Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለም​​​​​​​ሰላማዊ ሰዎችን ሰለባ ያደረገው የአፍጋን ታሊባን ጦርነት

​​​​​​​ሰላማዊ ሰዎችን ሰለባ ያደረገው የአፍጋን ታሊባን ጦርነት

ቀን:

በአፍጋኒስታን ከ20 ዓመታት በፊት በመንግሥትና በታሊባን ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ሰበብ በማድረግ በአገሪቷ ከትመው የነበሩት አሜሪካና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወታደሮች አፍጋኒስታንን ወደ ሰላም መመለስ አልቻሉም፡፡ ይህ ባልተሳካበትም የእርስ በርስ ከአገሪቱ መውጣት የጀመሩት ከግንቦት 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡

የእነሱን መውጣት ተከትሎ በርካታ የአፍጋኒስታን ከተሞችን የተቆጣጠረው የታሊባን ታጣቂ ቡድን ከአፍጋን መንግሥት ወታደሮች ጋር ጦርነት ገብቷል፡፡

የመንግሥት ወታደሮች በአየር ድብደባ የታሊባን ታጣቂዎች በእግር የጀመሩት ውጊያም ንፁኃንን ከተዋጊ ኃይሎች ሳይለይ እያረገፈ ይገኛል፡፡ አልጀዚራ የተባበሩት መንግሥታትን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በአየርና በምድር እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከፍተኛ ጥፋት እየደረሰ ነው፡፡

የአፍጋን ፖሊሶች የሮኬት ላውንቸር ይዘው ይዋጋሉ

በየቀኑ የሚመዘገበው ሞት፣ የጤና ተቋማትና የሰላማዊ ሰዎች ቤት መውደም ችግሩን አባብሶታል ተብሏል፡፡

የውጭ መከላከያ ሠራዊት አባላት ከአፍጋን መልቀቅ በጀመሩ ማግስት ከባድ ጥቃት መሰንዘር የጀመረውና በተለይ ገጠራማውን አካባቢ ጨምሮ በርካታ ከተሞችን የተቆጣጠረው ታሊባን፣ በአፍጋኒስታን የጦር ወንጀል ፈጽሟል ተብሏል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ንፁኃንም ተጨፍጭፈዋል ሲሉ አሜሪካና እንግሊዝ ኮንነዋል፡፡ ጥቃቱንም የጦር ወንጀል ብለውታል፡፡

ታሊባን በርካታ ከተሞችን የከበበ ሲሆን፣ በሄልማንድና ካንዳሃር ግዛቶች ዙሪያ ከባድ ውጊያ ጠቅሷል፡፡

የአፍጋን የደኅንነት አካላትና ታሊባንን አንቀበልም ያሉ የአፍጋን ዜጎች ታሊባን ላይ ከባድ ጦርነት መክፈታቸውም ተሰምቷል፡፡ ይሁን እንጂ ታሊባኖች በሄልማንድ ከተማ እምብርት መድረሳቸውን በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት፣ በእሥር ቤቶች፣ በከተማዋ እምብርት በሚገኙ ቁልፍ ሕንፃዎች ማቆሚያ የሌለው የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው ሲልም የአልጀዚራው ጀምስ ቤይስ ዘግቧል፡፡

የመንግሥት ባለሥልጣናትም ታሊባን በርካታ አካባቢያዊ የሬድዮ ጣቢያዎችን ይዘዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ጣቢያዎቹ ሥርጭት አቋርጠዋል፡፡

የሚከፈለው ተከፍሎ ከተሞች በታሊባን ቁጥጥር ሥር እንዳይውሉ እናደርጋለን ሲል ቃል በገባው የታሊባን መንግሥት የላሽካር ከተማን በታሊባን መነጠቁ ስትራቴጂክና ሥነ ልቦናዊ ውድቀት አስከትሎበታል ተብሏል፡፡

የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ አገሪቱ ለከፋ የደኅንነት ሥጋት የተጋለጠችው አሜሪካ ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ ወታደሮቿን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስወጣቷ ነው ብለው ኮንነዋል፡፡

ለፓርላማቸው የደኅንነት ዕቅድ ያቀረቡት ጋኒ፣ በአፍጋን ያለው የደኅንነት ችግር በስድስት ወራት ውስጥ እንደሚስተካከል፣ ለዚህም አሜሪካ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷን ተናግረዋል፡፡

በመንግሥትና በታሊባን በሕዝብ አስተዳደርና በፖለቲካ ጽንሰ ሐሳብ የተፈጠረው ልዩነት አገሪቷን ለእርስ በርስ ጦርነት ዳርጓታል፡፡

በአሜሪካና ኔቶ የሚደገፈው የአፍጋኒስታን መንግሥት ደጋፊዎችና የታሊባን ደጋፊዎች ለረዥም ጊዜያት ሲገዳደሉ የቆዩ ቢሆንም፣ ካለፈው ወር ወዲህ እንደ አዲስ ያገረሸው የእርስ በርስ ግጭት ግን ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረ ሞት በእጅጉ የበለጠ እንዲመዘገብ ምክንያት ሆኗል፡፡

ታሊባኖች በርካታ የአፍጋኒስታን ከተሞችን እየተቆጣጠሩም ነው፡፡ የአሜሪካ ጦር ከሥፍራው ሲለቅ ወዲያው በቦታው የተተካው ታሊባን ከአፍጋን መንግሥት ወታደሮች በኩል አልበገር ባይነትም አልገጠመውም ነበር፡፡ በርካታ ወታደሮች እጃቸውን እየሰጡ፣ ታሊባኖች የተለያዩ ከተሞችን ሲቆጣጠሩም ያለምንም ተኩስ እንደነበር የአካባቢው  ነዋሪዎች ተናግረው ነበር፡፡

የታሊባንን ባንዲራ የያዙ የአፍጋን ዜጎች በፓኪስታንና አፍጋኒስታን ድንበር አካባቢ

ነገር ግን ኃይሉን አጠናክሮ ታሊባን የተቆጣጠራቸውን ከተሞች ዳግም እናስመልሳለን ያለው የአፍጋን መንግሥት፣ የአየር ድብደባ አያካሄደ ነው፡፡

የአየር ድብደባ እያደረገ የሚገኘው የአፍጋን መከላከያ፣ ባለፈው ሰኔ ብቻ ከስድስት ሺሕ በላይ የታሊባን ታጣቂዎችን መግደሉንና በርካታ ማቁሰሉን አሳውቋል፡፡ በአፍጋን ከሚገኙ 419 ቀጣናዎች ደግሞ በርካቶቹ በታሊባን ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

በአፍጋኒስታን ባግራም ላለፉት ሃያ ዓመታት የጦር ሠፈሯን መሥርታ የከረመችው አሜሪካ፣ ታሊባንን ከአፍጋኒስታን ጠራርጎ ለማስወጣትና በአሜሪካው 9/11 ጥቃት ግንባር ቀደም የነበረውን አልቃይዳና የጥቃቱ ጠንሳሾች ለማጥፋት ነበር፡፡ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ አሜሪካ በባግራም የመሠረተችውን የጦር ሠፈር ለአፍጋኒስታን መንግሥት አስረክባለች፡፡

የአፍጋን መንግሥት የመከላከያ ኃይል ጠንካራ ኦፕሬሽን ጀምሯል

በአፍጋን ጦርነት ከተቀሰቀሰ እ.ኤ.አ. ከ2001 ወዲህ ከ66 ሺሕ በላይ የአፍጋን ወታደሮችና ፖሊሶች ተገለዋል፡፡ የአሜሪካ ሰርቪስ አባላት እስከ ሚያዝያ 2021 ድረስ 2448 መገደላቸውን አሶሽየትድ ፕሬስ አስፍራል፡፡

ከአፍጋን ንፁኃን ዜጎች 47,245፣ የታሊባን ተዋጊዎች ደግሞ ከ51 ሺሕ በላይ መሞታቸውም ተዘግቧል፡፡

  • ጥንቅር በምሕረት ሞገስ
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...