Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ውድቅ አደረገች

ቀን:

የኤርትራ ጦር መረጋገጥ በሚችል አኳኃን ከትግራይ እንዲወጣ የውሳኔሳቡ ያሳስባል

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሰብዓዊ ምክር ቤት ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን የውሳኔ ሐሳብ (Resolution)፣ ፖለቲካዊ ዓላማ ያነገበ እንደሆነ በመግለጽ ውድቅ አደረገች። 

የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ከትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ ጋር የተገናኘ ሲሆን፣ በዚህም የኢትዮጵያ መንግሥት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሰብዓዊ መብቶች ማክበርና ማስከበር ኃላፊነት እንዳለበት ይገልጻል። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህ አንፃር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ሳይፈጸሙ እንዳልቀሩ ሪፖርት የተደረጉ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብትና የስደተኞች መብቶችን የተመለከቱ ጥሰቶችጅምላ ጭፍጨፋ፣ ፆታዊ ጥቃት፣ ንፁኃንን ያልለየ ወታደራዊ ጥቃት እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በአካባቢው በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያትም ለነዋሪዎች የዕለት ዕርዳታ ለማድረስ አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩናዕርዳታራተኞች ላይ ጭምር ጥቃትና ግድያ መፈጸሙ እንዲሁም በአካባቢው የሕክምና ተቋማት ላይ ውድመት መድረሱ ችግሩን እንዳባባሰው ይገልጻል። 

በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ሰብዓዊ ጥሰትና ቀውስ የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ እንዳለበት፣ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ የወሰደውን የተናጠል ተኩስ ማቆም፣ እንዲሁም ለሰብዓዊርዳታ የሚያደርገውን ጥረትና የተፈጸሙ ጥሰቶችን ከተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመሆን በጋራ ለማጣራትና የሕ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እየወሰደ ያለውን ጥረት በበጎነት የሚቀበለው መሆኑንም አመልክቷል። 

በመሆኑም በክልሉ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ፣ እንዲሁም ሁሉም የግጭቱ ተዋናዮች ለዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች እንዲገዙና በክልሉ ያልተገደበ የሰብዓዊርዳታ ማቅረብ እንዲቻል እንዲያደርጉ አሳስቧል። 

በተጨማሪም በትግራይ ክልል የሚገኘው የኤርትራ ጦር በአስቸኳይና ሊረጋገጥ በሚችል አኳኃን ከአካባቢው ለቆ እንዲወጣ አሳስቧል። 

በዚህ የውሳኔሳብ ላይ የተገለጹ ጉዳዮችና በክልሉ ያለው የሰብዓዊ መብቶች አያያዝን በተመለከተ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር በመከታተል፣ በቀጣዩ የምክር ቤቱ ስብሰባ የተስተዋሉ ለውጦችን ሪፖርት እንዲያደርጉ ወስኗል። 

ውሰኔውን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ምሽት ባወጣው መግለጫ፣ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውሳኔን በማጣጣል ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ የውሳኔ ሐሳቡን በማርቀቅ ለምክር ቤቱ ያቀረበው የአውሮፓ ኅብረት እንደሆነ በመግለጽ ድርጊቱንም ፖለቲካዊ ዓላማ ያነገበ እንደሆነ አስታውቋል።

ይህ በአውሮፓብረት የቀረበ የውሳኔሳብ እንዳይጸድቅ የኢትዮጵያ መንግሥት ከጅምሩ አንስቶ ሲጠይቅ የነበረ መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሙሽን ጋር በጋራ በመሆን የተፈጸመውን ጥሰት እየመረመረ ባለበትና ምርመራው ባልተጠናቀቀበት ወቅት፣ የአውሮፓብረት የውሳኔ ሐሳቡ ማቅረቡ እየተደረገ ባለው ምርመራን የሚያደናቅፍ ጣልቃ ገብነት እንደሆነ ቀድሞ ማሳሰቡን መግለጫው ያመለክታል።

በመሆኑም የምርመራ ሥራ እየተከናወነ ባለበትና የዚህ ውጤት ሳይታወቅ የውሳኔ ሐሳቡን ለማጽደቅ የተደረገው መጣደፍ ምክንያቱ ፖለቲካዊ ዓላማ እንጂ፣ ሌላጋዊ ወይም ሞራላዊ ምክንያት ሊኖር እንደማይችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።

በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት የውሳኔ ሐሳቡን እንደማይቀበል የገለጸው መግለጫው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎቹን ለማክበር ቁርጠኛ እንደሆነ ገልጿል።

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙትም በሕግ ፊት ቀርበው እንደሚቀጡ አስታወቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓብረት የውጭ ግንኙነትና ደኅንነት ጉዳዮች ምክር ቤት ሰኞ ሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ተወያይቶ የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ውይይቱም በትግራይ ክልል ያለው ሰብዓዊ ቀውስና አጠቃላይ ፖለቲካዊ ግጭቱ ሁሉን አቀፍ በሆነ ብሔራዊ ውይይት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያገኝ አሳስቧል።

በትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረስ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርና ቀውሱ እንዳይባባስ በማሳሰብ፣ ሁኔታዎቹ የማይሻሻሉ ከሆነ እስከ ማዕቀብ የመጣል ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...