Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራ ክልል መንግሥት የቀድሞ መከላከያ ሠራዊት መኮንንን የልዩ ኃይል አዛዥ አድርጎ ሾመ

የአማራ ክልል መንግሥት የቀድሞ መከላከያ ሠራዊት መኮንንን የልዩ ኃይል አዛዥ አድርጎ ሾመ

ቀን:

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት አስተዳደር የቀድሞ የመከላከያ  ሠራዊት መኮንን የነብሩትን ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞን የክልሉ ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ አድርጎ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ሾመ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሸገር ተጨማሪ ሹመቶችን የሰጡ ሲሆን፣. ጀነራል መሰለ በለጠን የኦፕሬሽናል ዘርፍ ምክትል አዛዥ፣ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል አዛዥ ፣ኮሚሽነር አርአያ ካሴ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል አዛዥ ፣ጀኔራል ማሞ ግርማይ የሎጀስቲክስ ዘርፍ ምክትል አዛዥ ፣ጀኔራል ዘዉዱ እሸቴ  የሎጀስቲክስ ዘርፍ ምክትል አዛዥ፤ጀኔራል አበራ ተ/ዮሃንስ የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል አዛዥ ፣ረዳት ኮሚሽነር መለሰ ደገፋዉ የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል አዛዥና  ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴን የሰላምና ደህንነት ቢሮ  ሃላፊ ልዩ ረዳት ሆነው ተሾመዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ ሌሎች ተጨማሪ ሹመቶችና ምደባዎችን መስጠታቸው ታውቋል፡፡
ብርጋዴር ጀነረሰለረ ተፈራ ማሞ ኢሕአዴግ አገሪቱን በሚመራበት ወቅት በተሰለፉበት ሰራዊቱን በመምራትም ሆነ በግንባር ተሰልፈው ባደረጓቸው ውጊያዎች “ጀግና” መባላቸውንና በተለይም በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ባሳዩት ጀግንነት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ መሸለማቸው ተነግሯል፡፡ የእትዮ-ኤርትራ ጦርነት እንደተጠናቀቀ ገድል ለሰሩ ወታደራዊ መኮንኖች ሽልማት ሲሰጥ ለብርጋዴር ጀነራል ተፍራም 500 ካሬ ሜትር የቤት መገንቢያ መሬት አዲስ አበባ ውስጥ ተሰጥቷቸዋል፡፡ 
ብርጋዴር ጀነራሉ ጦርነቱ ካበቃ ከጥቂት ጊዜ በኃላ ከሟቹ ከእነ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌ ጋር በመሆን መፈንቅለ መንግሰት ለማድረግ ሲያሴሩ ተገኝተዋል ተብለው በተመሰረተባቸው ክስ ዕድሜ ልክ እስር ተፈረዶባው ነበር፡፡ ዓብይ አህመድ(ዶ/ር) ውደቸስልጣን በመጡ መግስት ከእስር ተፈትተው በአማራ ክልል በጸጥታው ዘርፍ የተሾሙ ቢሆንም፣ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም ርዕሰ መስተዳድሩን አምባቸው መኮንን(ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከመገደላቸው ጋር ተያይዞ የታሰሩ ቢሆንም ከወንጀል ድረጊቱ ነፃ መሆናቸው በመረጋገጡ የምርመራ መዝገባቸው ተዘግቶ በነፃ መሰናበታቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...