Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበትግራይ ክልል ግጭት ሳቢያ በአዲስ አበባ የተያዙ ሰዎች አዋሽ አርባ መታሰራቸው ተጠቆመ

በትግራይ ክልል ግጭት ሳቢያ በአዲስ አበባ የተያዙ ሰዎች አዋሽ አርባ መታሰራቸው ተጠቆመ

ቀን:

በትግራይ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ሰዎች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችን ጨምሮ ወደ አዋሽ አርባ እስር ቤት መወሰዳቸው ተጠቆመ። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንግልትና እስር፣ የንግድ ቤት መዘጋት፣ ብሎም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸሙንና ሕይወት መጥፋቱን ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደርሱ እንግልቶች፣ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስር፣ የንግድ ቤት መዘጋትና መሰል መረጃዎችን እየተከታተለ እንደሚገኝ የሚገልጸው ኮሚሽኑ፣ የሚድያ ሠራተኞችን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች እየተወሰዱ ስለመሆናቸው ጥቆማዎች እንደደረሱት ገልጿል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሪፖርተር ከኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ባገኘው መረጃ መሠረት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች የሕግ አግባብን ባልተከተለ መንገድ በተራዘመ እስር ላይ ናቸው። 

ኮሚሽኑ ታሳሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅና ለመጎብኘት የሚመለከታቸውን የመንግሥት ኃላፊዎች ቢጠይቅም፣ እስከ ዓርብ ሐምሌ 9 ቀን ድረስ ፈቃድ ማግኘት አለመቻሉን ማወቅ ተችሏል። 

ከአዲስ አበባ ተይዘው የታሰሩት ሰዎች ወደ አዋሽ አርባ መወሰዳቸውን ለኮሚሽኑ መረጃዎች እንደደረሱትም የኮሚሽኑ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል። 

ኮሚሽኑ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ በትግራይ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንግልትና እስር፣ የንግድ ቤት መዘጋት፣ ብሎም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መከሰቱንና ሕይወት መጥፋቱን፣ እንዲሁም በታሳሪዎችና በምርኮኞች ላይ የሚደርስ ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ በስደተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ሕፃናትን ለውትድርና መጠቀም የሚያመላክቱ መረጃዎች እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ ብሔርን መሠረት ባደረገ ጥቃት ሦስት የትግራይ ተወላጆች መገደላቸውንም አስታውቋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ሐምሌ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. መሆኑን የሚገልጸው ኮሚሽኑ፣ ጥቃቱ ከተፈጸመ አንድ ቀን አስቀድሞ ፍየል ውኃ በሚባል ቦታ ‹‹የሕወሓት/ትግራይ መከላከያ ኃይሎች›› በወሰዱት የጥቃት ዕርምጃ፣ የፎገራ ወረዳ ነዋሪዎች የሆኑ የሚሊሺያ ቡድን አባላትና የወረዳው የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ስለመገደላቸው መረጃ እንደ ደረሰው አስታውቋል።

የፀጥታ ኃላፊዎቹ መገደላቸው መሰማቱን ተከትሎ ሐምሌ 4 ቀን 2013 .. ረፋዱ ላይ ከተገደሉት የወረዳው የሰላምና ፀጥታ ኃላፊ ትውልድ ቦታ ማለትም ጉመራ ወንዝ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ የሟቾቹን አስከሬን ለመቀበል የመጡ ነዋሪዎች፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃቱን ስለማድረሳቸው መስማቱን ገልጿል።

በዚህ ጥቃትም የፎገራ ነዋሪዎች የሆኑ ሦስት የትግራይ ተወላጆች በድንገት በተሰባሰቡ ነዋሪዎች በደረሰባቸው ድብደባ ስለመገደላቸው ለኮሚሽኑ ጥቆማዎች እንደ ደረሱት አስታውቋል። 

የፎገራ ወረዳና የአካባቢው የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊዎች በወሰዱት አፋጣኝ ዕርምጃ ሁኔታው የተረጋጋና ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ቢሆንም፣ የተከሰተው ሁኔታ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እንዳይዛመት የሚያሠጋ እንደሆነ ገልጿል። 

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹ከሰኔ 22 ቀን 2013 .. ጀምሮ ተባብሶ የታየው ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ ክስተትና እስር ሁኔታ ተገቢውን ትኩረትና መፍትሔ ካለማግኘቱ በተጨማሪ፣ በስፋት የሚደመጡ የጥላቻና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ሁኔታውን ሊያባብሱና ብሎም በማኅበረሰቦች መካከል ያለውን ትስስር ሊያላሉ የሚችሉ ናቸው። ስለሆነም በየትኛውም አካባቢ ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ ነዋሪዎች በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁ፣ የፌዴራል መንግሥትም ሆነ የክልል መስተዳድሮች በእነዚህ ነዋሪዎች ላይ እንግልት ያደረሱና ሌሎች ሕገወጥ ድርጊቶች የፈጸሙ የሕግ አስከባሪ አካላትን ሕግ ፊት ሊያቀርቡ ይገባል፤›› ብሏል።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል በሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ላይ፣ ‹‹የሕወሓት/ትግራይ መከላከያ ኃይሎች›› ተቃዋሚ ናቸው የተባሉ ሲቪል ሰዎች ላይ የግድያና የአፈና ዕርምጃዎች እየተወሰደ ስለመሆኑ መስማቱንና ይህም እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ አስታወቋል።

በአላማጣና አካባቢው በድጋሚ ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ በመኾኒ አካባቢ የበቀል ዕርምጃዎች እየተወሰዱ ስለመሆናቸው መስማቱን የገለጸው ኮሚሽኑ፣ በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል። 

የቴሌኮምናማኅበራዊ አገልግሎቶች መቋረጣቸው የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ሥራውን አዳጋች ያደረገው ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ያለውን የተደራሽነት ሁኔታ በተመለከተ የሚያደርገውን ክትትል የሚቀጥልና በቆቦ፣ በወልዲያና በመርሳ ተጠልለው የሚገኙ ከአላማጣናአካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎችን የሚጎበኝ መሆኑን ገልጿል። 

ኢሰመኮ የግጭቱ መባባስና የግጭቱ ተፅዕኖ በአፋርና በአማራ ክልል የሚገኙ ቦታዎችን ጨምሮ ወደ ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ጭምር መስፋፋቱንና ሁኔታዎቹ እጅግ የሚያሳስበው እንደሆነም አስታውቋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለ (/) በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹መንግሥት በተለይም ይህን በመሰለ ፈታኝ የውጥረት ወቅት ለሲቪል ሰዎችና ተጋላጭ ለሆነው ማኅበረሰብ ክፍል ከፍተኛ ጥበቃ የማድረግ ተጨማሪ ኃላፊነት የሚጣልበት ነው። መሠረታዊ የሆኑ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችና የሰብዓዊ መብቶች መርሆች በግጭት ወቅት ጭምር ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የሚያዙና ሲቪል ሰዎችና የሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ፣ ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ላይ ከፍ ያለ ግዴታ የሚጥሉ ናቸው፤›› ብለዋል።

በማከልም፣ ‹‹ከትግራይ ክልል ጋር ተያይዞ በቀጠለው ግጭት የሚሳተፉ ወገኖች በሙሉ፣ እንዲሁም የሚዲያ ተቋማትን ጨምሮ አገራዊና ዓለም አቀፍ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሙሉ ማንኛውንም የማኅበረሰብ ክፍል አደጋ ላይ ከሚጥል ንግግር፣ መግለጫዎችና ተግባራት እንዲቆጠቡ ኮሚሽኑ ጥሪ ያቀርባል፤›› ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...