Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ልናገር​​​​​​​የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን ከተሰነጣጠቀ ህልውናቸው ከወጡ...

​​​​​​​የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን ከተሰነጣጠቀ ህልውናቸው ከወጡ…

ቀን:

አንዳርጋቸው አሰግድ

ስለልሂቃን 

አንድ የቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ስከታተል፣ አንድ መሪ የፖለቲካ ተዋናይ ‹‹እኛ (እኛ የፖለቲካ ወይም የሥልጣን ልሂቃን) ከተነጋገርንና ከተስማማን ሕዝቡ ይነጋገራል ይስማማል›› ሲሉ አደመጥኩ። ውነት ላቸው። ወይም ሕዝብ “የሚያጋጩን ልሂቃኑ ናቸው” እያለ የሚያማርረውንና “ወይ ተባበሩ፣ ወይ ተሰባበሩ” እያለ የሚመክረውን ያስታወሰ አገላለ ነው። ይሁንና የማይነጋገሩትየማይስማሙትና የማይተባበሩት ለምንድው ተብሎ መጠየቅም አለበት።

ልሂቅ (Elite) የሚለው የወል ስያሜ በአጠቃላይ የሚውለው በኅብረተሰብ ውስጥ በሀብት ክምችቱና በሙያ ክህት ልቀቱ ባለው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ማኅበራዊ አቀማመጥ ምክንያት ከፍተኛውን ሥፍራ ለያዘው ማኅበራዊ ክፍል ነው። የፖለቲካ (የሥልጣን)፣ የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስ፣ የሃይማኖት፣ የሕክምና፣ የጥብቅና፣ የምሕንድስና፣ የአስተዳደር፣ የመገናኛ፣ የኪነ ጥበብወዘተ. ልሂቃን እየተባሉ ይለያሉ። የፖለቲካ ሥልጣን፣ የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስ፣ የአገልግሎት፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የባህል ትርዒቶች፣ የመዝናኛ… አቅርቦቶች ዋነኞቹ ተገልጋዮችና ተጠቃሚ ማኅበራዊ ክፍሎች ናቸው። መደበኛ ትምህርት ባይቋደሱም ቅሉ በባህላዊ የአመራርና የአስተዳደር ዕውቀት፣ የአነጋገር ችሎታና ማራኪነት፣ ፍትሐዊነት፣ ታማኝነት፣ በአስታራቂነትና አስማሚነት በሚጫወቱት ሚዛናዊ ሚና… የሚኖሩበትን ማኅበረሰብ ዕውቅና የተጎናፀፉ ግለሰቦችና ቡድኖችም ከልሂቃን ማኅበራዊ ክፍል ይመደባሉ።

ልሂቃን ሁሉ የፖለቲካ (የሥልጣን) ልሂቃን አይደሉም። በፖለቲካው መስክ ተማርተው የሥልጣን ባለቤት ለመሆን የሚለፉት ልሂቃን፣ የፖለቲካ ወይም የሥልጣን ልሂቃን (Political or Power Elite) በሚል ተለይተው ይታወቃሉ። ይህንን ማለት ግን የተለያዩት ልሂቃን በፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ሚና የላቸውም ማለት አይደለም። በሙያ ልቀታቸው፣ በድርጅቶች አቅማቸው፣ በፋይናንስና በግንኙነት ሰንሰለቶቻቸው፣ በእንቅስቃዎች ፈጣሪነትና በመሪነት ሚናዎቻቸው ምክንያት ሁሉ ስትራቴጂዊ የፖለቲካ ሥልጣን ሥፍራ ያሏቸው ማኅበራዊ ክፍል ናቸው። በፖለቲካው ዓለም ላይ ወሳኝ ተፅዕኖ ፈጣሪና አሳራፊ በመሆናቸው ምክንያትም የፖለቲካ ሥልጣን ውጤቶችን በየወቅቱም ይሁን በዘላቂነት የመወሰን ወይም የማስወሰን አቅም ያላቸው ናቸው። ለምሳሌም ለፖለቲካ ተዋናዮች በሚያደርጉት የገንዘብና የቁስ “ልገሳ” እና ማኅበራዊ አቀማመጣቸው በሚያሳልጥላቸው የግንኙነትና ስትራቴጂዊ የጥቅም ሰንሰለቶች አማካይነት በፖለቲካ ደት ላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በሚያሳርፏቸው ተፅኖዎች።

ይህ በዚህ ሆኖ ልሂቅና ምሁር የሚሉት የወል ስያሜዎች አንዳንድ ጊዜ ላግባብ በጥቅም ላይ ሲውሉ ይስተዋላል። በተለይም አንዳንድ የዜና ማሠራጫዎች ደግሞ ምሁር የሚለው የወል ስያሜ የሙያ ማዕረግ ስያሜ የሆነ ይመስል አንዳንድ የውይይት ተጋባዦቻቸውን “ምሁር እገሌ” እያሉ ሲያስተዋወቁ ይደመጣሉ። በሌላም ጊዜ “አቲቪስት” የሚባሉት ግለሰቦች ጭምር ምሁር እየተባሉ ይስተዋወቃሉ።

ልሂቃን ከላይ በአጭሩ የገለኳቸው ሲሆኑ ምሁራንና አክቲቪስቶች ግን የራሳቸው ማንነትና ማኅበራዊ ሥፍራና ሚና ያላቸው ግለሰቦች ናቸው። በ2013 ዓ.ም. “ቀና ፍላጎት እስካለ (የፖለቲካ) መንገድ አለ” በሚል ርዕስ በታተመው መሐፌ ውስጥ ለማመልከት እንደሞከርኩት ምሁራን የሚባሉት በአብዛኛው የተማሩ ሲሆኑ መደበኛ ትምህርት የገቡና የማጠናቀቂያ ማዕረግ የተቀበሉ ሁሉ ምሁር ናቸው ማለት አይደለም። ከነዚህ መካከል ሳዊ አሰላሳይ (Critical Thinker) የሆኑት ግለሰቦች ናቸው ምሁር የሚባሉት። ሂሳዊ አሰላሳይና ተመራማሪ ምሁር ለአስተሳሰብና ለአመለካከት ነፃነቱ ቀናተኛ ነው። ያለፈውንና የዘመኑን ነባራዊ ሁት በመረጃ አስደግፎ በሂሳዊ መንገዶች ለመመርመርና ለመተንትን የሚጥር ነው። አርቆ ለማየትና ለማስተዋል የሚተጋ እንደ መሆኑምውን ዘመን በሂሳዊ መንገዶች ለማንበብና ለመተንበይ ይሞክራል። መደምደሚያዎቹን በግልና በድፍረት በአደባባይ ያሳውቃል። አብዛኛውም ለቁሳዊ ጥቅም ከመገዛትና ለጥቅም ከማደር ሩቅ ነው።

ነገር ግን ከመደበኛ ትምህርት ያልገቡና የትምህርት ማጠናቀቂያ ማዕረግ ያልተቀበሉ ሂሳዊ አሰላሳይ ግለሰቦችም የተገለውን መሥፈርት በአመዛኝ እስካሟሉ ድረስ ምሁራን ናቸው። ለምሳሌም አንዳንድ የቅኔ ሊቅ፣ ባህታዊ፣ አዝማሪ፣ ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ሰዓሊ፣ ጋዜጠኛ፣ ገበሬ፣ አርብቶ አደር፣ ነጋዴወዘተ። ይህ ማለት ግን የፖለቲካ ድርጅትን ከሚቀላቀሉት የተማሩ ግለሰቦች መካከል አንዱ ወይም ሌላው ምሁር አይደለም ማለት አይደለም። እነዚህኞቹ የፓርቲ ርዕዮተ ዓለምና ፕሮጋንዳ አራማጅ (Ideologues) ከሚባሉት የምሁር ክፍል የሚመደቡ ናቸው።

አክቲቪሲት የሚባለውም ሁሉ ምሁር አይደለም። አክቲቪስት በፅኑ የሚያምንበትንም ሆነ የማያምንበትን የሆነ ነገር ሳይታክት የሚሰብክና የሚያራምድ (Promote) የሚያደርግ ግለሰብ ነው። ሥራ ነገሩ ወደ ደላላነት ስለሚያስጠጋውም ልክ እንደ ኮካ ኮላና ሳሙና አሻሻጭ ደላላ (Sales Man)፣ የፖለቲካ በራዊ ጉዳዮችን የሚያሻሽጥ ግለሰብ እየተባለ ይገለል። በዛሬው ወቅት በቴሌቪዥንና በዲጂታል ቴክኖሎጂ እየታገዘ ጭምር ደግሞ ከፈጠራ ዘባዎች እስከ ሰተኛ ምል ልፋ ድረስ ያሉትን ቴክኒኮች እየተጠቀመ ያሻሽጣል። እንደ ማንኛውም አሻሻጭ ዛሬ ይኼንን፣ ነገ ሌላውን ቢል ደንታ አይሰጠውም። ዛሬ ከአንዱ ጋር፣ ነገ ከሌላው ጋር ቢሆን አይገደውም። አሁንም ይህንን ማለት ግን አክቪስቶች ሁሉ አሻሻጭ ናቸው ማለት እንዳልሆነም እንዲስተዋል ያስፈልጋል። ምሁራዊ ሚናቸውን በአግባቡ የሚወጡ በርካታ አክቲቪስቶች አሉ።

ለማጠቃለል ያህል በወል ስያሜዎች ረገድ አስፈላጊው ሳቤና ጥንቃቄ ቢደረግ ለተሻለ መግባባት ይረዳል። ጅምላ አመለካከትና አፈራረ የሚያስከትሏቸውን መዘዞች ለመግታት ይበጃል። የፖለቲካ መፍትሔ መሣሪያዎች ሞክራሲያዊና ሰላማዊ የመሆናቸውን ዕድል ያበረታል።

ስለኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን በጥቂቱ   

አንድ ወጥ ልሂቃን በየትም አገር የሉም። ወይም የየትኛውም አገር ልሂቃን በአስተሳሰብና በአመለካከት ይለያያሉ። ለሀብትና ለሥልጣን ይፏከታሉ። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ ልሂቃን ከሌላው ዓለም ልሂቃን በምንም አይለዩም። መሰነጣጠቅና መፏከት አንደኛው የልሂቃን መገለጫ ባህሪ ነው ቢባልም ያስኬዳል። ይሁንና ግን እንደ የኢትዮጵያ ልሂቃን በርዕዮተ ዓለም፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በፖለቲካ አመለካከትና ፕሮግራም፣ በትንተና፣ በትግል ልት፣ በታሪክ አተራረክና አረዳድ፣ በሕገ መንግሥት፣ በብሔር፣ በአውራጃ፣ በጎጥ፣ በግዛክልልለዘመናት የተሰነጣጠቁና የተፈረካከሱ ልሂቃንን (Fragmented Elites) ለማግኘት ብዙ መድከም ያስፈልጋል። ለምን? ተብሎ መጠየቅና የማርከሻው አዎንታዊ ልውና ሊቀዳጅ የሚችልበትን የመገንቢያ መንገድ መፈለግ አለበት።

በመንግሥታዊ (State) አካላት አደረጃጀት ረገድ አስፈሚ፣ ሕግ አውጪና ተርጓሚ የሚባሉትን የሥልጣን ክፍፍል አወቃቀር ሳብ ገና በ18ኛው ክፍለ ዘመን ያመነጩት ሞንቴስኬ፣ ‹‹በአገር ግንባታ ሥርዓተ ተቋማትን (Institutions) የሚፈጥሩት ልሂቃን ናቸው። ሥርዓተ ተቋማቱ በኋላ ላይ ልሂቃኑን ይቀርፃሉ፣ ይገራሉ፤›› ይላሉ። ሞንቴስኬ ይህንን ሲሉ መሪዎቹ (ልሂቃኑ) ለሥርዓተ ተቋማቱ ሕግና ሥርዓት ብቻ ተገዝተው መንግሥታዊ ተቋማትን በሕግና በሥርዓት ብቻ የሚመሩና የሚያስተዳደሩ ይሆናሉ። እንዲያም ሲል የብሔረ መንግሥት (Nation State) ገንቢዎች ይሆናሉ ማለታቸው ነው። ወይም የፖለቲካ ልሂቃኑ ለተቋማት ሕግና ሥርዓት የማይገዙ እስከሆኑ ድረስ በሥልጣን ይባልጋሉ። ሙሰኛ ይሆናሉ። በሥልጣንና በሀብት ቅርምት ላይ ተጠምደው እርስ በርስ የሚጠላለፉ፣ የሚጋጩ፣ የሚጠፈፉ የፖለቲካ ልሂቃን ይሆናሉ ማለታቸው ነው። በሌላ አገላለጽ የፖለቲካ ልሂቃኑ በተቋማት ሕግና ሥርዓት እስካልተቀረፁና እስካልተገሩ ድረስ የተሰነጣጠቁ (የተፈረካከሱ) ልሂቃን ይሆናሉ ማለታቸው ነው።

አስከትለን ብንቀጥል ለኢትዮጵያ ልሂቃን መሰነጣጠቅና መፈረካከስ መሠረታዊና ወሳኙ ምክንያት ኢትዮጵያ “ጠንካራ” በሚባሉ መሪዎች መልካም ፈቃድ እንጂ በሕግና በሥርዓት መሠረት በሚሠሩ ሥርዓተ ተቋማት ስትመራና ስትስተዳደር የኖረች አገር አለመሆኗ ነው። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን የፖለቲካ ግብ፣ ለሥልጣንና ሥልጣን ለሚያስገኘው ሀብትና ማኅበራዊ ክብር የመሮጥ (የመሰባር) ሆነ። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ዓለም የዚያኑም ያህል የተሰነጣጠቁና የተፈረካከሱ የፖለቲካ ልሂቃንን አብዝቶ የሚያመርት ሆነ።

ናይጄሪያዊው አይዛክ ኦላዋሌ እንደሚሉት፣ ‹‹የተሰነጣጠቁ የፖለቲካ ልሂቃን ‘ቆሻሻ ጨርቃቸውን’ በአደባባይ እያጠቡ እርስ በርስ የሚናጩና ሕዝብን የሚያናጩ ልሂቃን ናቸው፤›› (Isaac Olawale Albert Deconstructing Elite Fragmentation in Nigerian Politics 2012)። ኒኮል ጋሊና አስከትለው እንደሚሉትም፣ ‹‹በተሰነጣጠቁ (በተፈረካከሱ) የፖለቲካ ልሂቃን በሥርዓተ ተቋማቱ ጥንካሬ ረግቶና ደርጅቶ የሚቆምን የአዛዝና የአስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት የሚቻል አይሆንም፤›› (Nicole Gallina The Impact of Political Elite Conduct on State Reform: The Case of Ukraine 2008)

የጠቀስኳቸውን ሳቤዎች ወደ ኢትዮጵያ አምጥተን ብናጤናቸው፣ ኢትዮጵያ የተቋማት (Institutes) ፈጣሪ የሆኑ የፖለቲካ ልሂቃን መካን የሆነችበት ጊዜ የለም። ልሂቃኖቿ ራሳቸው በፈጠሯቸው ተቋማት የተቀረፁበት፣ የተገሩበትና ለተቋማቱ ሕግና ሥርዓት ተገ የሆኑበት ጊዜ ግን የለም ማለት ይሆናል። ይም ተቋሟቱ (Institutes) እንደ ሥርዓተ ተቋም (Institutions) የተመሩበትና የተስተዳደሩበት ጊዜ የለም። በዚሁ ቀጥለንም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን እስከዚህ የሚሰነጠቁትና የማይስሙት ራሳቸው በፈጠሯቸው ተቋማት ያልተቀረፁና ያልተገሩ በመሆናቸው ምክንያት ነው ለማለት ይቻለናል።

ኢትዮጵያ ስለዚህም ገው ግለሰብ ወይም ቡድን ራሱ ተቋም ሆኖና ለአገልጋዮቹ ሥልጣንንና ሀብትን በመልካም ፈቃዱ እያከፋፈል ሲገዛት የኖረች አገር ሆነች። በሌላ አነጋገር የጌታና ሎሌ (Patronage/Clientelism) በሚባለው ሥርዓት ወይም በጥቀመኝ ልጥቀምህና በእከክልኝ ልከክለህ የአገዛዝ ሥርዓት በተሳሰሩ የፖለቲካ ልሂቃን ስትገዛና ስትስተዳደር የኖረች አገር ሆነች። በዛሬው ቋንቋ ብንገልው ለገው ግለሰብ ወይም ቡድን ብቻ ባደሩ “ሆድ አደሮች” የምትገዛ አገር ሆነች። ወይም ሙርማንና ፒቸር በአንድ ስለምዕራብ አፍሪካ ባቀረቡት ሑፋቸው “የሆድ ፖለቲካ” ባሉት የፖለቲካ አገዛዝ ዓይነት ስትገዛ የኖረች አገር ሆነች (Marissa Moorman & Anne Pitcher The Politics of the Belly 1989)። የያኑም ያህል በተቋማቱ ጥንካሬ ረግታና ደርጅታ የሚቆምን የአዛዝና የአስተዳደር ሥርዓት፣ ሕግና ደንብ ለመገንባት ሳይቻላት የቀረች አገር ሆነች።

ዚህ አኳያ ጌታው ንጉሠ ነገሥት ተባለ አገረ ገ፣ ወይም ፕሬዳንት ተባለ ጠቅላይ ሚኒስትር ሎሌውም ቀኛዝማች ተባለ ሚኒስትር፣ ወይም ኮሚሽነር ተባለ ካድሬ ልዩነት የለውም። ስለሆነም ነው ኢትዮጵያ ጌው “ውሻ በበላበት ይጮኸል” እለ በሎሌዎቹ ላይ ሲተርት የተኖረባት አገር የሆነችው። ሎሌውም፣ “እኔ የእገሌ አሽከር” እያለ ሲፎር የኖረባት አገር የሆነችው። በአብዮቱ ዘመን ካድሬውም፣ “ከአብዮታዊ ሊቀመንበራችን ጋራ ወደፊት” እያለ ሲምልና ሲገዘት የኖረው። በ1970ዎቹ ዓመታት የብሔር እንቅስቃሴዎች እየጎለበቱ ከመጡ ወዲህ ደግሞ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን በየብሔር ኮሮጆዎቻቸው ውስጥ እየታሸጉ የባሰውን ተሰነጣጠቁ። ተፈረካከሱ። ካድሬዎቻቸውም “ከአብዮታዊ ሞክራሲ ጋራ ወደፊት” እያሉ መማልና መገዘት ውስጥ ገብተው ለ27 ዓመታት ናኙ። “እኔ የእገሌ አሽከር” ከሚለው የፊውዳል ኢትዮጵያ ካድሬዎች ፉከራ በምንም የሚለይ አልነበረም።

ኢትዮጵያ እንዲያም ሲል፣ “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል” በሚለው አሉታዊ ብሂልተቋማቱ በፖለቲካ ልሂቃኖቿ የተሰለቡ አገር ሆና ኖረች። የዘመናት ታሪኳም በፖለቲካ ልሂቃኖቿ የግጭት፣ የጦርነትና የመጠፋፋት ዝክሮች ተሞልቶ የሚገ ሆነ። የሺ ዘመናት መንግሥት ባለቤት ብትሆንም ወደ ብሔረ መንግት ግንባታ ለመሻገር የተቸረች አገር ሆና ኖረች። ኢትዮጵያ ከሆድ አደር አገዛዝ ሥርዓት እስካልወጣችና በተቋማት ሥርዓት የተቀረፁና የተገሩ ለቲካ ልሂቃን ባለቤት እስካልሆነች ድረስም በሥርዓት ከማይነጋገሩት፣ ከማይስማሙት፣ ከማይተባበሩትና እርስ በርስ ከሚጠፋፉት የፖለቲካ ልሂቃኖቿ ልውና አትገላገልም። የኢትዮጵያ የ ፖለቲካ ታሪክና የ በራዊ ፖለቲካ ተመራማሪዎች ይህንን ጉዳይ በዝርዝር ቢያጠኑት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ልሂቃን ልውና ምንነት ለመረዳት የሚስችል ውጤት ይገኛል። የዚያኑም ያህል ማርከሻውን መድኒት ለማግኝት የሚቻል ይሆናል ብዬ እገምታለሁ።

የተሰነጣጠቁና የተፈረካከሱ የፖለቲካ ልሂቃን ከሚስማሙበት ይልቅ የሚለያዩበትን እያጎሉ እርስ በርስ ይናጫሉ። ተከታዮቻቸውን ከጉም በተለፉ ትርክቶችና ውሸቶች ጭምር እያንቦገቡ ያጋጫሉ። ሕዝብንና አገርን ያናጫሉ። ያጋድላሉ። ንብረት ያድማሉ። ደግሞም በነገረ ሥራቸው ተኩራርተውና ራሳቸውን በራሳቸው አግዝፈው ይወናኛሉ። በማህሎኝነት ተወጥረው ይንጎባለላሉ። መታከም ያለበት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን ልውና ነው።

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ልሂቃን መሰነጣጠቅ ለማከም

ከላይ የጠቀስኳቸው ኦላዋሌ እንዳሉት የልሂቃን መሰነጣጠቅ መረን ለቅቆ ከናኘ፣ የመንግሥታዊ አስተዳደርን መና የአገርን መፍረስ እስከ ማስከተል ሊደርስ ይችላል ነባራዊ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታቸውን በፅሞና አጢነው የጋራ ወደፊታቸውን በጋራ ለመገንባት የሚወያዩ፣ የሚደራደሩና የተስማሙ የፖለቲካ ልሂቃን ግን ሕዝብና አገርን ያስቀድማሉ። ይተባበራሉ። ያስተባብራሉ። መልካም አስተዳደርንና ፍትሕን የሚያከብሩና የሚያደጁ ሥርዓተ ተቋማትን በጋራ ይገነባሉ። ለተቋማቱ ሕግና ሥዓት ይገዛሉ። የተቋማትን ሥልጣንና ውስጣዊ ራስ ገዝነት ያከብራሉ። ያስከብራሉ። ለጋራ ዕድገትና ብልፅግና በጋራ ይተጋሉ። ሰላምን ያሰፍናሉ። የአገርንና የሕዝብን ብሩህ ተስፋ ጎህ ያበራሉ። ኬያዊው ቢንያም በዳሶ ስለኬያ የፖለቲካ ልሂቃን ምንነት ባቀረቡት አንድ ሑፍ እንዳሉት“በምርጫዎች ወቅት አልፎ አልፎ ከሚከሰተው የብሔሮች ግጭት ው፣ ኬያ በአንፃራዊ የተረጋጋች አገር ናት። ለዚህም ዋናው ምክንያት፣ የኬያ ልሂቃን ለሥልጣንና ሥልጣን ለሚያስገኘው ጥቅም የሚታገሉት በሕገ መንግሥቱ መሠረት ስለሆነ ነው።አለመረጋጋት ባቀነቀነ ቁጥር የኬያ ሕገ መንግሥት ብዙ ጊዜ ተሻሽሏል። ይህም የኬያ ልሂቃን በሕገ መንግሥትና በሕግ መሠረት ብቻ ለመመራትና ለመተዳደር ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎትና አካሄድ ያመለክታል (Biniam E.Bedasso Ethnicity, Intra–Elite Differentiation and Political Stability in Kenya 2015)።

‹‹የኬያ ሕገ መንግሥት በውነትም፣ ከ1955 እስከ 2011 (1963 እስከ 2019) ባሉት 56 ዓመታት ውስጥ 46 ጊዜ ተሻሽሏ። በመሆኑም የኬያ የፖለቲክ ልሂቃን በሕግና በሥርዓት ብቻ የሚስተዳደሩና ለሕግና ሥርዓት ብቻ የሚገዙ የፖለቲካ ልሂቃንና ተቋማትን ወደ መገንባት አቀኑ። በተሻለ ገነቡ። ሮ ዙሮ የብሔረ መንግሥታቸውን ግንባታ ጎዳና ያዙ። ወይም የፖለቲካ ልሂቃኑ የብሔረ መንግሥት ግንባታ መሐንዲሶች ሆኑ። ለትውልድና ለታሪክ የሚተርምድ ጥለው የሚያልፉ መሥራች አባቶች (Founding Fathers) እየተባሉ እስከ ወዲያኛው የሚታወሱና የሚወደሱ ሆኑ

ከላይ የጠቀስኳቸው መሪ የፖለቲካ ተዋናይ ‹‹እኛ የፖለቲካው (የሥልጣን) መሪዎች (ልሂቃን) ከተነጋገርንና ከተስማማን ሕዝቡ ይነጋገራል ይስማማል፤›› ብለው አሉ። ይሁንና ስለግባቸው ቀርቶ በሥርዓት ስለሚነጋገሩበት መንገድ ያቀረቡት ዝርዝር ሳብ አልነበረም። ብቻ እያንዳንዱ የፖለቲካ ቡድን ሥልጣን ስለሚይዝበት ወይም ሥልጣንን ስለሚጋራበት የጣምራ (Coalition)፣ የአድን (Salvation)፣ የብሔራዊ አንድነት (National Unity) አስተዳደር ይመሥረት እያለ ጥሪዎችን በነጋ ጠባ ይወረወራል። ያስተጋባል።

ነገሮች በእንህ እንዳሉ የ2013 ዓ.ም. ምርጫ ተከናወነ። አሸናፊው ፓርቲ በመስከረም 2014 ዓ.ም. አስተዳደሩን ይመሠርታል። በዚህም የቅ ምርጫው የሽግግር አስትዳደር ጥሪዎች በምርጫው ውጤት እንደታለፉ ግል ሆኗል። የሚያስገርመው እንበልና ግን አንዳንድ የፖለቲካ መሪዎች አሁንም ለሽግግር መንግሥት መቋቋም ሲጠሩ ይሰማሉ። ሌሎችም ከ ጭራሹ ጊዜያዊ የክልል አስተዳደራቸውን እንደ መሠረቱ ጭምር እስከ ማስታወቅ ሄደዋል። ደግሞ ሌሎችም በመሣሪያ ኃይል አዲስ አበባ ሥልጣን እየተሟሟቱ ናቸው። የ1987 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት በሙሴ ፅላት ላይ የተከተበ መለኮታዊ ቃል ይመስል፣ ሕገ መንግሥቱ ከተነካ “እንገነጠላለን” እያሉ የሚሰብኩና በተደራጀ መልክ የሚቀሰቅሱም አልታጡም። ይህ ሑፍ ለኅትመት በሚላክበት ዕለት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በሁለት ተፃራሪ ሁኔታዎች ዓይነተኛ ኖ ይገኛል።

አንደኛ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. በሰሜን ኢትዮጵያ የጀመረው ውጊያ ነው። ውጊያው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃንን ደግሞም በብሔር ረድፎች ተሰነጣጥቀው ከጀመሩት የሥልጣን ትግል ጋራ የተያያዘ መሆኑን ማተት የሚታወቀውን መድገም ይሆናል። ይሁንና ውጊያው በአንድ ወገን አስከፊ በሆኑ መንገዶች እየተስፋፋና እየተካረረ የቀጠ መሆኑንና በሌላውም ወገን የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት እየጋበዘ ጭምር የሚካሄድ ውጊያ መሆኑን በማሳወቅ መወሰን ቀደም ባለ አንድ ሑፌ ለማመልከት እንደሞከርኩት ለብዙ መዘዞች ጦስ መሆኑን አሳንሶ መገመት ይሆናል። ለትውልድ የሚያትመውን የታሪክ ጠባሳና የሚያስቋጥረውን ርሾ አለመመዘን ይሆናል። ስለዚህም የተለያዩ የፖለቲካ መፍትሔ መንገዶችን በብልህነትና በጥንቃቄ መፈለግ ይገባል ብዬ አምናለሁ።

ሁለተኛ2010 ዓ.ም. የተካሄደውን ለውጥ ተከትሎ ተቋማትን ወደ ሕግና ሥርዓት ለማስገባትና ለሕግና ሥርዓት ተገ ለማድረግ በርካታ ጉዳዮች ተከናውነዋል። ንዳንዶቹ በምርጫ ቦርድ፣ በፍትሕ፣ በማረሚያ ቤቶች፣ በፖሊስና በሠራዊት አመራርና አስተዳደር ረገድ የተከናወኑት መሠረታዊ የማሻሻያ ለውጦች (ሪፎርሞች) ናቸው። ስለዚህም ጭምር ነው ለማለት ይቻላል የ2013 ዓ.ም. ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ። ቅሬታ ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶችም ቅሬታቸውን ለማሳወቅና ፍትሕ ለመሻት ወደ ፍርድ ቤቶች መሄድን መረጡ። ከፍ ሲል ከጠቀስኩት ቢኒያም በዳሶ ልዋስና ይህም፣ ‹‹(የኢትዮጵያ) የፖለቲካ ልሂቃን በሕግና በሕጋዊ ውሳኔ መሠረት ብቻ ለመመራትና ለመስተዳደር፤›› ማቅናት እንደ ጀመሩ የሚያመለክት መልካም ጅማሮ ነው። የማሻሻያ ለውጦቹ ተጠናክረው የቀጠሉትንና ሕጋዊ መንገዶች የኢትዮጵያ ልሂቃንና የሕዝቦቿ የፖለቲካ ባህል ለመሆን የበቁትን ያህል ኢትዮጵያ ሞክራሲያዊ ሥርዓትን ካዳበሩ የአፍሪካ አሮች ተርታ ለመሠለፍ የበቃች አገር ትሆናለች። ብሔረ መንግሥቷን መገንባት ከሚያስችላት ጎዳና ውስጥ ትገባለች።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን ከተሰጣጠቀና ከተፈረካከሰ ልውናቸው የሚወጡት የአገሪትን ተቋማት ሥርዓት፣ ሕግና ደንብ የሚጠብቅና የሚያከብር አስተዳር ባለቤት እስከሆነች ድረስ ነው። የተቋማትን ሥርዓት፣ ሕግና ደንብ የሚጠብቁና የሚያከብሩ የፖለቲካ (የሥልጣን) ልሂቃን ባለቤት እስከሆነች ድረስ ነው።

ይህ ጉዞ ለኢትዮጵያ ልውናና ሉዓላዊነት ሲባል መኬድ ያለበት ረጅምና ወጣ ገባ መንገድ ነው። ተጠናክሮ እንዲቀጠልበት ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን ለሥርዓተ ተቋማት ተገዥ የሆኑትን ያህልከተሰነጣጠቀ ልውናቸው ይወጣሉ። በኢትዮጵይ የፖለቲካ ዓለም ሰማያት ላይ የሰላምና የሞክራሲያዊ አብሮነት ዘመን ጎህ ይቀዳል።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...