Friday, July 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝና አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ፍርድ ቤት ባለመቅረባቸው መጥሪያውን እንዲያደርሱ...

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝና አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ፍርድ ቤት ባለመቅረባቸው መጥሪያውን እንዲያደርሱ የታዘዙ ኃላፊዎች ታስረው እንዲቀርቡ ተወሰነ

ቀን:

የገንዘብ ሚኒስትሩመከላከያ ምስክር ሆነው ፍርድ ቤት ቀረቡ

በመከላከያ ምስክርነት ለተቆጠሩትቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝናቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ ፌዴራል ፖሊስ አስፈርሞ የሰጣቸውን የፍርድ ቤት መጥሪያ ለምስክሮቹ አላደረሱም ወይም ፍርድ ቤት ቀርበው አላስረዱም የተባሉ የተቋማት ኃላፊዎችን፣ የፌዴራል ፖሊስ አስሮ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ሰኞ ሐምሌ 26 ቀን 2013 .. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ትዕዛዝ የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀሎች ችሎት ሲሆን፣ ከሁለት ዓመታት በፊት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋንይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ክስ ተመሥርቶባቸውና በዓቃቤ ሕግ ምስክር ተሰምቶባቸው እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡ በመሆኑም በመከላከያ ምስክርነት ከቆጠሯቸው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል  የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሸዴ አንዱ ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ከባለቤታቸው ጋር በጋራ ላቋቋሙትሮማንና ኃይለ ማርያም ፋውንዴሽንጽሕፈት ቤት ኃላፊ መጥሪያ የተሰጠ ቢሆንም፣ መጥሪያው ደርሷቸው ይሁን ወይም ሳይደርሳቸው ባልታወቀ ሁኔታ ፍርድ ቤት ቀርበው ሊመሰክሩ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትርና አሁን በኢጋድ (IGAD) የሰላምና ፀጥታ ዲቪዥን ዳይሬክተር ሆነው እየሠሩ ለሚገኙት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ የፍርድ ቤት መጥሪያ እንዲደርሳቸው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተደጋጋሚ የተሰጠ ቢሆንም፣ ምስክሩ ይድረሳቸው ወይም አይድረሳቸው ባለመታወቁ ሊቀርቡ አለመቻላቸው ተገልጿል፡፡

ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 26 ቀን 2013 .. ምስክሮቹ ሊቀርቡ ባለመቻላቸው የሮማንና ኃይለ ማርያም ፋውንዴሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደግሞ የሚመለከተውን ኃላፊ የፌዴራል ፖሊስ ለነሐሴ 7 ቀን 2013 .. አስሮ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በቀድሞው የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው መከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት አቶ ኃይለ ማርያምና አቶ ሲራጅ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቅ የነበረው፣ ከእርሻ ትራክተር መለዋወጫ ግዥ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ነው፡፡

ሌላው በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሲሆኑ፣ ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በተከሰሱበት የእርሻ ትራክተር  መለዋወጫ ግዥን  በሚመለከት  የገንዘብ ሚኒስትሩ እንዳስረዱት፣ ..አ. 2014 ኢትዮጵያ ከፖላንድ መንግሥት ብድር በማግኘቷ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትርነበሩት አቶ ኃይለ ማርያም ከተመራዑክ ጋር ወደ ፖላንድ ተጉውዘው ነበር፡፡ ብድሩ የተፈቀደውእርሻ ትራክተር መለዋወጫ መግዥያ ሲሆን፣ ግዥውን ለመፈጸም ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣት እንደማይቻል ሁለቱ መንግሥታት መስማማታቸውንና ስምምነቱም በካቢኔና በፓርላማ መፅደቁንም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ግዥው የሚፈጸመው ከፖላንድ የመንግሥት ልማት ድርጅት እንደሆነ፣ የፖላንድ መንግሥት በብድር ከሰጠው 50 ሚሊዮን ዶላር ክፍያው እንዲፈጸም መስማታቸውንና ምንም ዓይነት ገንዘብ በጥሬው እንዳልተሰጠ እንደሚያውቁም ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አክለዋል፡፡ በወቅቱ ወደ ፖላንድ ከተጓዘው ልዑክ ጋር የመከላከያ ሚኒስትርና የሜቴክ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ሲራጅ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡

ገንዘቡ እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ወለድ የብድር ስምምነት የተገኘ መሆኑን፣  ከፖላንድ መንግሥትኢትዮጵያ በጥሬ ገንዘብ የተሰጠ ገንዘብ እንዳልነበረ ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...