Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​የጤና ባለሙያዎች ትሩፋት በዘመነ ኮቪድ

​​​​​​​የጤና ባለሙያዎች ትሩፋት በዘመነ ኮቪድ

ቀን:

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የጤና ባለሙያዎች ፈተና ውስጥ ቢገቡም፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሕይወታቸውን በመሰዋት ጭምር አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በተለይም በአሁኑ ወቅት ያሉትን ችግሮች በመጋፈጥ የብዙ ሰዎችን ሕይወት መታደግ ችለዋል፣ እየታደጉም ይገኛል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ደፋ ቀና እያሉ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎችና ክብካቤ ሠራተኞች አቶ ጃንጥራር ዓባይና ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት የምሥጋናና የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዮሐንስ ጫላ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ሕይወታቸውን በመሰዋት የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡ የጤና ባለሙያዎች ምሥጋና ይገባል፡፡

ወረርሽኙ በስፋት እየተሠራጨ የሚገኘው በከተማዋ ላይ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፣ የጤና ባለሙያዎች በዘርፉ ላይ ያሉትን ችግሮች በመጋፈጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስረድተዋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባለፈ በወረርሽኙ ምክንያት የሚያጋጥሙ ችግሮች ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ የተናገሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጃንጥራር ዓባይ ናቸው፡፡

የጤና ባለሙያዎች ቅንጅት ፈጥረው በመሥራት የብዙ ዜጎችን ሕይወት መታደግ እንደቻሉ፣ ወረርሽኙ የበለጠ እንዳይስፋፋ ለማድረግ ከ2,000 በላይ የጤና ባለሙያዎችን በመቅጠር በትምህርት ቤቶች ላይ እንዲሠሩ መደረጉን አቶ ጃንጥራር አስታውሰዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩም ለዘርፉ ትኩረት በመስጠጥ አዲስ አበባን የጤና ማዕከል ቱሪዝም ለማድረግ እየሠራ መሆኑን፣ ይህም ወደ ውጭ አገር ወጥተው ሕክምና ለሚያደርጉ ዜጎች ቁጥርን ለመቀነስ የሚያግዝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡  

በሚሌኒየም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ አገልግሎት እየሰጠች ያለችው ሲስተር ሃና ሳምሶን እንደገለጹት፣ ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ወቅት የተለያዩ ችግሮች እንደገጠማቸው፣ በተለይም የኦክስጅን እጥረት መኖሩ አብዛኛውን ሕሙማን ለሞት ተዳርገዋል፡፡

በማዕከሉ የኦክስጅን እጥረት እንዳይኖር ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ እንደነበር ያስታወሱት ሲስተር ሃና፣ የጤና ባለሙያዎች ያላቸውን አቅም በማውጣት የኮቪድ-19 ሕሙማኖች እየረዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች እፍንፍን ባለ ሁኔታ ውስጥም ሆነው አገልግሎት መስጠታቸው የሚበረታታ መሆኑን፣ እሳቸውም በአንድ ወቅት በወረርሽኙ ተይዘው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከሌሎች በሽታዎች ሁሉ ለየት ያለ በመሆኑ፣ ሁሉም የሕክምና ባለሙያ ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን፣ በወረዳ አራት በአራብሳ ጤና ጣቢያ እያገለገለ የሚገኘው የጤና መኮንን አበጀ ሰለሞን ተናግሯል፡፡

በጤና ጣቢያው ላይም ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሚናገረው የጤና መኮንኑ፣ ይህንን መሠረት በማድረግና ያሉትን ችግሮች ሁሉ ወደ ጎን በመተው ወረርሽኙን ለመከላከል እየተሠራ መሆኑን አክሏል፡፡

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ታመነ አጫሞ፣ በኢትዮጵያ ወረርሽኙ ተከሰተ በተባለበት ጊዜ ለሕክምና የሚሆኑ ግብዓቶች እጥረት እንደነበር፣ ከዚያም አልፎ ለተጓዳኝ በሽታዎች የሚሆኑ መድኃኒቶች እጥረት መከሰቱን አስታውሰዋል፡፡  

ማኅበረሰቡ ለወረርሽኙ ትኩረት ባለመስጠቱ ምክንያት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንና ይህንንም ችግር ለመፍታት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ግንዛቤ መፍጠር እንደተቻለ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝም ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ከጤና ሚኒስቴርና ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሠሩ መሆኑን የገለጹት አቶ ታመነ፣ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅትም የመድኃኒት እጥረት እንዳለ አስረድተዋል፡፡

የመድኃኒት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ፣ ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ማኅበረሰቡ ራሱን ከወረርሽኝ በመጠበቅ ትልቅ ሚና መጫወት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

የኮቪድ-19 ምላሽ ለሰጡና በመከላከል ተግባር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የመንግሥትና የጤና ተቋማት እንዲሁም ማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የሚያገለግሉ የክብካቤ ሠራተኞች የዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...