ከሁለት ሳምንታት በላይ በዘለቀው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ተሳትፎ በ1 ወርቅ፣ 1ብር እና 2 ነሐስ ሜዳሊያዎች የተመለሱት አትሌቶች ነሐሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ከኤርፖርት በኋላ ወደየቀያቸው ካመሩት መካከል የወርቅ ሜዳሊያ ባለድሉ ሰሎሞን ባረጋ ቤተሰቡና ኅብረተሱ በመኖርያ ቤቱ በደማቅ ሥርዓት ተቀብሎታል፡፡ ፎቶዎቹ የአቀባበሉን ገጽታ በከፊል ያሳያሉ፡፡