Sunday, June 23, 2024

​​​​​​​[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው ገብተው ከአማካሪያቸው ጋር ስለወቅታዊ ጉዳዮች እያወጉ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር እንዲያው አንድ ያልገባኝን ነገር ልጠይቅዎት ነው፡፡
 • መፍትሔ ታመነጫለህ ተብሎ የአማካሪነት ቦታ ቢሰጥህ የተገላቢጦሽ ሥራህ መጠየቅ ሆነ፣ ግድ የለም ጠይቅ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር በማማከር ሥራዬ ያጎደልኩት አለ እንዴ?
 • እኔ አማክርሃለሁ፣ ጠይቅ አንተ፡፡
 • ኧረ ክቡር ሚኒስትር አይቀልዱብኝ፣ እንዲያው የክተት ጥሪው ነገር ግራ ገብቶኝ እንዲያስረዱኝ ብዬ እንጂ ሌላ እንኳ አልነበረም፡፡
 • የክተት ጥሪው ምን ጥያቄ ፈጠረብህ?
 • በታሪክ እስከማውቀው ክተት የሚጠራው ለውጭ ጠላት ነበር፣ የአሁኑ ክተት ግን ለአገር ውስጥ መሆኑ ትንሽ ጥያቄ ፈጠረብኝ፡፡
 • ብቻቸውን መስለውህ ነው?
 • ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ብቻቸውን አይደሉም፣ በሱዳን በኩል ከተሠለፉት እስከ አሜሪካ ድረስ ክተት ብለው ዘምተውብን አይደለም እንዴ ያሉት?
 • እሱስ ልክ ብለዋል፣ ሕዝቡ ጥሪውን ተቀብሎ የሚያደርገው ድጋፍ አስገራሚ ነው የሆነብኝ፡፡
 • ወጣቱ ወደ መከላከያ ለመቀላቀል የሚተመው ሚስጥሩ ገብቶት አይመስልህም? ብቻ እንዳልከው አስደናቂ ምላሽ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ወጣቱ ብቻ መሰለዎት እንዴ እየተመመ ያለው? ሠንጋውስ ቢሉ?
 • ምኑ?
 • ስንት ሺሕ ሠንጋ በስንቅ መልክ ሲቀርብ አላዩም እንዴ?
 • አላየሁም፡፡
 • እንዴት አላዩም?
 • የምናየው እንደምንመርጠው ይወሰናል፡፡
 • አቤት ሠንጋ… አቤት ሠንጋ…
 • ከስንት ነገር መካከል የታየህ ሠንጋው ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር እሱማ የክተት ጥሪው ነው ዋናው፣ እኔ ራሱ…
 • አንተ ራሱ ምን?
 • አማካሪ ባልሆን ጥሪውን ተቀብዬ እከት ነበር፡፡
 • አንተ በጊዜ ከከተትክ ይበቃል፡፡
 • ወዴት?
 • ወደ ቤትህ!

[የክቡር ሚኒስትሩ ስልክ ጠራ፡፡ ሰሞኑን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እያነጋገሯቸው የነበሩ አንድ የአውሮፓ ዲፕሎማት ናቸው] 

 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • እንደምን አሉ አምባሳደር?
 • ክቡር ሚኒስትር በሠራችሁት ሥራ በጣም አዝኜ ነው የደወልኩት፣ ጥረታችንን የሚያበላሽ ተግባር ነው የፈጸማችሁት፡፡
 • አምባሳደር ምንድነው ያሳዘነዎት ተግባር?
 • ቅድመ ሁኔታዎቹን በሙሉ አንስተው ድርድሩን ሊቀበሉ ጫፍ በደረሱበት ሰዓት ክስ መሠረታችሁባቸው፡፡ የሰላም ጥረቱን የሚያደናቅፍ አካሄድ ነው የመረጣችሁት፡፡
 • አምባሳደር ቀድሞውንም ቢሆን በወንጀል መጠየቅ የሚገባቸው እንዳሉ አሳውቀውናል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ክስ እንዳይመሠረትባቸው ያደረግንባቸው አመራሮች መኖራቸውን አይዘንጉ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ማን ክስ ያልተመሠረተበት አለ? ሁሉም ተመሥርቶበት የለ እንዴ?
 • ክስ ያልተመሠረተባቸው አሉ አምባሳደር፡፡ እነሱ ይህንን ያውቃሉ ለዚያ ነው ክስ በተመሠረተባቸውና ባልተመሠረተባቸው መካከል ግጭት ማለቴ የአቋም ልዩነት የተፈጠረው፡፡
 • እና በድርድሩ ጉዳይ ላይ ቡድኑ ለሁለት የተከፈለው ለዚያ ነው ማለት ነው? አንዳንዶቹ ድርድሩን ለመቀበል ቅድመ ሁኔታዎቹ እንዲነሱ ሲጠይቁ ሌሎቹ አሻፈረኝ ብለው አስቸግረውናል፡፡
 • አምባሳደር በእኛ በኩል ወንጀለኛ ብለን ከፈረጅነው አካል ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንደሌለን ነው ልነግርዎት የምችለው፣ በፍጥነት ወደ ድርድር የማይመጡ ከሆነም መንግሥት በቅርቡ ውሳኔ ሊያሳልፍ እንደሚችል እንዲያውቁ እንፈልጋለን፡፡
 • የምን ውሳኔ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እስካሁን የመከላከል እንጂ የማጥቃት ዕርምጃ እንዳልወሰድን የሚያውቁ ይመስለኛል፡፡
 • አዎ አውቃለሁ፡፡
 • ይህ የሆነው ወደ ድርድር እንዲመጡ ብለን ነው አምባሳደር፣ በፍጥነት ወደ ድርድር የማይመጡ ከሆነ ግን የማጥቃት ውሳኔ ለማሳለፍ እንገደዳለን፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቶኪዮ ያመራውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድንን በተመለከተ ከአንጋፋ አትሌቶች ጋር እየመከሩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር እንዴት ኢትዮጵያን የሚያህል አገር በተከበረችበት የኦሊምፒክ ስፖርት በሁለት ሰው ብቻ ትወከላለች?
 • መንግሥት ስፖርቱን መደገፍ እንጂ አስተዳደር ውስጥ ሊገባ እንደማይችል ታውቃላችሁ ብዬ እገምታለሁ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እሱን እናውቃለን፣ ነገር ግን ችግሩ የተፈጠረው መንግሥት ሳያውቀው ስለገባ ነው፡፡
 • መንግሥት ሳያውቀው ስለገባ ነው?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • እንዴት?
 • ሰውዬው መንግሥት ናቸው፡፡
 • መቀለድ ጀመራችሁ? እንደዚያ ከሆነ ምርጫ ማድረግ ነዋ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እሱንም እኮ ሞክረን ነበር ግን አልቻልንም፡፡
 • ለምን?
 • ኮሮና ብለው አራዘሙት፡፡

 

 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...