የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ፣ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ባለፈው እሑድ ነሐሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. መጠናቀቁን ባወጁበት ሰዓት ለኦሊምፒያኖች የተናገሩት፡፡ ለዐሥራ ስድስት ቀናት በተካሄደው 32ኛው ኦሊምፒያድ 205 አገሮችና ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች፣ የስደተኞች ቡድን ተሳትፈውበታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን በየዐራት ዓመቱ የሚመላለሰውን የኦሊምፒክ ጨዋታ፣ የተስፋ ግጥሚያዎች የወንድማማችነትና የሰላም መገለጫዎች ሲሉም አግዝፈውታል፡፡