Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ልናገር​​​​​​​ቱሪዝም በኢኮኖሚው ያለው ቦታ ሲውገረገር

​​​​​​​ቱሪዝም በኢኮኖሚው ያለው ቦታ ሲውገረገር

ቀን:

መስፍን ብቱ

ባለፉት ሁለት ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለቱሪዝም በሰፊው አውግተውናል፡፡ በአዲስ አበባና በሌሎችም አካባቢዎች የተቋቋሙት ፓርኮች ቱሪስቶችን ምን ያህል እንደሚስቡልን በዚህም አገሪቱ ገቢዋ ከፍ እንደሚል ብዙ ጊዜ ነግረውናል። እንዲያውም ራሳቸው በእንጦጦ ፓርክና በሌሎችም ቦታዎች እየተገኙ በቴሌዥን የተላለፈ መግለጫ ሰጥተዋል። ይኼ ሁሉ መግለጫ የተሰጠበትና እንደ አንድ ገቢ ምንጭ ተስፋ የተጣለበት “የቱሪስት መሳቢያ” ሮጀክት በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ ስንት ቱሪስት ሳበልን? ስንትስ አገኘን? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳት ተገቢ ይሆናል። የዚህ ጽፍ ዓላማ የታለመውን ገቢ ስላላገኘን ፕሮክቶቹን ለመንቀፍ ሳይሆን፣ ስለቱሪዝም ያለውን የተሳሳተ ቅኝት እንዲስተካከል ለማድረግ ነው።

በመረቱ ቱሪዝምን የገቢ ምንጭ አድርገን ለማየት ስንነሳ በአንድ በኩል በቱሪዝም ከፍተኛ ገቢ ያገኙ አገሮችን ተመክሮ መቃኘት በሌላ በኩል ከቱሪዝም ጋር አብሮ የሚመጣውን ባህላዊ መበከል ለመቆጣጠር ምን ምን ማድረግ እንደሚስያስፈልግም እያሰብን መሆን አለበት። ከመነሻው ቱሪዝም ውጫዊና ውስጣዊ ነው፡፡ ማለትም የውጭ አገር ቱሪስቶችንና የአገራችን ቱሪስቶችን ይመለከታል። በቻይናና በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከውጭ አገር ከሚመጣው ቱሪስት በቁጥር እዚያው አገር ውስጥ ያለው የአገሬው ቱሪስት ይበልጣል። የሚገኘውም ገቢ ተመጣጣኝ ነው። ይሁን እንጂ የአገር ውስጥ ቱሪስት እንዲኖር የዚያ አገር ኢኮኖሚ የዳበረ ለዚህም የነፍስ ወከፍ ገቢውም ከፍተኛ ሊሆን ይገባዋል። አለዚያማ አፋሩ እንዴት ብሎ ነው ጎንደር ቱሪስት ሆኖ የሚሄደው? ቦረናውስ እንዴት ብሎ አክሱምን ለመጎብኘት ቱሪስት ሆኖ ይነሳል?

በውጭ አገር ቱሪስቶች ላይ ብናተኩር ሁለት ዓይነት ቱሪስቶች አሉ። አንደኛው በታሪክ ላይ ከፍተኛ ፍቅር ያለው ስለዚህም ታሪካዊ ቦታዎችን ለማየት የሚፈልገው ቱሪስት ነው። በዚህኛው ክፍል በአብላጫው የታሪክ፣ የአንትሮፖሎጂ፣ አርኪዮሎጂና መሰል ትምህርት የተማሩ ምሁራን ሲገኙበት ሌሎችም የጥንት ታሪክ አድናቂዎችም ይገኙበታል። ይኛው ክፍል ከጠቅላላው የቱሪስት ቁጥር እጅግ አነስተኛ እንደ መሆኑ መጠን ከዚህ ክፍል የሚገኘው ገቢም እጅግ አነስተኛ ነው። በርግጥ እጅግ የታወቁና ከፍተኛ ማስታወቂያ የተደረገላቸው እንደ ታጅ ማሃል (ንድ) ግሬት ዎልና (ቻይና)፣ ማቹ ፑቺ (ፔሩ) የመሳሰሉት በአገር ውስጥም በውጭ አገር ቱሪስቶችም የመጎብኘት ድል አላቸው። ነገር ግን በዓለም ያሉ ታሪካዊ ቦታዎች ሁሉ እንደ ታጅ ማሃል፣ ግሬት ዎልና ማቹ ፑቺ በገፍ ይጎበኛሉ ማለት አይደለም።

ሁለተኛው የቱሪዝም ፈርጅ ማስ ቱሪዝም ሊባል የሚችለው ነው። በቁጥሩም ገቢ በማስገኘትም ከፍተኛ ሚና አለው። ማስ ቱሪዝም እንደ ስሙ ተራውን የውጭ አገር ሰው በተለይም ፈረንጁን፣ ቻይናውንና ጃፓ ቱሪስቶችን ይመለከታል። በዚህ ፈርጅ ቱሪስት ሆኖ የሚመጣው ተራው ራተኛ ፈረንጅ ሲሆን በዓመት አራ አንድ ወሩን ደሙን ተፍቶ ላቡን አንጠፍጥፎ ርቶ የአንድ ወር የረፍት ጊዜውን በመጠቀም ሌላ አገር ሄዶ ለመዝናናት፣ ጥሩ ጥሩ ምግብ ለመብላት፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አገሩ በማያገኘው ፀሐይ ላይ እየተሰጣ ዋናውን እየዋኘ፣ ቀዝቃዛ ቢራውን/መጠጡን እየጠጣ የሚዝናና ነው። እንዲህ ያለውን ቱሪስት በማጥመድ የተካኑ አገሮች አሉ፡፡ ታይላንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኬኒያ፣ ቱኒዚያ፣ ግብ፣ ጋምቢያ፣ታንዛኒያ፣ የካሪቢያን ደሴቶችታሂቲ፣ ሃዋይና ሌሎችም ይገኙበታል። ከነዚህ አገሮች አብኞቹ ደግሞ ይኼ ለአንድ ወር ለማበድ ተዘጋጅቶ ለሚመጣ ፈረንጅ በተጓዳኝ ሽርጥናውን ከፍተውለታል፡፡ የጋምቢያው ሴሬኩንዳ፣ የኬያው ሞምባሳ፣ የኢንዶኔዢያው ባሊ፣ እንዲሁም ያታይላንዱ ፓታያና የካሪቢያን ደሴቶች በዚህ የታወቁ ናቸው። እነዚህ አገሮች ከእንዲህ ያለ ቱሪዝም የሚያገኙት ገቢ እጅግ ከፍተኛ ነው። የቱሪዝም ሽርሙጥናው ሆን ብሎ በቁጥጥር ምክንያት ባልተፋፋባቸው እንደ ግብና ቱኒዚያ ያሉት ከቱሪዝም የሚያገኙት ገቢ ጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ለምሳሌ በቱኒዚያ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከጠቅላላው የውጭ ምንዛሪ (Foreign Exchange Earnings) እስከ 60 በመቶ ያገኙ ነበር።

እንግዲህ እኛም ቱሪዝምን አስፋፍተን ገቢ እናሳድጋለን ካልን በሁለተኛው ፈርጅ ስላለው ቱሪም እንጂ የታሪክ ፍቅር ያላቸውን ወይም የአገር ውበትን አድናቂዎችን ማለታችን እንዳልሆነ ከአሁኑ ግልጽ መሆን ያስፈልጋል። ገቢ የሚያስገኘው ማስ ቱሪዝም እንደ መሆኑ መጠን ይኼኛው የቱሪዝም ዘርፍ የሚያስፈልገውን መዋቅር ማዘጋጀት ያስፈልጋል ማለት ነው። እንዳልነው ፈረንጁ ፀሐይ፣ ጥሩ ምግብ፣ መጠጥ፣ መዋኛ ቦታዎች ነው የሚፈልገው። ሽርሙጥናውን ለሌሎቹ ትተን በአንድ በኩል ፈረንጁ ቱሪስት የሚዝናናበትን መዋቅርና ግልጋሎቶች ማዘጋጀት፣ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ግብና ቱኒዚያ ቱሪዝም ሽርሙጥናን እንዳይጨምር አድርገን ማዘጋጀት እንችላለን። ለቱሪስቱ የጥታ ዋስትና ዋነኛው ጉዳይ ነው። ሊዝናና የመጣ እንጂ በቱኒዚያና በግብ በአንድ ወቅት አሸባሪዎች እንዳደረጉት ሊታረድ የመጣ ስላልሆነ የጥታ ዋስትና ቁልፍ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የጥታ አካላት ራዬ ብለው በየትኛውም ቦታ ቱሪስቶች የጥታ ጋት እንዳይኖራቸው ማድረግ ይኖርባቸዋል። ይህ ራሱ በጥታ አስከባሪው አካል ዘንድ ቱሪዝምን በሚመለከት ራሱን የቻለ ግዴታ አለበት ማለት ነው።

መዋቅር ስንል መንግት በራሱ የሚቆጣጠራቸውን ብቻ ማለት አይደለም። የግል ሴክተሩንም ይመለከታል። ለምሳሌ ሆቴሎች ለዚህ በቅጡና በብቃት መዘጋጀት አለባቸው። ሆቴሎች ለዚህ ራ እንዲበቁ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዝርዝር መመያ ለሆቴሎች ማውጣትና ሆቴሎችም ለዚህ እንዲበቁ ማድረግ ይኖርበታል። ለምሳሌ ሪሴፕሽን ውስጥ የሚሩና አስተናጋጆች (ዌይተሮች) በቀጥታ ከቱሪስቱ ጋር የሚገናኙ እንደ መሆናቸው በቂ ልጠናና የቋንቋ ችሎታ ያስፈልጋቸዋል። ማጭበርበር ወይም ከዋጋው በላይ ማስከፈል እንዳይኖር ማድረግ የሆቴሎች ላፊነት ነው። ግና የቱሪዝም መስተንግዶ ቱን የሚጥሱ ወይም የማያስከብሩ ሆቴሎች ወይም ሌሎች አገልግሎቶች መቀጣት አለባቸው። የቱሪዝም ራ በጣም ስሱ (ሴንቲቭ) ነው። አንድ ቱሪስት “እዚህ አገርማ እንዲህ አርገው አጭበርብረውኛል” ብሎ ካወራ ይኼን የሰማ ቱሪስት ተባለበት አገር/ከተማ ዝር አይልም።

ዓላማውን ገቢ ማስገኛ ያደረገ ማስ ቱሪዝም ዋና ዋና ገጽታው ይ ሲሆን ለዚህም አንድ አገር ምን ያህል ዝግጅት በፖሊሲና መዋቅር ደረጃ ማድረግ እንዳለበት አሳይተናል። አሁን ባለንበት ሁኔታ ማስ ቱሪዝምን ለመሳብ አገራችን ያላት ዝግጁነት ምን ያህል ነው ብለን ብንጠይቅ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ስለዚህ ከጅማሮው ገና ብዙ መራት እንዳለብን የታወቀ ነው። ፖሊሲውም፣ መዋቅሩም ዝግጁነቱም የለንም። እንግዲህ ማስ ቱሪዝምን ለማስፋፋት ከፈለግን መጀመያ ቱሪስቶች ሊዝናኑባቸው የሚችሉ የባህር ዳርቻዎች (ቾች) አሉን ወይ ብንል የለንም ነው። አገራችን የባህር ዳርቻ ስለሌላት ባሉን ይቆች ዳርቻዎች ማዘጋጀት ንችልም ወይ ቢባል ይቻላል ነው መልሱ። አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ይቆች ላይ ዳርቻዎች አዘጋጅተው ቱሪስቶችን የሳቡ አሉ (Black Sea)። እኛም ይኼን ማድረግ እንችላለን። በነዚህ ይቆች ደረጃውን የጠበቁ ሆቴሎች፣ ግልጋሎቶች (ኢንተርኔት ጭምር)፣ መዝናኛዎች እንዲኖሩ ማድረግን ይጠይቃል። በአሁኑ ጊዜ ይኼ ሁሉ እንደሌለን የታወቀ ነው። ስለዚህ የቱሪዝም ኢንስትሪውን ለመጀመርና ለማሳደግ ራዬ ብሎ መራትን ይጠይቃል። እንደ ኬያና ታንዛኒያ ከቱሪዝም ገቢ ለማግኘት ማስ ቱሪዝምን ላማ ማድረግን ጠይቃል። እነዚህን አገሮች በዓመት ቢያንስ እስከ ሁለት ሚሊዮን ቱሪስት ይጎበኛቸዋል።

አሁን በቅርብ የተሩት የአገራችን ፓርኮች ማንን ይማርካሉ ቢባል ከአውሮፓ፣ ከቻይና ወይም ከጃፓን ሊመጣ የሚችለውን ቱሪስት ሳይሆን ደህና ገቢ ያለውን የአገራችንን የከተማ ነዋሪ እንደሆነ የታወቀ ነው። አንድ ሊትር ዘይት ከ500 ብር በላይ በሆነበትና ሰ በኑሮ ውድነት በሚያማርርበት አገር አንድነት ፓርክን ለመጎብኘት 200 ብር መክፈል የሚችለው ማነው? ስንቱ? ስለዚህም አሁን ባለው ሁኔታ የፈረንጁን ቱሪስት እንደ ገቢ ምንጭ አድርገን ማየት እንችላለን? አንችልም። ስለዚህ ፓርኮቹ በቂ ገቢ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን እንጂ የፈረንጅ ቱሪስትን አይስቡልንም። ታሪካዊ ቦታዎችንና እንደ ሊማሊሞና ሰሜን ተራሮች የመሳሰሉ አስደናቂ የተፈጥሮ ቦታዎችን ሊመለከት የሚመጣው ፈረንጅ ምሁር ምሁሩ ስለሆነ ቁጥሩ እጅግ አነስተኛ ነው። ስለዚህ ገቢ ሊያስገኝ የሚችል ማስ ቱሪዝም ለመሳብ ጥሩ ስትራቴጂ ማውጣትን ይጠይቃል። ጥሩ ስትራቴጂ ለማውጣት ከላይ የተጠቀሱት አገሮችን መጎብኘትና ማስ ቱሪዝምን እንዴት እንዳዘጋጁት ከተክሯቸው መማርን ይጠይቃል።

ለመሆኑ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ምን ያህል ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ የኮኖሚ ዘርፍ ነው? ከላይ እንዳየነው የቱሪዝም ኢንስትሪ ሰፊ ዝግጅት ብሎም ካፒታል የሚጠይቅ ነው። እንደ ኬያና ታንዛኒያ የውቅያኖስ ዳርቻ ስለሌለን ዳርቻውን እኛው ራሳችን ከይቆቻችን የምንገነባው ስለሆነ ካፒታል ይጠይቃል። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ምን ያህል ቅድሚያ የሚሰጠው (Priority) ይሆናል ስንል ብዙም ባይሆን ካፒታልን የሚጠይቁ ሌሎች አንገብጋቢ የኮኖሚ ክፍሎች እንዳሉ ማየት አለብን። ከኢትዮጵያ ዝብ ወደ 85 ከመቶ የሚሆነው ገጠሬ ወይ አርሶ አደር ወይ አርብቶ አደር ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ለኢንስትሪ የሚሆን ካፒታል ማከማቸት የሚቻለው በእጃችን ላይ ካለው ብት ሲሆን ይኸውም የአርሶ አደሩ የእህል ምርትና የአርብቶ አደሩ እን ርባታ (ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ብዛት ከአፍሪካ አንደኛ ናት) ናቸው። የገጠሩ ልማት ቅድሚያ የሚሰጠው በአንድ በኩል የካፒታል ክምችት ሊያመጣ የሚችል ሴክተር ስለሆነ ሲሆን በሌላ በኩል ግን ከፍተኛ ድህነት ያለበት በመሆኑ ድህነትም መጥፋት ስላለበት ነው፡፡ ስተኛው ደግሞ በአገሪቱ ልማት የሚመጣ ከሆነ ብረሰቡም ግለሰቡም ትራንስፎርም ማድረግ ስለሚኖርበት ከፍተኛው የትራንስፎርሜሽን ራ የሚካሄደው በገጠር ስለሆነ ነው። ለገጠሩ ልማት የተሰጠውን ትኩረት ብናይ አርሶ አደሩ ላይ ብቻ እንደሆነ እናስተውላለን። በዚህ ረገድ ብዙ እንደተራ እንሰማለን እሰየው የሚያሰኝ ነው።

ይሁን እንጂ በአርብቶ አደሩም እጅ ከፍተኛ ብት ያለ ስለሆነ ይኼም ዘርፍ ትኩረት ይሻል። ሁለተኛ የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ችግራችን የገበያ መዋቅር ማጣት ስለሆነ ገበያ ይከፈትልን እያሉ ገና ከንጉ ዘመን ጀምረው ሲጮሁ የነበሩት እስከ ዛሬ አልተከፈተላቸውም(አርብቶ አደሩ ከብቱን ለመሸጥ ድንበር እያቋረጠ ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያና ሱዳን እንደሚጓዝ የታወቀ ነው)። መንግት እዚህ ላይ ትኩረት አድርጎ ገበያ ቢከፍትላቸው በአንድ በኩል አርብቶ አደሩ ኑሮውን እያሻሻለ ልጆቹንም እያስተማረ በአገሩም ላይ ያለው እምነት እየጨመረ ስለሚሄድ አያሌ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በሌላ በኩልም መንግት ወይም ባለብቱ በወተትና ተዋጽኦ ኢንስትሪ ወስጥ እየገባ አገልግሎት ሊሰጥ ስለሚችል ለአገሪቱ ኮኖሚ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በዚህ ስትራቴጂ እጅግ ብዙ አርብቶ አደሩ ዝብ ከድህነት ሊወጣ ይችላል፡፡ ለኢንስትሪም መስፋፋት (በወተት ተዋጽኦ ላይ ያተኮረ) እንዲሁ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ከዚህ አንር ካየነው የገጠሩ ልማት ምን ያህል ቅድያ ሊሰጠው እንደሚገባ ግልጽ ነው።

ቅድሚያ መስጠትና አለመስጠት ከጀት ምንጭ ጋር መያያዝ የለበትም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት ፓርኮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው አይገባም የሚለውን ሲተቹ ጀቱን የሰጠኝ ፓርላማው ስላልሆነ እኔ በራሴ ጥረት ያገኘሁት ገንዘብ በመሆኑ ልጠየቅ አይገባም ብለው ነበር። ጉዳይ እኮ “ቅድሚያ ለማነው?” የሚለው ነው። ለአርብቶ አደሩ ልማት ቅድሚያ ቢሰጡና ፓርላማውም ጀት ባያድቅልዎት አርብቶ አደሩን ሊረዱ ጀት ፍለጋ ይሄዳሉ ማለት አይደለም። ዋናው ጉዳይ በቅድሚያ ስትራቴጂው ላይ አንድ ልብ መሆኑ ላይ ነው። በርግጥ አንድ የሆነ ፋውንዴሽን አቋመው ጀቱ በፋውንዴሽኑ ራ ላይ ቢውል ፓርላማው የሚያገባው አይደለም። እንደ መንግት ፕሮክት ሲሆን ግን ይለያያል። ንኛውም የመንግት ተግባር (ጀቱ በግል ጥረት ተገኘ አልተገኘ) ተጠያቂነቱ ለፓርላማ ስለሆነ።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...