሚሊዮን እንዳደረሰው ጠቁሟል፡፡ ባንኩ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር 607 አድርሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች