Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ደቡብ ግሎባል ባንክ አዲስ የቦርድ ሰብሳቢ ሰየመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የደቡብ ግሎባል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ሹመት ማፅደቁንና አዲሱ ቦርድም  ቢቂላ ሁሬሳን (ዶ/ር) የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ መምረጡን ደቡብ ግሎባል ባንክ አስታወቀ፡፡

ደቡብ ግሎባል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ያካሄደው ታኅሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ቢሆንም፣ በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኩ ላይ ጥሎት በነበረው እገዳ ምክንያት የተመራጮቹ ሹመት ሳይፀድቅ ቆይቶ ነበር፡፡ አሁን ግን ባንኩ ዕገዳውን አንስቶ የአዲሶቹን የደቡብ ግሎባል ባንክ ሹመት በማፅደቁ ሹመቱ የፀደቀላቸው የቦርድ አባላት ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳን የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ አድርገው ሰይመዋል፡፡

አቶ ዮናስ ጌታቸው ደግሞ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው አዲሶቹ የቦርድ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ የቀድሞውን ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኑረዲን አወልና ምክትላቸውን አቶ ማቴዎስ አሰሌን ተክተው የሚሠሩ ናቸው፡፡

ዶ/ር ቢቂላ የባንኩ ሁለተኛ የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ፣ ባንኩ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በቦርድ ሰብሳቢነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ኑረዲን አወል መሆናቸው ይታወቃል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች