Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ሽኝት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ሽኝት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት

ቀን:

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በብስክሌትና በዋና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በብሔራዊ ቤተ መንግሥት አሸኛኘት ተደረገለት፡፡ በአሸኛኘት ፕሮግራሙ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ቡድኑ መልካም ዕድል እንዲገጥመው በመመኘት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከአትሌቶቹ ለተወከሉት ሌሊሳ ዲሳሳና ሰንበሬ ተፈሪ አስረክበዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑም ኮቪድ-19 ታሳቢ ባደረገ መልኩ በወጣለት የውድድር መርሐ ግብር መሠረት ወደ ቶኪዮ እንደሚያመራ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የዞን አምስት አገሮች (አኖካ) ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በብስክሌት፣ በዋና እበእግር ኳስ ለመሳተፍ ቀደም ሲል ዕቅድ የነበረው ቢሆንም ከእግር ኳሱ በስተቀር በሌሎቹ ስፖርቶች ዕቅዱን ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በፕሬዚዳንቱ አገላለጽ የኢትዮጵያኦሊምፒክ ተሳትፎ ዕውን መሆኑ ከተረጋገጠበት ..አ. 1956 ጀምሮ የተለያዩ አደረጃጀቶችና መንግሥታትም ሲቀያየሩ የታዩ ሲሆን፣ በዚህ መሀል በአብዛኛው በራሳቸው ጥረት በሚባል ደረጃ ብዙ ጀግኖች አትሌቶች ተፈጥረው በተለያዩ የኦሊምፒክ መድረኮች ዓለምን ጉድ አሰኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ እንዲልና የኩራትና የአሸናፊነት ተምሳሌት በመሆን በትውልድ ቅብብሎሽ ወደር የሌለው ሚና ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡

የዚህ ሁሉ ድል ፈር ቀዳጅ የሆነው ሻምበል አበበ ቢቂላ በሮም በባዶ እግሩ በመሮጥ ካሸነፈበት ዕለት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች፣ ‹‹በተለያዩ የኦሊምፒክ መድረኮች ተዓምራዊ ውጤት ሲያስመዝግቡ ቆይተዋል›› ብለው ከስድስት አሠርታት በኋላ ቶኪዮ ላይ የታላቁን አትሌት ገድል ለመድገም ዝግጅታቸውን አጠናቀው ከሰሞኑም ወደ ሥፋራው ያመራሉ ብለዋል

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በማራቶን ስድስት አትሌቶች ሦስት ወንድና ሦስት ሴትበ20 ኪሎ ሜትር ዕርምጃ በአንድ ሴትአሥር ሺሕ ሜትር ስድስት አትሌቶች ሦስት ወንድና ሦስት ሴት፣ አስምት ሺሕ ሜትር ስድስት አትሌቶች ሦስት ወንድና ሦስት ሴት3,000 ሜትር መሰናክል ስድስት አትሌቶች ሦስት ወንድና ሦስት ሴት1,500 ሜትር ስድስት አትሌቶች ሦስት ወንድ እና ሦስት ሴት800 ሜትር በአራት አትሌቶች ሦስት ሴት እና በአንድ ወንድበወርልድ ቴኳንዶ በአንድ ወንድበሳይክል በአንድ ሴትበዋና በአንድ ወንድና በአንድ ሴት በድምሩ በ38 አትሌቶች የምትወከል ስለመሆኑ ጭምር ተናግረዋል፡፡

‹‹የኦሊምፒክ ጨዋታዎች መርሕና ኦሊምፒዚም መሠረታዊ ዓላማው ከወርቅና ሜዳሊያ በላይ ነው›› ያሉት ዶ/ር አሸብር፣ አገሮች አሸናፊነታቸውን የሚያረጋግጡት ገና እንደ አገር መሳተፍ ትችላላችሁ ተብሎ ተሳትፏቸው ሲረጋገጥ እንደሆነ አስረድተዋል

ኦሊምፒዝም የዓለም አገሮችንና ሕዝቦችን አሰባስቦ ስለ አንድነት፣ ስለ ሰላም፣ ስለ ሰው ልጆች ክብርና ትብብር በጎ ተግባራትና ግጭት አወጋገድ እንዲሁም መፍትሔዎችን የማሰብና የመጨነቅ ፍልስፍናም ተደርጎ ስለሚወሰድ የሽልማትና የሜዳሊያ ዋጋን በልኩና በገደቡ ማየት በሜዳሊያ ከምናገኘው ደስታ በላይ በዓላማውና ተግባሩ ሰዎች የበለጠ እንዲደሰቱ የሚያደርግ ስለመሆኑ ጭምር አስረድተዋል።

‹‹አትሌቶቹ የአበበ ቢቂላ የድል ከተማ የሆነችው ቶኪዮ ላይ የተሻለ ውጤትና ድል እንደሚያስመዘግቡ በጉጉት ይጠበቃል፤›› ያሉት ፕሬዚዳንቱ ‹‹ቶኪዮ ከዚህ በኋላ ኦሊምፒክን ለማዘጋጀት ምናልባት ምዕተ ዓመት ይፈጅባት ይሆናል፣ ስለዚህ እናንተ ደግሞ የማያቋርጥ የምዕት ዓመ የድልና የጀግንነት ታሪክ ባለቤት ለመሆን ራሳችሁን፣ አገራችሁን ዘወትር ልክ እንደ አበበ ቢቂላ የምትወደሱና የምትዘከሩ ልትሆኑ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

የቶኪዮ 2020 ዝግጅትአትሌቶችና አሠልጣኞች የልምምድ የድጋፍና የትኩረት ዕድል የፈጠረ፣ በአንፃሩ አትሌቶችም በአገር ውስጥ በተለይም በአዲስ አበባ ስታዲየምምና በዓለም ተይዘው የነበሩ ክብረ ወሰኖች መስበር ያስቻለ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅትና ከዚያም በፊት በተለያዩ ጉዳዮች በተለይም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር አለመግባባት ውስጥ መግባቱ ይታወሳል፡፡

‹‹በስፖርት ሥራ ላይ የተሰማራን አመራሮች ሥራዎቻችንን ተነጣጥቀን ሳይሆን፣ በኦሊምፒክ ቻርተሩና በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መተዳደርያ ደንብ የአገራችንን የስፖርት ፖሊሲ መሠረት በማድረግ በመደጋገፍ ለማሳካት መድከም እንዳለብን ማመን ይኖርናል፡፡ ይሁንና አንዳንዴ ከልምድ ማነስ አልያም ደግሞ ለቦታው አዲስ ከመሆናችን ጋር ተያይዘው የመጡት ሥራዎቻችን ባለን ኃላፊነት መሥራቱ ላይ ክፍተቶች ነበሩብን፤›› በማለት ያስታወሱት ዶ/ር አሸብር፣ እንደዚያም ሆኖ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች፣ ስፖርት ኮሚሽን፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ሌሎችም የበኩላቸውን ሚና ስለመጫወታቸው አልሸሸጉም፡፡

በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሸኩር፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣ ጥሪ የተደረገላቸው ለፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ተገኝተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...