የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ከህውሐት ቡድን ጋር ተሳትፎ አላቸው ያላቸውን የቀድሞ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔና እነ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ ዮሐንስ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ በ74 ከፍተኛ መኮንኖችና ግለሰቦች የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡
የሽብር ወንጀል ክሱ የተመሰረተባቸው ከፍተኛ መኮንኖች መካከል ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ፣ሜጀር ጀነራል ዩሀንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ብርጋዴር ጄነራል ምግባይ ሀይለ፣ሜጀር ጀነራል ሀለፎም አለሙ፣ ሜጀር ጀነራል ሀለፎም እጅጉ፣ ሜጀር ጄነራል አታክልቲ በርሄና ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ ይገኙበታል። አቶ ሀዱሽ አበበና አቶ ቢኒያም ተወልደም በክሱ ተካተዋል።
ተከሳሾቹ ከህውሐት አመራሮች ተልኮ ተቀብለው ወታደራዊ ኮማንድ በማደራጀትና በመምራት፣ በፌደራል ፖሊስ፡ በሰሜን ዕዝ ጦር፣የአማራና የአፋር ክልሎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ዓቃቤ ህግ በክሱ ተካቷል።
ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የተመሰረተ ቢሆንም ቢሆኑም ዳኞች ባለመሟላታቸው ምክንያት የመጥሪያ ቀጠሮ አልተሰጠም፡፡