Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉ​​​​​​​አንዱ ችግራችን የፅንሰ ሐሳብ ልጠጣ የሚባለው ነው!

​​​​​​​አንዱ ችግራችን የፅንሰ ሐሳብ ልጠጣ የሚባለው ነው!

ቀን:

አንዳርጋቸው አሰግድ

ይህንን ሑፍ ለማዘጋጀት የተነሳሳሁት በሁለት ምክንያቶች ነው። አንደኛ በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ ‹‹ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያን እንዳትሆን ያሠጋ (እንዲያውም) ትሆናለች›› የሚለው አመለካከት ለስንተኛ ጊዜ እንደገና ነፍስ ዘርቶ ሲደጋገም ሰነበተ። ሌሎች ‹‹ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያ አይደለችም›› እያሉ አመለካከቱን ሲያፋልሱ ከረሙ። ኢትዮጵያና ዩጎዝላቪያ ምንና ምን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ጫረብኝ። ስለዚህም የዩጎዝላቪያ መንግሥት አመሠራረት ከኢትዮጵያ መንግሥት አመሠራረትና ታሪክ ጋር ያለውን ልዩነት ለማስታወስ ያህል ብቻ ስለዩጎዝላቪያ መንግሥት አመሠራረት ክንዋኔ በአጭሩ ለመከለስ አሰብኩ። ሁለተኛ በቤልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ሩት ዘመነ ዝቅ ሲል በማነሳው ሑፋቸው ለአንድ ባሮኔስ አርሚንካ ሊች ለተባሉት ሴትዮ ሲመልሱ ‹‹የተሳሳት አመለካከት በፅንሰ ሐሳብ ረድም ሆን ተብሎ እተለጠጠ ይሠራጫል›› ብለው ያሉት ቁምነገር የኢትዮጵያ የፖለቲካ (የሥልጣን) ልሂቃንስ በፖለቲካ ሳይንስ የፅንሰ ሳብ ልጠጣ (Concept Stretching or Straining) እየተባለ በሚገለው ምልከታ እየተጧጧዙ በሥርዓት ለመወያየት እንኳን የተቸገሩ ፍጡራን አይደሉም ወይ? የሚለውን ጥያቄ ጫረብኝ። በጥቂቱ ልመለስበት አሰብኩ።

‹‹ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያን እንዳትሆን ያሠጋል (እንዲያውም) ትሆናለች›› የሚለው አመለካከት በኢሕአዴግ አገዛዝ ላይ ጠጠር ያለ ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር አንዳንድ የድርጅቱ አመራሮቹ ሲደጋግሙት የነበረ አመለካከት ነው። መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም. ሲያርፉም ‹‹ተተንብዮ›› ነበር። ኢሕአዴግ በ2010 ዓ.ም. ከሥልጣን ሲወርድም ሰሞነኛ ሆኖ ነበር። ፍሎራልን ብሬበርና ወንድምአገኝ ታደሰ ገብሩ የተባሉ ግለሰቦችም፣ የውጭ ፖሊሲ (Foreign Policy) በሚባለው የአሜሪካ መሔት ላይ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም. (January 152019) ‹‹ኢትዮጵያ የሚቀጥለው ዩጎዝላቪያ እንዳትሆን ተከላከሉ›› እያሉ አንድ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አዘል ሑፍ አሳትመው ነበር (https://foreignpolicy.com/2019/01/15/dont-let-ethiopia-become-the-next yugoslavia-abiy-ahmed-balkans-milosevic-ethnic-conflict-federalism/)።  

አሁን የሰሜኑ ጦርነት በጥቅምት 2013 ዓ.ም. ከተነሳ ወዲህ ደግሞ የኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያን የመሆን ዕጣ እየተደጋገመ መነሳሳያዘ። የተጠቀሰው የአሜሪካ የውጭ ፖሊሲ ሔት ገና ታኅ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. (December 31, 2020) ‹‹ኢትዮጵያ የሚቀጥለው ዩጎዝላቪያ ናት ወይ?›› በማለት ጠይቆ ተነበበ። ወደ ሐምሌ መጨረሻ ሲደረስ ምናልባትም ማንታ ፓወር የተባሉት የአሜሪካ አስተዳደር ባለሥልጣን ወደ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ለማጀብ ይሆናል የኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያን የመሆን/አለመሆን ዕጣ ሰሞነኛ ሆኖ ሰነበተ።

የሐምሌ ወር መጨረሻ ቀናት ትርክት የቀደሱት አንዲት የቦዝኒያ ርዞ ጎቪና ተወላጅ የነበሩና በአንድ ወቅት የእንግሊዝ መንግሥት የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ለመሆን የበቁት ባሮኔስ አርሚንካ ሊች የሚባሉት ሴትዮ ናቸው። ሴትዮዋ ሐምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. (August 2, 2021) ‹‹የዩጎዝላቪያ የገደል ማሚቱ በኢትዮጵያ ምድር እየጮኸች ነው›› (Ethiopia Echos from Yougoslavia) በሚል ርዕስ አንድ ሑፍ አሠራጩ (https://www.davidalton.net/2021/08/04/baroness-arminka-helic-warns-that-in-ethiopias-war-in-tigray-there-are-echoes-of-yugoslavia-and-says-in-the-1990s-as-yugoslavia-was-torn-apart-western-nations-proved-unwilling-to/)።

ሳቸው ምላሽ ለመስጠት ይመስላል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ና ሐምሌ 28 ቀን፣ ‹‹ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያ አይደለችም›› በማለት አንዲት አጭር መልዕክት ትዊተር ገቸው ላይ ለቀቁ። ልጂየም የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ወ/ሮ ሒሩት ዘመነም፣ ለባሮኔሷ በቀጥታ በመመለስ ንድ እጥር ምጥን ያለ መልስ አቀረቡ (https://www.fanabc.com/english/ethiopia-is-not-yugoslavia/)።

‹‹ነገር ነገሩ ምድነው? ዩጎዝላቪያና ኢትዮጵያ ምንና ምን ቢሆኑ ነው? ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያን እንዳትሆን ያሠጋል (እንዲያውም) ትሆናለች›› እየተባለ እስከዚህ ተደጋግሞ የሚነሳውና ተደጋግሞ የሚነገረው? በሌላ መንገድ ለመጠየቅ የአመለካከቱ አራማጆች የቱን ያህል ቢጠበቡልንና ቢጨነቁልን ነው ‹‹! ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትሆናለች›› እያሉ የሚያሳስቡን? ወይስ ኢትዮጵያን ዩጎዝላቪያ እንደሚያደርጓት አስቀድመው እያሳወቁን ናቸው? ወይስ ደግሞ ከአሁኑ ነግረናችሁ ነበር እያሉን ነው ወይ?

ኢትዮጵያና ዩጎዝላቪያ ምንና ምን ናቸው?

ኢትዮጵያ ‹‹ትፈርሳላች›› እና ‹‹ትበታተናለች›› የሚለው አመለካከት አብሮን የኖረ አመለካከት ነው። ወይም ኢትዮጵያ በሆነ የሽግግር ወቅት ከፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በገባችበት ዘመን ሁሉ ሲስተጋባ የኖረ አመለካከት ነው። በዮዲት ዘመን ተብሎ ነበር። በ16ኛው ክፍለ ዘመን የክርስቲያንና የእስላም ኢትዮጵያ ጦርነቶች ዘመን ተብሎ ነበር። በዘመነ መፍንት የመቶ ዓመታት ጦርነት ዘመን ተብሎ ነበር። በድዋ ዘመን ተብሎ ነበር። አፄ ምኒልክ በጠና በታመሙባቸው ዓመታት ተብሎ ነበር። በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ዘመን ተብሎ ነበር። አፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ ተብሎ ነበር። ኮኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ወደ ዚምባዌ ሲሸሹ ተብሎ ነበር።

ስለዚህም አሁን ከሰሜኑ ርነት ጋር ተያይዞ መደጋገሙ ሊያስገርም አይገባም። የሚያስገርም ነገር ቢኖር አሁን በተለይም ማንታ ፓወር ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት አንድ የአሜሪካና አንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ በአንድ ጊዜና በአንድ ጉዳይ ላይ በአንድ ዓይነት ርዕስ ተመሳሳይ አመለካከት መያዛቸውና ማሠራጨታቸው ነው። ታሪኩን መለስ ሎ ያስተዋለ ማንም ኢትዮጵያዊም ሁለቱ አምባሳደሮች ‹‹ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያ አይደለችም›› እያሉ ያስተጋቡትየአገሩ ታሪክ ነባራዊ እውነታ መሆኑን ሊስተው አይችልም፡፡

ባሮኔሷ ‹‹የዩጎዝላቪያ የገደል ማሚቱ በኢትዮጵያ ምድር እየጮኸች ነው›› እያሉ ለፉት፣ አምባሳደር ቲቦር ና የሁለቱን መንግሥታት ዕድሜ ቆጥረው እንደሚከተለው በአጭሩ መልሰውላቸዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትናዳለች የሚሉት ክፍሎች ተሳስተዋል። ዩጎዝላቪያን የፈጠሯት የመጀመያው ዓለም ጦርነት አሸናፊ ኃይሎች ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን በሁለት ሺ ዘመን የታሪክ ክንዋኔ የተገነባና ብዙ ቀውሶችን የተሻገረ መንግሥት ነው፤›› ነው ያሉት፡፡  

አምባሳደር ሩት ዘመነ ለባሮኔሷ ሑፍ ሲመልሱ የባሮኔሷን አጉል ንፅፅር እንደሚከተለው አጣጥለውታል፡፡ ‹‹የባሬኔሷ አመለካከት በተጨባጭም ይሁን በፅንሰ ሐሳብ ደጃ ሆን ተብሎ በተሳሳት አስተሳሳብ ላይ የተመሠረተ ነው። ባሬኔሷ ኢትዮጵያን ከዩጎዝላቪያ ጋር ለማመሳሰል በሚደርጉት ጥረት የኢትዮጵያን ማኅበራዊፖለቲካ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ምንነት ሊረዱ አልቻሉም፤›› በቂ መልሶች ናቸው። ለማስታወስ ያህል ብቻ በሚከተለው ክፍል ስለዩጎዝላቪያ መንግሥት አመሠራረት ታሪክ በአጭሩ እከልሳለሁ።

ስለዩጎዝላቪያ መንግሥት

አምባሳደር ቲቦር ና እንዳሉት፣ የመጀመያው የዓለም ጦርነት የሚባለው በ1910 ዓ.ም. (1918) ከማብቃቱ በፊት፣ የዩጎዝላቪያ መንግሥት የተባለ መንግሥት አልነበረም። ሁለተኛም ስለአመሠራረቱ የሚያጠኑ የፖለቲካ ታሪክ ተመራማሪዎች የዩጎዝላቪያን መንግሥት አመሠራረት ክንዋኔ የሚያትቱት በሦስት ወቅቶች ለያይተው የመጀመሪያው፣ ሁለተኛውና ሦስተኛው የዩጎዝላቪያ መንግሥት እያሉ ነው። የመጀመያው የዩጎዝላቪያ መንግሥት የተመሥረተው የመጀመያው የዓለም ጦርነት የሚባለው እንዳበቃ ነበር። ጦርነቱ እንዳበቃ ‹‹የፓሪስ ሰላም ጉባዔ›› የተባለው የጦርነቱ አሸናፊ ኃይሎች ጉባዔ በ1911 ዓ.ም. (1919) በፓሪስ ተካሄደ። በጉባዔው ውሳኔ መሠረት ከተሸናፊው የኦስትሪያ ንጋሪ አፄያዊ ግዛት ተቆርጦና ሰርቢያን፣ ሞንቶኔግሮን፣ ክሮአትን፣ ቦስኒያንና ርዞጎናን አካቶ አንድ የዘውድ አገዛዝ መንግሥት ተመሠረተ። አሌክሳንደር አንደኛው የሚባሉት ንጉሥ በ1921 ዓ.ም. (1929) በደነገጉት አዋጅ ግዛታቸውን ዩጎዝላቪያ ብለው ሰየሙ። ስያሜው ዩግ (ድቡብ) እና ስላቪያ ከሚሉት ሁለት የስላቪክ ቃላት ተውጣጥቶ የተቀመረ ነው። ደቡብ ስላቪያ ማለት ነው።

የመጀመርያው የዩጎዝላቪያ መንግሥት ለ22 ዓመታት ዘለቀ፡፡ ይሁንና መሥራቹ ንጉሥ አሌክሳንደር አንደኛ በመስከም 1927 ዓ.ም. (1934) ፓሪስ ላይ ተገድሉ። ልጃቸው አልጋ ወራሽ ፔታር አልጋውን ወርሰ። ፔታር ገና የ11 ዓመት ሕፃን ስለነበር ግን ዩጎዝላቪያ እስከ በ1933 ዓ.ም. (1941) ድረስ በእንደራሴዎቹ ተዳደረች። ይሁንና እንደራሴዎቹ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከትለር ጋር በመግጠማቸው ምክንያት ዩጎዝላቪያ አክሲስ ፓወርስ በሚባሉት ኃይሎች ተይዛ የመጀመያው መንግሥቷ እንዲፈርስ ተደረገ። ከ1941 እስከ 1946 ዓ.ም. በነበሩት የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ዓመታትም፣ በጀርመን፣ በኢጣሊያ፣ በንጋሪና በቡልጋሪያ መንግሥታት ሥር ተሸንሽና ተስተዳደረች።

ሁለተኛው የዩጎዝላቪያ መንግሥት የሚባለው በ1938 .. (1946) ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላ ከኢጣሊያ ግዛት ስትሪያና ዲልማሲያ የተወሰኑ ክፍሎችን አክሎ በማርሻል ቲቶ ተመሠረተ። የዩጎዝላቪያ ሶሻሊስት ፌዴራል ሪፐብሊክ ተብሎ ተጠራ። ዩጎዝላቪያ በማርሻል ቲቶ ዘመን በአንፃራዊ ከፍተኛ ዕድገቶችን ያስመዘገበች ቢሆንምበተለይም በ1970ዎቹ ዓመታት የተከሰቱት የዋጋ መናር፣ ሥራ አጥነትና የምርታማነት ማሽቆልቆል በአገሪቱ አኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫናዎችን አሳረፉ። የዓለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ ላይ ገንዘብ ለማበደር ‹‹መዋቅራዊ ማስተካከያ›› የሚባለውን ፖሊሲውን በ1975 ዓ.ም. (1983) በጫነባት ጊዜ የፖለቲካ፣ የአኮኖሚና የማኅበራዊ ውቅሯ እያደር ተናጋ። የፖለቲካ ለውጥ ጥያቄዎች ተጠናክረው እስከሚነሱ ድረስ የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነበር።

ነገሮች በዚህ እንዳሉ የሁለተኛው ዩጎዝላቪያ መንግሥት መሥራች ማርሻል ቲቶ በሚያያ 1972 ዓ.ም. (May4, 1980) ረፉ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለማለትም ይቻላል፡፡ ዩጎዝላቪያ ወደ እርስ በርስ ፍትጊያና አሰቃቂ ጦርነቶች አመራች። የሶቪየት ብረት መፍረስና የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት በዚህ ላይ ታክሎ ሁለተኛው የዩጎዝላቪያ መንግሥት ፈራረሰ። ይህም 1983 እስከ 2000 .. (1991 እስከ 2008) ወደ አካሎቶቿ የተበታተነችው ዩጎዝላቪ የዩጎዝላቪያ መንግሥት ፍሜ ታሪክ ነው። ወይም በማርሻል ቲቶ ዩጎዝላቪያ ፍርስራሽ ላይ የተመሠረተው የሦስተኛው ዩጎዝላቪያ መንግሥት ታሪክ መጀመያ ነበር።

ስለሦስቱ የዩጎዝላቪያ መንግሥታት አመሠራረት ታሪክ ባጭሩ የከለስኩት ኢትዮጵያና ዩጎዝላቪያ በምንም የማይመሳ የመንግሥት አመሠራረትና ክንዋኔ ታሪኮች ባለቤት መሆናቸውን በመጠኑ ያመለከተ ይመስለኛል። ስለዚህም በዚህች ሑፍ ወደ ረሙ ዘመን የኢትዮጵያ መንግሥት አመሠራረትና ክንዋኔው ላይና በኢትዮጵያ ማኅበራዊፖለቲካና ባህላዊ ምንነት ላይ ሆ ኢትዮጵያ በታሪኳ በተሻገራቸው በርካ የሽግግር ወቅት የፖለቲካ ቀውሶች ላይና በኢትዮጵያያን የዘመናት መስተጋብሮችና የጋራ ትውስታዎች (Shared Memories) ላይ ተመልሼ ነገር ማራዘም የሚያስፈልገኝ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያያን ለስንተኛ ጊዜ እንደ አንድ ሰው ቆመው ለአገራቸው ሉዓላዊነት፣ ለማንነታቸውና ለነፃነታቸው ያደርጓቸውን የጋራ ትግሎችንና ድሎችንም መዘርዘር አስፈልገኝም፡፡ እንደዚሁም ስለአትንኩኝ ባይነት የጋራ ልቦና ውቅራችን በአጭሩ ለመግለያህል ዝቅ ሲል የምጠቅሳቸው ሳርቶሪ እንዳሉት ‹‹ድንጋይንና ጥንቸልን ለማነፃፀር›› የመጣርን ያህል ይሆንብኛል። ስለዚህም ከፍ ሲል የኢትዮጵያ የፖለቲካ (የሥልጣን) ልሂቃንስ በፅንሰ ሳብ ልጠጣ እየተጧጧዙ በአግባቡ ለመወያየት የተቸገሩ ፍጡራን አይደሉም ወይ? በሚል ወዳቀረብኩት ጥያቄ ተመልሼ አንዳንድ አስተያየቶችን በማቅረብ እወሰናለሁ።

ስለፅንሰ ሳብ ልጠጣ

ስለፅንሰ ሳብ ልጠጣ ደጋግመው የፉት ሳርቶሪ እንደሚሉት፣ ‹‹የፅንሰ ሳብ ልጠጣ የማኅበራዊ ፖለቲካ ጉዳዮችን አረዳድ ሆን ሎ እሴት አልባ አድርጎ ለመርዳት የሚደረግ ጥረት ነው››፡፡ሳቸው ቃል ‹‹Conceptual Stretching (Also) Represents a Deliberate Attempt to Make Our Conceptualizations Value Free›› (Giovanni Sartori Concept Misformation in Comparative Politics 1970)።

ማይምሬ መናሰማይ የሳርቶሪን ሌላ ሑፍ ጠቅሰው እንዳሉት ደግሞ፣ ‹‹አንድ ፅንሰ ሳብ የሚለጠጠው የሚሸፍነው መደባዊ (Original) ትርጉም ወዲያ ተጥሎና ተጨማሪ ሌሎች ጉዳዮችን እንዲሸፍን ለማድረግ ሆን ተብሎ ሲለጠጥና በሥራ ላይ ሲውል ነው። በውጤቱ ለጊዜው (የፖለቲካ) ትርፍ ያስገኝ ቢመስልም የመጨረሻ መጨረሻ ስለነገሮች ሊኖር የሚገባውን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ትክክለኛ አዳድና ግንዛቤ የሚያኮስስ ይሆናል፤›› በማይምር ቃል ‹‹Concept stretching is the practice of discardingelements constitutive of the original meaning of the concept in order tomake it cover more cases than the original meaning allows. The result is athin conceptualization that provides ‹‹gains in extensional coverage›› butgenerates ‹‹losses in connotative precision›› (Maimire Mennasemay The Horn of Africa as a Democratic Project: Some Conceptual Issues 2007).

አስከትለንም ለማለት ይቻለናል በኢትዮጵያ የፖለቲካ ዓለም ውስጥ በፅንሰ ሳቦች ረገድ የሚፈመው ልጠጣ አንደኛው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ (የሥልጣን) ልሂቃን ከፍተኛ ችግር ነው። የኢትዮጵያ የፖለቲካ (የሥልጣን) ልሂቃን ፅንሰ ሳቦችን እየለጠጡ የማይናጩበት አንድም የፖለቲካ ፅንሰ ሳብና ቃል የለም ብንልም ውነታ ነው። እንዲያም ሲል የአገራዊው ታሪክ ሆነ የብሔሮች ታሪክ አተራረክ የሞክራሲ ሆነ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የዜጋ ሆነ የቡድን መብትየገበያ ኢኮኖሚ ሆነ መንግሥታዊ ካፒታሊዝምወዘተ. ከመደባዊ ይዘቱና ትርጉሙ በላይ እየተለጠጠ የማያናጩበት አንድም ፅንሰ ሳብ ያለ አይመስልም፡፡

በሚለጠጡት ፅንሰ ሳቦች ላይ ሁሉ መመለስ መንዛዛት ይሆናል። ስለዚህም በአንድ ሁለት ጉዳዮች ላይ ብቻ ተወስኜ የልጠጣውን መጠንና ጉዳቱን ለማመለከት እሞክራለሁ። ለዚህም ሩቅ መሄድና መዘባዘብ አይስፈልገኝም፡፡ እዚሁ ላይ ግን ደግሞ በአብዮቱ ዘመንም፣ ‹‹ፋሺስታዊ ሥርዓት ነገሠ›› እና ‹‹ባንዳ ምሁራን›› የሚሉት ፅንሰ ሳቦች ለመለጠጥ የሚቻላውን ያህል ተለጥጠውከኢሕአፓ አመራር ነጭ ሽብር እስከ ደርጉ የመንግሥት ሽብር (ቀይ ሽብር) ጭፍጨፋ ድረስ አድርሰው እንደነበርም ማስታወስ ይገባኛል።

ከ1983 ዓ.ም. ለውጥ በኋላ የኢትዮጵያ ብሔሮች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰንን መብት እንደተቀዳጁ በሕገ መንግሥት ጭምር ፀድቆ ታወጀ። ይሁንና ኢሕአዴግ ፅንሰ ሳቡን በርዕዮተ ለምም ሆነ በሥልጣንና በኢኮኖሚ ይዞታው ለጥጦ ለጥጦ ኢትዮጵያን የአንድ ድርጅት የግል ንብረት አድርጎ በሥራ ላይ አዋለው። በባላምራስ ገብረ ሕይወት ባይዳኝ ግሩም አባባል አተኩረን ብንመለከት ግን የአንድ ብሔር መብት እንደ ማንኛውም ሞክራሲያዊ መብት የሌላው ብሔር መብት ከሚጀምርበት ድንበር ላይ የሚቆም መብት ነው። በኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ዘመን ግን ተለጥጦ ተለጥጦ የብሔሮች መጋጫና ማጋጫ መብት ሆነ። ተለጥጦ ተለጥጦ በጥቅምት 2013 ዓ.ም. ከፈነዳው የሰሜን ኢትዮጵያ ውጊያ ያደረሰ መብት ሆነ።

ኢትዮጵያ ፌራል ሪፐብሊክ እንደሆነችም ታውጆ ነበር። ይሁንና የፌዴሬሽን ሥርዓት መደባዊ ትርጉም ተለጥጦ ተለጥጦ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከቀበሌ ቀበሌና ከጎጥ ጎጥ አንድ ለአምስት በተባለው አደረጃጀት ተጠርንፈው በአንድ ድርጀት የተማከለ አገዛዝ ሥር ለብዙ ዓመታት ተገዙ። ኢትዮጵያ በሞክራሲያዊ ምርጫ በተመረጠ አስተዳደር ብቻ እንደምትተዳደር በሕገ መንግሥት ጭምር ተደንግጎም ነበር። ይሁን እንጂ አንድ ድርጅት የምክር ቤቱን መቀመጫ ሙሉ በሙሉ እየጠቀለለ ጭምር እስከሚሸፍበት ድረስ የተለጠጡ ‹‹ምርጫዎች›› እየተካሄዱ ዓታት ተቆጠሩ። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚም በመጀመያ በገበያ ኢኮኖሚና በኋላም በመንግሥታዊ  እንደሚመራ ተነገሮ ነበር። ይሁንና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ‹‹የመንግሥት ፓርቲ ካፒታሊዝም›› በሚባለው ሥሪት ተለጥጦ ተለጥጦ በአንድ የመንግሥታዊ ፓርቲ ድርጅት ካፒታሊዝም ለብዙ ዓመታት ሙሉ ተሄደበት፡፡

ለማጠቃለል

ቀደም ሲል ‹‹ኢትዮጵያን ለማሻገር›› በሚል ርዕስ ባቀረብኩት አንድ ሑፍ ‹‹ብሔራዊ የምክክርና የአሻጋሪ ፖለቲካ መፍትሔ ምክረ ሐሳቦች አፍላቂ ጉባዔ›› መቋቋም አስፈላጊ መሆኑን አመልክቼ ነበር፡፡ ጉባዔው በሥርዓት የሚቋቋምና የሚሠራ ከሆነ በሳርቶሪ አገላለጽ፣ ‹‹በዕውቀት ላይ የተመሠረተን ትክክለኛውን የፅንሰ ሳብ ዳድና ግንዛቤ ያኮስሰውን›› የኢትዮጵያን የፖለቲካ (የሥልጣን) ልሂቃንን የፅንሰ ሳብ ልጠጣ ጉዳይና መዘዙን አካቶ ጭምር የሚወያይ ቢሆን መልካም ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...