Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርት​​​​​​​ኢትዮጵያ  በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአትሌቲክስ ባሻገር የነበራት ተሳትፎ

​​​​​​​ኢትዮጵያ  በቶኪዮ ኦሊምፒክ ከአትሌቲክስ ባሻገር የነበራት ተሳትፎ

ቀን:

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከጀመረ የሳምንት ዕድሜ አልፎታል፡፡ ኢትዮጵያ ከምትወከልበት የስፖርት ዓይነቶች በአትሌቲክሱ ከማራቶን በስተቀር በአራት ዙር የተከፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ቡድን ወደ ሥፍራው አምርቷል፡፡

ኢትዮጵያ በዋና፣ በብስክሌት፣ በወርልድ ቴኳንዶና በአትሌቲክስ ተወክላለች፡፡ በመጀመሪያው ዙር ላይ ወደ ቶኪዮ ያመራው ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በኦሊምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ የተወዳደረው ሰሎሞን ቱፋ ይገኝበታል፡፡

እ.ኤ.አ 2018 በአፍሪካ ሻምፒዮና በ54 ኪሎ ግራም ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ፣ በዚያው ዓመት በአፍሪካ ጨዋታ የነሐስ ሜዳልያ ማምጣት የቻለው ሰሎሞን ኢትዮጵያን በኦሊምፒክ ለመወከል መብቃቱ ትልቅ ስኬት ሆኖለታል፡፡ የ22 ዓመቱ ወጣት ሰሎሞን ተወልዶ ያደገው በቆጂ ከተማ ነው፡፡ የረዥም ርቀት ተወዳዳሪ እህቶቹን መስታወት ቱፋና ትዕግስት ቱፋን እያየ ያደገው ሰሎሞን፣ በስድስት ዓመቱ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ ተደረገ፡፡

- Advertisement -

ከስድስት ዓመቱ ጀምሮ ዕድገቱን አዲስ አበባ እህቶቹ ጋር ያደረገው ሰሎሞን፣ ገና በለጋ ዕድሜው ወርልድ ቴኳንዶን መጀመሩን ከሪፖርተር ጋር በነበረው ቆይታ አስረድቷል፡፡

በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ተሳትፎን አቀላጥፎ፣ በአኅጉርና በዓለም ሻምፒዮናዎች ላይ መሳተፍ ችሏል፡፡ በኢትዮጵያ ያለውን የውድድር ዕጥረት ተከትሎ፣ ሰሎሞን በኮሪያና ሩሲያ ላይ ተጋብዞ ተወዳድሯል፡፡

ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ማለፉን ካወቀበት ጊዜ አንስቶ፣ በኮቪድ-19 ምክንያት እስከተራዘመበት ጊዜ ጠንክሮ ሲዘጋጅ ነበር፡፡

ስትጋልብ እንደነበረ አነጋጋሪ ሆኖ አልፏል::  ሰላም በውድድሩ ወቅት ባጋጠማት ሕመም ምክንያት በቶኪዮ እንድትቆይ ተደርጓል:: የ23 ዓመቷ ሰላም እ.ኤ.አ በ2017 በግብፅ፣ በ2018 በሩዋንዳ እንዲሁም በ2021 ግብፅ ላይ ያደረገቻቸው ግልቢያዎች በኦሊምፒኩ እንድትመረጥ አስችሏታል:: ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1956 ሜልቦርን ኦሊምፒክ ገረመው ደምቦባ፣ መስፍን ተስፋዬ፣ ፀሐይ ባሕታ እንዲሁም መንግሥቱ ንጉሤ በብስክሌት ተወክለው ነበር:: በ1960 ሮም ኦሊምፒክም አምስት ጋላቢዎች ኢትዮጵያን መወከል ችለዋል:: ኢትዮጵያ ለብስክሌት የበለጠ ትኩረት መስጠት ከቻለች፣ ውጤታማ መሆን የሚያስችላት ዕድል እንዳላት ግልፅ ነው:: በዚህም በቀጣይ ኦሊምፒኮች ላይ በበርካታ ስፖርቶች መወከል የሚቻልበትን ዕድል ለማስፋት ከወዲሁ የቤት ሥራዋን መሥራት እንደሚገባት ፍንጭ የሰጠ አጋጣሚ ነው:: የዋና ተሳትፎ ውዝግብ የማያጣው የዋና ስፖርት ዘንድሮም ኢትዮጵያ በዩኒቨርሳሊቲ ዕድል ማግኘት ችላ ነበር:: የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርት ፌዴሬሽንና የኦሊምፒክ ኮሚቴው ባለመስማማታቸው በሴት የተገኘው ዕድል መጠቀም አልተቻለም:: አንድ ሴት እና አንድ ወንድ መሳተፍ ቢኖርባቸውም ኢትዮጵያ በወንድ ዋናተኛውን ቶፊክ አብዱልመሊክ ብቻ አካፍላለች:: በሪዮ ኦሊምፒክ ባለው ሰዓት መመረጥ ቢገባውም፣ ሳይመረጥ ቀርቶ በሮቤል ኪሮስ የተወከለው አብዱርመሊክ ዘንድሮ ዕድል ደርሶት በቶኪዮ ኦሊምፒክ መክፈቻ ወቅት ባንዲራ ማንገብ ችሏል:: ዓርብ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በተደረገ የ50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ 26.65 መግባት ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል:: ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በወንድ ያገኘቸውን ዕድል መጠቀሟ የሚደነቅ ቢሆንም መወከል የምትችል ሴት ዋናተኛ እያለች ዕድሉን ማጣቷ በርካቶችን ያሳዘነ ነበር:: ዋናተኛው ቶፊክ አብዱልመሊክ የብስክሌት ጋላቢዋ ሰላም አምሃ በ

የወርልድ ቴኳንዶ ተሳትፎው

ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀመረው ውድድር፣ ሰሎሞን ሦስት ተጋጣሚዎችን አስተናግዶ ነበር፡፡ በ58 ኪሎ ግራም ውድድር በመጀመሪያው ዙር የጃፓኑን ሱዚኪን የገጠመው ሰለሞን 22 ጊዜ ሰንዝሮ በበላይነት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ሁለት ጊዜ ብቻ ቡጢ አርፎበታል፡፡ ይኼም ድንቅ ብቃት ሰሎሞንን በቀጥታ ወደ ሁለተኛው ዙር አሳልፎት ነበር፡፡ ሰሎሞን በሁለተኛው ዙር ቱኒዚያዊውን መሐመድ ከሊልን ነበር የተፋለመው፡፡

ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለማለፍ በተደረገው የሁለተኛው ዙር ውድድር ላይ እንደ አንደኛው ዙር ፍልሚያ ቀላል አልነበረም፡፡ ሰሎሞን በጣቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በፈለገውና ባቀደው መንገድ ሊሰምርለት እንዳልቻለ ገልጿል፡፡

ጉዳቱን ተቋቁሞ የተፋለመው ሰሎሞን በቱኒዚያዊው 32ለ9 በሆነ ውጤት ተረቷል፡፡ በመጨረሻም ለነሐስ ሜዳሊያ የሩሲያውን ሚካኤል አርታሞኖቭን ገጥሞ፣ 27ለ5 በሆነ ውጤት ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቆ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲፕሎማ ማግኘት ችሏል፡፡

 በኢትዮጵያ እምብዛም ትኩረት በማይሰጠው ቴኳንዶ፣ በኦሊምፒክ ላይ ተሳታፊ ማግኘት በራሱ ጥረት ይፈልጋል፡፡ በርካቶች ኢትዮጵያ በቶኪዮ በሰሎሞን ተወክላ በማየታቸው ደስታቸው ወደር አልነበረውም፡፡ ይኼንንም ደስታ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሰሎሞንን በማበርታትና መልዕክታቸውን በመግለጽ አሳይተዋል፡፡

የሰሎሞን የቶኪዮ ተሳትፎ ኢትዮጵያ በቀጣይ በኦሊምፒክ ያላትን ውስን ውክልና የበለጠ እንድታሰፋው ፍንጭ የሰጠ እንደሆነ በርካቶችን ያስማማ ጉዳይ ነው፡፡

ሐሙስ ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ ለደረሰው ሰሎሞን ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን፣ እናቱና እህቶቹ ተገኝተው ነበር፡፡

የብስክሌት ተሳትፎ

ኢትዮጵያ በሰላም አምሃ በብስክሌት ተወክላ ነበር፡፡ እሑድ ሐምሌ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. 137 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የጎዳና ላይ ግልቢያ ከፊት ሆና መምራት ጀምራ ነበር፡፡ ሆኖም በጊዜው በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ውድድሩን መቀጠል አልቻለችም፡፡ እሷን ጨምሮ በርካታ ብስክሌተኞች ግልቢያውን ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡

ምንም እንኳን ግልቢያውን አቋርጣ ለመውጣት ብትገደድም፣ ተሳትፎዋ በራሱ የሚደነቅ ነበር፡፡ ሰላም በውድድሩ ላይ ከነበሩት ተወዳዳሪዎች ጋላቢዎች መካከል አምስት ዓመታት ወደ ኋላ የቀረ ብስክሌት ስትጋልብ እንደነበረ አነጋጋሪ ሆኖ አልፏል፡፡

  ሰላም በውድድሩ ወቅት ባጋጠማት ሕመም ምክንያት በቶኪዮ እንድትቆይ ተደርጓል፡፡ የ23 ዓመቷ ሰላም እ.ኤ.አ በ2017 በግብፅ፣ በ2018 በሩዋንዳ እንዲሁም በ2021 ግብፅ ላይ ያደረገቻቸው ግልቢያዎች በኦሊምፒኩ እንድትመረጥ አስችሏታል፡፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ1956 ሜልቦርን ኦሊምፒክ ገረመው ደምቦባ፣ መስፍን ተስፋዬ፣ ፀሐይ ባሕታ እንዲሁም መንግሥቱ ንጉሤ በብስክሌት ተወክለው ነበር፡፡ በ1960 ሮም ኦሊምፒክም አምስት ጋላቢዎች ኢትዮጵያን መወከል ችለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለብስክሌት የበለጠ ትኩረት መስጠት ከቻለች፣ ውጤታማ መሆን የሚያስችላት ዕድል እንዳላት ግልፅ ነው፡፡ በዚህም በቀጣይ ኦሊምፒኮች ላይ በበርካታ ስፖርቶች መወከል የሚቻልበትን ዕድል ለማስፋት ከወዲሁ የቤት ሥራዋን መሥራት እንደሚገባት ፍንጭ የሰጠ አጋጣሚ ነው፡፡  

ሰሎሞን አዲስ አበባ ሲደርስ አቀባበል ካደረጉለት መካከል እናቱ ይገኙበታል

የዋና ተሳትፎ

ውዝግብ የማያጣው የዋና ስፖርት ዘንድሮም ኢትዮጵያ በዩኒቨርሳሊቲ ዕድል ማግኘት ችላ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርት ፌዴሬሽንና የኦሊምፒክ ኮሚቴው ባለመስማማታቸው በሴት የተገኘው ዕድል መጠቀም አልተቻለም፡፡ አንድ ሴት እና አንድ ወንድ መሳተፍ ቢኖርባቸውም ኢትዮጵያ በወንድ ዋናተኛውን ቶፊክ አብዱልመሊክ ብቻ አካፍላለች፡፡ በሪዮ ኦሊምፒክ ባለው ሰዓት መመረጥ ቢገባውም፣ ሳይመረጥ ቀርቶ በሮቤል ኪሮስ የተወከለው አብዱርመሊክ ዘንድሮ ዕድል ደርሶት በቶኪዮ ኦሊምፒክ መክፈቻ ወቅት ባንዲራ ማንገብ ችሏል፡፡

ዓርብ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በተደረገ የ50 ሜትር ነጻ ቀዘፋ 26.65 መግባት ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡

ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በወንድ ያገኘቸውን ዕድል መጠቀሟ የሚደነቅ ቢሆንም  መወከል የምትችል ሴት ዋናተኛ እያለች ዕድሉን ማጣቷ በርካቶችን ያሳዘነ ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...