Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የደረሰው የውኃ ዋና ስፖርት ውዝግብ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የደረሰው የውኃ ዋና ስፖርት ውዝግብ

ቀን:

የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርት ፈዴሬሽን በኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ከሚወክሉ የስፖርት ዓይነቶች አንዱ ነው፡፡ ‹‹በቶኪዮ እ.ኤ.አ. 2020 ኢትዮጵያን ማን ይወክላል?›› የሚለው ለበርካቶች ጥያቄ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ውኃ ዋና ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እሰጣ አገባ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ ፌዴሬሽኑ የዓለም አቀፍ ሕግና መመርያ ተከትሎ ሲሠራ መቆየቱንና ኦሊምፒክ ኮሚቴ ያለ አግባብ ጣልቃ ገብቶብኛል ያለበትን ጉዳይ ዕረቡ ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኢትዮጵያ ተሳትፎ (Universality) እንዲኖራት በሚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ በውኃ ዋና ለአንድ ሴትና ለአንድ ወንድ ዕድል መስጠቱን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያን በውኃ ዋና የሚወክሉ ስፖርተኞች ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ የውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን እ.ኤ.አ. 2019 በዓለም ሻምፒዮና ላይ ተካፋይ ከሆኑ ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ዋናተኞች መካከል፣ ጥሩ ሰዓት ያላቸውን ሁለት ስፖርተኞች መርጦ በጊዮን ሆቴል ከሦስት ወራት በላይ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በውኃ ስፖርት ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መካከል አለመግባባቶች መፈጠራቸውን ተከትሎ፣ ዓለም አቀፉ ዋና ፌዴሬሽን ጣልቃ በመግባት፣ ራሔል ፍሰሐ ገብረ ሥላሴና አብዱር መሊክ ቶፊክ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የተመረጡ ስፖርተኞች መሆናቸውን ፌዴሬሽኑ በጋዜጣዊ መግለጫው አስታውቋል፡፡

    የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ዓቃቤ ነዋይና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ  ዳግም ዝናቡ በፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴና ሥራ አስፈጻሚ በጋራ ሆነው የመረጧቸውን የውኃ ዋና ስፖርተኛና አሠልጣኝ ማፅደቁን አስታውሶ፣ በውሳኔ ግን በኦሊምፒክ ኮሚቴ ጣልቃ ገብነት ዋናተኛን ከኦሊምፒክ እንዳስቀረ ያስረዳል፡፡

በዓለም ሻምፒዮና ባመጣችው ጥሩ ሰዓት ከዓለም አቀፉ ውኃ ፌዴሬሽን ተቀባይነት አግኝታ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን ለመወከል ዝግጅት ስታደርግ የነበረችው ራሔል፣ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንድትቀር መደረጉን ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ዓቃቤ ነዋይና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዳግም በጋዜጣዊ መግለጫው አስረድተዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በኦሊምፒክ ኮሚቴው ተቀባይነት ያጣችው ስፖርተኛዋ፣ በሌላ ውኃ ዋና ስፖርተኛ መተካቷንና የተተካችው ዋናተኛ በኦሊምፒክ ጨዋታው ላይ ተቀባይነት ያለት ባለመሆኑ፣ ኢትዮጵያ በሴት ያገኘችው ዕድል እንደተነጠቀችም ገልጽዋል፡፡

እንደ ዓቃቤ ነዋዩ ዳግም አስተያየት ከሆነ፣ ውኃ ዋና ፌዴሬሽን ሚያዝያ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. የአራት ስፖርተኞች፣ ሦስት አሠልጣኞች፣ ቡድን መሪና የቴክኒክ ባለሙያ ስም ዝርዝርን ለኦሊምፒክ ኮሚቴና ለዓለም አቀፉ ውኃ ዋና ፌዴሬሽን ማሳወቁን ገልጾ፣ በአንፃሩ በኦሊምፒክ ኮሚቴ ጆሮ ዳባ ልበስ መባሉን አቶ ዳግም ጠቅሰዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ውኃ ዋና ፌዴሬሽን ራሔልና አብዱር መሊክ ስፖርተኞች  ባላቸው ውጤት መሠረት ኢትዮጵያን መወከል እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ልኮ ቢያሳውቅም፣ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ራሔልን በሊና ሴሎ እንድትተካ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

መግባባቶች ሳይፈቱ ቆይተው ኦሊምፒክ ኮሚቴም ሆነ ውኃ ዋና ፌዴሬሽን የሚንቀሳቀሱት በግል ሆኗል፡፡ ሦስቱም ስፖርተኞች የተለያዩ አሠልጣኞች ተመድቦላቸው፣ በጊዮን ሆቴል ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፈላጭ ቆራጭነት ብቻ፣ በአግባቡ የተመረጠችው ልጅ እያለች በዓለም አቀፉ ውኃ ዋና ስፖርት ፌዴሬሽን ዕውቅና የሌላትን ዋናተኛ ይዞ በመጓዙ ምክንያት ኢትዮጵያ በሴት መሳተፍ ዕድሏን አጥታለች፡፡›› በማለት ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንቱን ተጠያቂ አድርጓዋል፡፡

ውኃ ዋና ስፖርቶች ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ተሾመ ሶሬሳ በሠሩት ሥራ ከኃላፊነታቸው የታገዱና ቀጥታ የተላለፈባቸውን ዕግድ ሳያከብሩ አሠልጣኝ ሆነው ወደ ቶኪዮ ይዘው ለመሄድ ሲንቀሳቀሱ ነበር ሲል ፌዴሬሽኑ በጋዜጣዊ መግለጫው አብራርቷል፡፡

በሪዮ ኦሊምፒክ በውኃ ተሳታፊ የነበረችው ራሔል ለሦስት ወራት ዝግጅት ስታደርግ እንደነበርና ወደ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ለማምራት ብቸኛዋ ዋናተኛ እንደሆነች እንደምታውቅ ለሪፖርተር አስረድታለች፡፡

በጊዮን ሆቴል በቀን ሁለት ጊዜ ዝግጅት ስታደርግ እንደነበር የምትገልጸው፣ ዋናተኛዋ፣ ወደ ቶኪዮ ማምራት ያለባት እሷ ሆና ሳለ ሌላ ሰው መወሰዱ ጥያቄ እንዳጫረባት ትናገራልች፡፡ ‹‹በተለያዩ ውድድሮች ውጤት ማምጣቴን ተከትሎ፣ በዓለም አቀፉ ውኃ ዋና ፌዴሬሽን የተመረጥኩት እኔ ብሆንም፣ በግለሰብ ፍላጎት ከኦሊምፒኩ እንድቀር ተደርጌያለሁ፡፡›› በማለት ራሔል ታስረዳለች፡፡

በኮምቦልቻ የውኃ ዋና ስፖርትን የጀመረችው ራሔል፣ ከአገር ውስጥ ውድድር ባሻገር፣ የሪዮ ኦሊምፒክን ጨምሮ በአፍሪካ ሻምፒዮና ሞሮኮ፣ ደቡብ ኮርያ እንዲሁም በሩሲያ የተለያዩ ሻምፒዮና ላይ መሳተፍ ችላለች፡፡

እንደ ራሔል አስተያየት ከሆነ፣ ከኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር በነበረው አለመግባባት ተከትሎ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ወደ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ጽሕፈት ቤት ጎራ ቢሉም፣ ከውኃ ዋና መሆናቸውን ሲገልጹ ከበር እንዳይገቡ እንደሚደረጉ ለሪፖተር ሁኔታውን አስታውሳለች፡፡

‹‹ለችግሩ መፍትሔ ለመሻት ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ሄደን ከተወያየን በኋላ ስፖርት ኮሚሽን ችግሩን እንዲፈታው ተነግሮትና ስፖርት ኮሚሽንም ጠብቀሽ ክርክር ማድረጉን አሳውቆናል፡፡›› በማለት ራሔል ለሪፖርተር አስረድታለች፡፡

በዚህም ውኃ ዋና ስፖርት ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን በአገር ውስጥ እንዲሁም ከአገር ውጭ ክስ መመሥረቱንና እስከ ዓለም አቀፉ ስፖርት ገላጋይ አካል ድረስ ጋር እንደሚያደርሰው በጋዜጣዊ መግለጫው አሳውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...