Monday, June 24, 2024

​​​​​​​[በፖለቲካ አቋማቸው የሚተቹት ክቡር ሚኒስትሩ ሌሎች ሚኒስትሮች በማኅበራዊ ገጻቸው ጻፉ ስለተባለው ጉዳይ አማካሪያቸውን መረጃ እየጠየቁ ነው]

 • አንዳንድ ሚኒስትሮች ሰሞኑን በትዊተር ገጻቸው ላይ የጻፉትን ነገር ተመልክተሃል እንዴ?
 • ስለምን የጻፉትን ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እኔ ምን አውቄ ወዳጆቼ ደውለው ስለወቀሱኝ ነው የጠየቅኩህ፡፡
 • ምን ብለው ወቀሱዎት ክቡር ሚኒስትር? 
 • አንተስ እንዴት ተቃውመህ አትጽፍም ብለው። 
 • ገባኝ… ገባኝ…
 • ምንድነው ሌሎቹ ሚኒስትሮች የጻፉት? 
 • የምዕራባውያኑን የሪጅም ቼንጅ ሴራ በመቃወም ነው የጻፉት። 
 • ሪጅም ቼንጅ? ምን ማለታቸው ነው?
 • ምዕራባውያኑ አሁን ያለውን የውስጥ ግጭት ተጠቅመው የመንግሥት ለውጥ ሴራ እየሸረቡ እንደሆነ ጠቋሚ ነገሮች አሉ፣ ይህንን ነው ፊት ለፊት ወጥተው የተቃወሙት። 
 • አሃለራሴ ሲሉ ነዋ ወዳጆቼ የወቀሱኝ። 
 • ለራሴ ሲሉ? የሪጅም ቼንጅ ሴራው ከተሳካ አልተርፍም ማለትዎ ነው?
 • እሱ ከተሳካማ ሁሉንም ነው የሚመለከተው፣ ከዚያ በፊት ማለታቸው ነው። 
 • አልገባኝም አለቃ?
 • ሴራውን ተቃውሜ ባለመጻፌ ከላይ ሊመጣ የሚችለው አደጋ እንዴት አይታይህም? 
 • ከላይ የምን አደጋ ይመጣል?
 • ኦ… እንኳን እኔ አንተም አትተርፍም፣ በል አሁን ቶሎ የማኅበራዊ ትስስር ገጼ ላይ የሚጽፈውን ጥራውናቶሎ ሴራውን የሚቃወም መልዕክት ጻፉ፡፡
 • እሺ ክቡር ሚኒስትር እንዳሉት ሪጅም ቼንጁን እንደተቃወሙ እንጽፋለን። 
 • ሪጅም ቼንጅ የሚለውን ቃል እንዳትጠቀሙ። 
 • ለምን? 
 • ለየት ብንል አይሻልም? አለቃንም ለማስደሰት ለየት ቢል ይሻላል። 
 • ምን ቢባል ይሻላል ታዲያ?
 • በሬውን አናርድም ቢባል አይሻልም? ሰሞኑን የተገለጸው በሬ። 
 • ለዶሮ በሽታ በሬውን አናርድም የሚለውን?
 • አዎ እሱን በሬ አናርድም በልልኝ! 

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር ሰሞኑን ከዚያ ወገን በወጣው የድርድር ቅድመ ሁኔታ ዙሪያ እያወጉ ናቸው]

 • ክቡር ሚኒስትር የፌዴራል መንግሥትን ወደ ድርድር እንዲመጣ ለማስገደድ ሲሉ ጦርነቱን እንደቀጠሉበት ሰሞኑን ተናግረዋል፣ አዲሱ መረጃ ይህ ነው። 
 • እንዴት አድርገው ነው የሚያስገድዱት? መንግሥት አይደል እንዴ የተናጠል ተኩስ አቁም በማድረግ ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ጥሪ ያቀረበው? 
 • መንግሥት ግጭቱን በሰላም ለመፍታት ጥሪ አቅርቧል እንዴ ክቡር ሚኒስትር? 
 • የተናጠል ተኩስ አቁም ሲታወጅ ምንድነው የተባለው? አንተም አልሰማሁም ልትል ነው? 
 • አልሰማሁም ክቡር ሚኒስትር፣ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙ ሰው የሚያውቅ አይመስለኝም፣ ጫና እያደረጉ ያሉ የውጭ መንግሥታትም ይህንን የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ 
 • የውጭዎቹን ተዋቸው፣ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ነው የእነሱ ነገር። ይልቅ አንተ በይፋ የተነገረውን ጉዳይ አለማወቅህ ነው የሚገርመው። 
 • በይፋ የተነገረ መረጃ ነው እንዴ ክቡር ሚኒስትር? 
 • የተናጠል ተኩስ ማቆም መታወጁን የሚገልጸው መግለጫ ምን ይላል? 
 • አርሶ አደሩ የክረምቱን ወቅት ተረጋግቶ እንዲጠቀምበት በማሰብ መታወጁን አይደል እንዴ የሚገልጸው? 
 • እሱ አንደኛው ምክንያት ነው። 
 • ሌላው ምክንያት ምንድነው ክቡር ሚኒስትር? 
 • ሌላው ምክንያት በረሃ ከተበተነው ኃይል ውስጥ ወደ ሰላም መንገድ መምጣት ፍላጎት ላላቸው ዕድልመስጠት ነው። 
 • ፍላጎት ያላቸው አሉ ማለት ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እሱን እነሱ ያውቁታል። 
 • ግን አብዛኞቹ አመራሮች ሰሞኑን ክስ ተመሥርቶባቸው እንዴት ወደ ሰላም ሊመጡ ይችላሉ ክቡር ሚኒስትር?
 • ለምን አይመጡም? በዕድሉ መጠቀም ከፈለጉ መምጣት አለባቸው። 
 • እኮ እንዴት አድርገው ሊመጡ ይችላሉ መንግሥት ክሱን ያነሳል? 
 • ለምን ያነሳል? 
 • ክሱ ካልተነሳ ምን ማድረግ ይችላሉ? እንዴትስ ብለው ይመጣሉ?

 

 • ዋናው ለሰላም ያላቸው ፍላጎት ነው፣ ፍላጎቱ ካለ በቀላሉ ወደ ሰላም መምጣት ይችላሉ።
 • ክቡር ሚኒስትር እንዴት አድርገው? 
 • እጃቸውን ሰጥተው! 

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው ከቅርብ ዘመዳቸው ጋር ስለኑሮ ውድነት እየተማረሩ ሲያወሩ ደረሱ]

 • ደህና አመሻችሁ የሞቀ ወሬ ይዛችኋል ልበል?
 • በልእናንተ ምን አለባችሁ? ሥጋትና ጭንቀት ሁሉ የሞቀ ወሬ ነው የሚመስላችሁ። 
 • የምን ሥጋትና ጭንቀት ነው? ምን ተፈጠረ? 
 • ይኸው ሕዝቡ ከላይ እስከ ታች ምን እንደገጠመው እንኳን አታውቁም?
 • እንዴት አናውቅም? 
 • ካወቃችሁማ በኑሮ ውድነት ሲሰቃይ መልስ ትሰጡት ነበር። 
 • የኑሮ ውድነቱ ጊዜያዊ ነው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፈታል።
 • ጊዜያዊ ነው? ችግር ጊዜ ይሰጣል እንዴ ደሃው ምን በልቶ ይኑር?
 • ለደሃውማ መንግሥት የፍጆታ ሸቀጦችን እያቀረበ ነው።
 • ልክ ነህ ዜና ላይ እየቀረበ ነው። 
 • የፍጆታ ሸቀጥማ እያቀረብን ነው። 
 • ዳቦ ነው?
 • አንዱ ዳቦ ነው፡፡
 • የት አለ? 
 • ዳቦ ብቻ አይደለም፣ ዘይትም እያቀረብን ነው።
 • የሕዝቡ ጩኸት የሞቀ ወሬ ነው የሚመስላችሁ የምለው ለዚህ ነው። 
 • እንዴት?
 • ዳቦ የለ፣  ዘይት የለ፣  ስኳር የለ፣  ሲሚንቶ የለምን አለ?
 • እንዴት ምንም የለም?
 • እንዴት የለም አትበል፣ ካለ ንገረን። 
 • ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እጥረት ተከስቶ ሊሆን ይችላል፡፡ 
 • ወቅታዊ ሁኔታ፣ አሃ አዋጁ የሸቀጥ አቅርቦትንም ይመለከታል ማለት ነው? 
 • የቱ አዋጅ?
 • የጥሞና ጊዜ አዋጁ! 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...