Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየፌዴራል ፍርድ ቤቶች እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ተነገረ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች እስከ መስከረም 30 በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ ተነገረ

ቀን:

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሐምሌ 30 ቀን ጀምሮ ዝግ እንደሚሆኑ በአዋጅ የተደነገገ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቶቹ ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ፣ ከዜጎች መሠረታዊ መብቶችና ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸው ጉዳዮች ሊከሰቱ ስለሚችሉ፣ እነሱን  ለማስተናገድ እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 .ም. ድረስ በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማክሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2013 .ም. አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደገለጸው፣ ፍርድ ቤቶቹ በየዓመቱ ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዲስ በፀደቀው አዋጅ ቁጥር 1234/2013 በአንቀጽ 38 ተደንግጓል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቶች የዜጎች መብቶችን የሚያስከብሩ የፍትሕ ተቋማት በመሆናቸውና የፍርድ ቤት ውሳኔና ትዕዛዝ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ወቅታዊ ምላሽ መስጠት እንዲቻል፣ ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ መወሰኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቅዳሜ ነሐሴ 1 ቀን 2013 .ም.  እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 .ም. ድረስ በከፊል ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ፣  እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ውዝፍ መዛግብት ነፃ የማድረግ ፅኑ ዓላማቸውን ዕውን ለማድረግ በከፊል ዝግ የሚሆኑበትን ጊዜ በማራዘም፣ ከነሐሴ 16 ቀን 2013 .ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 .ም. በከፊል ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡ 

ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ ከዜጎች መሠረታዊ መብቶች፣ ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸው የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ  ሥነ ሥርዓት የሚታዩ እጅ ከፍንጅ ወንጀሎች፣ እንዲሁም ከቤተሰብ፣ ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሠረታዊ ጉዳዮች ይታያሉ፡፡

እንዲሁም ይግባኝ የተባለበት ጉዳይ ከመታየቱ በፊት የተላለፈው የእስራት ቅጣት ጊዜ የሚያልቅ ወይም በአመክሮ ከእስር መፈታት ውጤት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮች፣ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይነታቸውና አጣዳፊነታቸው የታመነባቸው ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች እንደሚስተናገዱ፣ ሪፖርተር ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ ዳኞች በመልካም ፈቃዳቸው የዕረፍት ጊዜያቸውን ተጠቅመው ለምርመራ፣ ለብይንና ለውሳኔ በቀጠሮ ወደ 2014 .ም. የተሻገሩ መዛግብትን የማጥራት ሥራ እንደሚያከናውኑጠቁሟል፡፡ በዚህም 1,494 ውዝፍ መዛግብት እልባት እንደሚያገኙ፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሦስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች 171,276 መዛግብት ዕልባት ማግኘታቸውን ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...