Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊኮሜርስ ግቢውን እንዲለቅ ታዘዘ

ኮሜርስ ግቢውን እንዲለቅ ታዘዘ

ቀን:

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቴ የንግድ ሥራ ትምህርት ቤት (ኮሜርስ) ለ80 ዓመታት ገደማ ሲገለገልበት የቆየውን ቅጥር ግቢ ለቅቆ እንዲወጣ ትዕዛዝ እንደደረሰው ታወቀ፡፡

በ1935 ዓ.ም. ተመሥርቶ እስካሁን ድረስ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሥልጠናዎችን በመስጠት የሚያስመርቀው ትምህርት ቤቱ፣ ከሁለት ዓመት ገደማ ጀምሮ አሁን ካለበት ሥፍራ እንደሚነሳ ሲነገር የቆየ የነበረ ቢሆንም፣ ከሁለት ቀናት በፊት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመጣ ትዕዛዝ ግቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ተነግሮታል፡፡

የዚህ ውሳኔ መነሻ ትምህርት ቤቱ ያለበት አካባቢ የፋይናንስ ማዕከል ተብሎ ለባንኮችና ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ግንባታ እየዋለ የሚገኝ እንደሆነ ለሪፖርተር የተናገሩት የትምህርት ቤቱ ኃላፊ ወርቁ መኮንን (ዶ/ር)፣ በዚህ ምክንያት ከሆነ እንዲያውም ትምህርት ቤቱ በዚህ ሥፍራ መቆየት ነው እንጂ ያለበት መነሳት አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

- Advertisement -

ከአሁን ቀደም ይኼንን ሐሳብ አስመልክቶ ምክረ ሐሳብ እንዲያቀርብ የተቋቋመ ኮሚቴ እንደነበርና ከባንኮች ጋር በቅርበት መሆኑ ለትምህርት ቤቱም ሆነ ለተማሪዎች እንዲሁም ለፋይናንስ ተቋማቱ ጠቃሚ ነው በማለት ምክረ ሐሳብ አቅርቦ የነበረ መሆኑን፣ አሁን ግን ሚኒስቴሩ ትምህርት ቤቱን ሳያማክር ውጡ የሚል ትዕዛዝ ሰጥቷል ሲሉ ወርቁ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ የአገሪቱን የመንግሥትና የግል ዘርፍ መዋቅሮችን የሰው ሀብት ፍላጎት ለማሟላት ታልሞ የተመሠረተና ይኼንንም ሲያደርግ እንደቆየ በማስረዳት፣ አሁን ባለበት ቦታ መሆኑ ከፋይናንስ ዘርፉ ጋር ፍፁም የሚጣጣም ነው ይላሉ፡፡ ይኼም በዓለም የተለመደ እንደሆነና የኦክስፎርድ ሞዴልና የዎል ስትሪት ሞዴል በማለት፣ የለንደንንና የኒውዮርክ ከተማ የፋይናንስ ማዕከላትንና የትምህርት ቤቶችን ቅንጅት አጣቅሰዋል፡፡

‹‹እየታየ ያለው ማብለጭለጩ ነው፡፡ ነገር ግን እዚህ መሆኑ የማይገኝ ዕድል ነው፤›› ብለዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ እንደ ንግድ ባንክና ቡና ባንክ ለመሳሰሉ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት በሥልጠናና በቅጥር ሥራ እንደሚሠራላቸው ኃላፊው ጠቁመው፣ ይኼ የሚጠናከርበት ዕድል ይበልጥ ይፈጠር ነበር በማለት ውሳኔው ለምን እንደተፈለገ አልገባንም ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አንድ ግዙፍ ሕንፃ በግቢው የተገነባ ሲሆን፣ የቅጥር ግቢውን ሃምሳ በመቶ የሚሸፍኑት አራት ሕንፃዎች ደግሞ በቅርስነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ ይኼንንም የሚያረጋግጥ ደብዳቤ በቅርቡ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የተሰጣቸው መሆኑን የገለጹት ወርቁ (ዶ/ር)፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ግን ገና እንዳልተሰጣቸው አልሸሸጉም፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ቤቱ ያሳወቀው ምንም ነገር እንደሌለና ትዕዛዙ የመጣው ከሚኒስቴሩ እንደሆነ በመግለጽ፣ ቦታው ከትምህርት ቤት ይልቅ ለምን ተፈልጎ እንደሆነም እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ 5,000 የሚጠጉ ተማሪዎች፣ ከ100 በላይ መምህራንና ከ200 በላይ የአስተዳደር ሠራተኞች እንደሚገኙ የጠቆሙት ኃላፊው፣ መንግሥት ቦታውን እፈልጋለሁ ቢል እንኳን ለእነዚህ የሚበቃ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ ሆኖም መንግሥት ስንት አገራዊ አጀንዳ ወጥሮት ሳለ ይኼንን ማድረጉ ጊዜው አይደለም በማለት፣ ኮሜርስ ብዙ ወዳጆች አሉትና ትልቅ የፖለቲካ አጀንዳ ሊሆን ይችላል ሲሉም ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በግጭቶች ፍርኃት ሳቢያ እዚህ የሚያስተምሩ ወላጆች ልጆቻቸው እንደሚያስተምርና ከመቀሌና ከተለያዩ ሥፍራዎች በግጭት ሳቢያ የሚመጡ ተማሪዎችን እያስተናገደ እንዳለ በመጠቆም፣ ከሥፍራው ተነስቶ ወደ ሌላ ሥፍራ መሄዱ ብቻ ሳይሆን እነዚህንም ጉዳዮች ያገናዘበ ውሳኔ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ ግቢ ይገባል መባሉም ልክ እንዳልሆነ፣ ቅጥር ግቢው እንኳን አዲስ ተጨማሪዎች ተማሪ ሊይዝ ይቅርና ለራሱም በቂ ቦታ እንደሌለው አስረድተዋል፡፡

‹‹ይኼ ኮሌጅ ብራንድ ነው፣ ማደግ አለበት እንጂ መፍረስ የለበትም፡፡  ለመገንባት 80 ዓመት ፈጅቷል፡፡ አቆይቶ ለትውልድ ማሻገር ነው የሚያስፈልገው፤›› በማለት የተከረራከሩ ሲሆን፣ ለዩኒቨርሲቲው እስከ 15 ሚሊዮን ብር በዓመት ፈሰስ በማድረግ ራሱን የቻለ ተቋም ሞዴል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...