Saturday, April 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አፍሪካ ፋይናንስ ኢንተርናሽናል ብሔራዊ ባንክን ከአፍሪካ ብልጫ ያለው ብሎ ሸለመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

አፍሪካ ፋይናንስ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ ተቋም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር)ን የአፍሪካ ምርጥ የማዕከላዊ ባንክ ገዥ በማለት ሲሰይም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ደግሞ ምርጥ የአፍሪካ 2021 ምርጥ ማዕከላዊ ባንክ በማለት ሸለመ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተሸላሚ የሆነው በማዕከላዊ ባንክ አመራር ረገድ በመላ አፍሪካ ከሚገኙ ባንኮች መካከል ብልጫ ያለው ውጤት በማስመዝገቡ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አመራርን በተመለከተ ስትራቴጂያዊ ግቡንና ዓላማውን ለማሳካት ይቻለው ዘንድ፣ ለባለሙያዎቹ የአቅም ግንባታም ሆነ ሌሎች ማበረታቻዎችን መተግበሩ ባለሙያዎችን ለመሳብና ያሉትንም ለማቆየት ብሎም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በማስቻሉ የባንኩን ገዥ ዕውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡

በአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ የተመዘገበው ከፍተኛ እመርታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያካሄዳቸው የሪፎርም ሥራዎች ያስገኙት ውጤቶች በሙሉ ባንኩን ተሸላሚ አድርገውታል፡፡

ባንኩ ለዚህ ሁሉ ውጤት የበቃው ደግሞ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) ወደ ባንኩ ገዥነት በመጡ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

ዶ/ር ይናገር ወደ ባንኩ ገዥነት ከመጡ ጀምሮ በተወሰዱትርምጃዎች የአገሪቱ የፋይናን ሴክተር ላይ በጉልህ የሚታይ ዕድገት መምጣቱን የመሰከረው ድርጅቱ፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲረጋጋና እንዲያድግ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውል በብስለት መምራታቸውን ድርጅቱ አስረድቷል፡፡ ‹‹በሁሉም ወቅት በምክንያት ባንኩን ወደፊት ያራመደ፤›› ሲልም ገልጿቸዋል፡፡

 ምንም እንኳን የውስጥም ሆነ የውጭ ጫናዎች ቢኖሩም፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በዕድገት ጎዳናው ሊቀጥል የቻለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተጫወተው ትልቅ ሚና መሆኑን ስለመጥቀሱ ዕውቅናውን በተመለከተ ባንኩ ያወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓለማችን ትልቅ ተግዳሮት በሆነው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የፋይናንስ ዘርፉ እያደረገ የመጣው በዶ/ር ይናገር የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከቁልፍ አጋሮቹ ጋር በመተባበር ባደረገው የቅርብ ክትትልና አመራር መሆኑን አመልክቷል፡፡

ከመስከረም 2013 .ም. አንስቶ የተካሄደው የንዘብ ቅየራ በስኬት መጠናቀቁ ደግሞ የአገሪቱ ባንኮች የፋይናንስ ተደራሽነታቸው እንዲጎለብትና ገንዘብ በሚገባ ማሰባሰብ እንዲችሉፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉንም ድርጅቱ አብራርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች