Monday, December 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የቀንጢቻ ታንታለም ማዕድን በመንግሥትና የውጭ ኩባንያ ጥምረት እንዲለማ ተወሰነ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በመንግሥት የልማት ድርጅት ይዞታ ሥር ይገኝ የነበረው የቀንጢቻ ታንታለም የማዕድን ልማት ፈቃድ ተሰርዞ፣ በመንግሥትና በውጭ ኩባንያ ጥምረት እንደ አዲስ እንዲለማ ተወሰነ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ የሚገኘው ከፍተኛ የታንታለም ማዕድን ክምችት የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት በሆነው የኢትዮጵያ የማዕድን፣ ፔትሮሊየምና ባዮ ፊውል ኮርፖሬሸን ሥር ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት እየተመረተ ወደ ውጭ ሲላክ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ከአንድ ወር በፊት የኮርፖሬሽኑን የታንታለም ማዕድን ልማት ፈቃድ ሰርዟል፡፡ ይህንን ተከትሎም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አፍሪካ ማይኒንግ ኤንድ ኢነርጂ የተባለ አውስትራሊያ የተመዘገበ ኩባንያ ከመንግሥት ጋር በሽርክና የታንታለም ማዕድን ክምችቱን በዘመናዊ መንገድ በማምረት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ስምምነት ማድረጉን ተቀብሎ፣ አዲስ ፈቃድ መስጠቱን ሪፖርተር ለማወቅ ችሏል፡፡

ሪፖርተር ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ምንጮች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አፍሪካ ማይኒንግ ኤንድ ኢነርጂ የተባለው ኩባንያ ከመንግሥት ጋር በፈጠረው የሽርክና ኩባንያ ውስጥ 51 በመቶ ድርሻ በመያዝ የታንታለም ማዕድን ልማቱን በበላይነት ይመራል፡፡

መንግሥትን በመወከል በማኅበሩ ውስጥ 49 በመቶ ድርሻ የሚኖራቸው የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ፔትሮሊየምና ባዮ ፊውል ኮርፖሬሸንና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንደሆኑም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የቀንጢቻ ታንታለም ማዕድን ክምችት እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ ውስጥ በሩሲያ የጂኦሎጂ ባለሙያዎች የተገኘ ሲሆን፣ በማዕድን ክምችቱ ከታንታለም ውጪ የዩራኒየምና ሊቲየም ማዕድናት እንደሚገኙም ተረጋግጧል፡፡

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያው ኮርፖሬሽን ለውጭ ገበያ የሚያቀርበው ያልተጣራውን የታንታለም ማዕድን እንደሆነ፣ በዚህም ምክንያት ማዕድኑን የሚረከቡ የውጭ ገዥዎች ካልተጣራው የታንታለም ማዕድን ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ማዕድናትን በነፃ የመጠቀም ዕድል ሲያገኙ ቆይተዋል፡፡ ከቀንጢቻ የታንታለም ማዕድን ክምችት በዓመት ከ90 እስከ 95 ቶን ታንታለም በአማካይ ለውጭ ገበያ ሲያቀርብ የነበረው ኮርፖሬሸኑ፣ በዓመት እስከ 20 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያገኝ ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች