Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምርጫ እንዲደገም ጥያቄ በቀረበባቸው 28 የምርጫ ወረዳዎች ጉዳይ  ቦርዱ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ...

ምርጫ እንዲደገም ጥያቄ በቀረበባቸው 28 የምርጫ ወረዳዎች ጉዳይ  ቦርዱ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ተሰጠ

ቀን:

ሰኔ 14 ቀን 2013 .ም.  በተካሄደው አገራዊ ምርጫ ሕግ የጣሱ የድምፅ አሰጣጥ ሒደቶች ተፈጽሞባቸዋል ባላቸው 28 የምርጫ ወረዳዎች ምርጫው እንዲደገም፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ለፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ላይ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝሰጠ።

አቤቱታውን እያየው የሚገኘው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሲሆን፣ ትዕዛዙን የሰጠው ኢዜማ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. በተደረገው የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ከጅምሩ እስከ ድምፅ ቆጠራ ድረስ በነበሩት ሒደቶች፣ ከምርጫ ሕግ አዋጅ 1162/2011 እና ቦርዱ ካፀደቀው መመርያ ቁጥር 15/2013 ውጪ 28 ምርጫ ወረዳዎች (የምርጫ ክልሎች) የተለያዩ ሕገወጥ የሆኑ ተግባራት ተፈጽሞባቸዋል በማለት ምርጫው እንዲደገም ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ያቀረባቸውን ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ነው፡፡

ኢዜማ ምርጫውን ሲጀምር እንደ መጀመርያ ምርጫ አድርጎ የወሰደው ቢሆንም፣ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ግን ከጅምሩ እስከ የምርጫ ውጤት ገለጻው ድረስ የነበረው ሒደት ግን ካለፉት አምስት ምርጫዎች ያልተለዬ መሆኑን እንዳረጋገጠ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ኢዜማ በተሳተፈባቸው የምርጫ ክልሎች ከፍተኛ የሆነ በደል የተፈጸመበት መሆኑን ጠቁሞ፣ በምርጫ ሕጉ በተቀመጠው መሥፈርት መሠረት የቪዲዮ፣ የሰነድና የሰዎች  ማስረጃዎች በማካተት የመጀመርያ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅሬታውን አስገብቶ እንደነበር አስታውሶ፣ ቦርዱሰጠው ምላሽ ግን ሕጉን ያልተከተለና የማይጠበቅ መሆኑን አስታውቋል፡፡

 28 የምርጫ ወረዳዎች ላይ ከድምፅ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ፣ ከቀበሌ እስከ ክልል ባሉ የገዥው ፓርቲ አመራሮች፣ ከቀበሌ ሚሊሻ እስከ ክልል ልዩ ኃይል ድረስ ባሉ የፀጥታ አስከባሪዎች፣ የምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈጸሚዎችና ማንነታቸውና ሕጋዊ የሥራ ኃላፊነታቸው በግልጽ ያልታወቀ ግለሰቦች በድምፅ አሰጣጥ ሒደትና በምርጫው ውጤት ላይ እጅግ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን ጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ሕገ መንግሥቱን፣ የምርጫ አዋጁንና ምርጫ ቦርድ ያወጣቸውን መመርያዎች በቀጥታ የሚፃረሩ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የሚያስረዱ 192 የሰው ምስክሮችና ተንቀሳቃሽ ምሥሎችን ጨምሮ በቂ ማስረጃዎች በማያያዝ፣ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት  በማቅረቡ፣ ችሎቱ የቀረበለትን ማስረጃ መርምሮ ቦርዱ ሐምሌ 30 ቀን 2013 .ም. መልሱን በጽሑፍ እንዲያቀርብ ቀጠሮ ሰጥቷል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...