Monday, March 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኅብረት ባንክ የፋይናንስ ደኅንነት ሥርዓት በመዘርጋት ዕውቅና አገኘ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኅብረት ባንክ በኦንላየን ባንኪንግ፣ በዳታ ሴንተርና በዲዛስተር ሪከቨሪ ፋሲሊቲ የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ማኔጅመንት ሲስተም የISO/IEC 27001፡2013 መሥፈርትን በማሟላት ለዘረጋው የደኅንነት ሥርዓት የዕውቅና ሰርተፍኬት ማግኘቱን ገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች ISO/IEC 27001፡2013 ሰርተፍኬት በማግኘት ቀዳሚ ባንክ እንዳደረገው፣ የባንኩ የኢንፎሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት  ዳይሬክተር ኡስማን ሰዒድ ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ISO/IEC 27001፡2013 ሰርቲፋይድ መሆኑን አስመልክቶ ሐሙስ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ሰርቲፋይድ መሆኑ ደንበኞች አስተማማኝ  የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውንና የፋይናንስና ሌሎች የባንኩ መረጃዎች ደኅንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡ አቶ ኡስማን እንዳሉት ደንበኞች ደኅንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ አመኔታ የሚሰጣቸውም ነው፡፡ የሳይበር ጥቃትን በመከላከሉ ረገድ የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳለውም አክለዋል፡፡

ባንኩ ይህንን ሰርተፍኬት ያገኘው ዓለም አቀፉ PECB MS ISO/IEC 270012013 መሥፈርቶች መሠረት የባንኩን የኢንፎርሜሽን ሴኩሪቲ ሲስተም በመመርመርና ብቁ መሆኑን በማረጋገጥ ነውም ተብሏል፡፡

በተለይ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የሳይበር ጥቃቶች አንፃር ባንኩ ISO/IEC 270012013 ሰርቲፋይድ መሆኑ አገልግሎቱን የበለጠ እንደሚያደርግለትም ተጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች