የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ የሽብርና ሕገመንግስታዊ ጉዳዮ ችሎት፣ የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ ደሞዝና ወ/ሮ አስካል ደምሌ ላይ የቆጠራቸውን ምስክሮች ከሐምሌ 14 እስከ 16 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲያሰማ ቀጠሮ ሰጠቶ የነበረ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ በማቅረቡ ታገደ፡፡
ፍርድ ቤቱ የዓቃቤ ሕግን ምስክሮች መስማት ለመጀመር ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የተሰየመ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግ የእግድ ትዕዛዝ ይዞ በመቅረቡ ሳይሰማ ቀርቷል፡፡
ዓቃቤ ሕግ የስር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ያሳገደው፣የስር ፍርድ ቤት የምስክሮችን ቃል የሚሰማ ከሆነ፣ ሊታረም የማይችልና ፍትሕን ሊያዛባ የሚችል ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁሞ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታገድለት ጠይቆ ነው፡፡
ስበር ሰሚ ችሎቱ የዓቃቤ ሕግን ማመልከቻ ከተመለከተ በኋላ በሰጠው ተዕዛዝ እንደገለጸው፣የስር ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲሰሙ የወሰነበት አግባብነት፣ የወንጀል ምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃአዋጅ ቁጥር 699/2003 አንቀጽ 3 ፣4(1 ቀ፣በ)፣ አንቀጽ 15(1 እና 3)፣ አንቀጽ 7፣8፣ 23(1 እን 2) ዓላማና ዐዋጁን ለማስፈጸም የስር ፍርድ ቤት ካለው ሚናና ሌሎች ተዛመጅ ነጥቦች አንፃር መጣራት አለበት፡፡ በመሆኑም እንደሚያስቀርብ በመግለጽ፣ ተለዋጭ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ መዝገቡ መታገዱን ሦስት ዳኞች ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -