Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል​​​​​​​‹‹ሩብ ጉዳይ›› ቴአትር ከእሑድ እስከ እሑድ ሊመረቅ ነው

​​​​​​​‹‹ሩብ ጉዳይ›› ቴአትር ከእሑድ እስከ እሑድ ሊመረቅ ነው

ቀን:

‹‹ሩብ ጉዳይ›› የተሰኘው ቴአትር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትርና በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡

በቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ ተደርሶ፣ በተፈራ ወርቁ የተዘጋጀው ‹‹ሩብ ጉዳይ›› ቴአትር፣ ከነሐሴ 9 እስከ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚመረቅባቸው ቦታዎች በቅደም ተከተል በብሔራዊ ቴአትር፣ በዓለም ሲኒማ፣ በአዶት ሲኒማና በአምባሳደር ቴአትር ናቸው፡፡

በሩብ ጉዳይ ኮሜዲ ቴአትር የሚተውኑት ታዋቂ ተዋንያን ሳምሶን ታደሰ፣ ሸዊት ከበደ፣ ሕይወት አራጌ፣ ትዕግስት ዓለሙና ሔኖክ ብርሃኔ ሲሆኑ የዝግጅት አስተባባሪው ተስፋዬ ጌታቸው ነው፡፡

ተስፉ የኪነ ጥበብ ኢንተርፕራይዝ እንዳስታወቀው የመክፈቻና መዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይከናወናል፡፡

ከምርቃቱ ባሻገር ‹‹ክብር ለቴአትር – ምስጋና ለመድረክ ባለሙያዎች›› በሚል መሪ ቃል፣ ለቴአትር ጥበብ አስተዋጽኦ ያደረጉ ባለሙያዎች በየቀኑ በሚኖረው ሥነ ሥርዓት ዕውቅና ይሰጣቸዋል፡፡

በተጨማሪም በሕይወት የሌሉ የቴአትር ባለሙያዎች በየቀኑ ከተለያዩ ዘርፎች ማለትም በድርሰት፣ በዝግጅት፣ በትወና ያደረጉትን አስተዋጽኦ በመተንተን እንዲታወሱ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

የተውኔቱ ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ በቅርቡ ያሳተሟቸው የፍልስምና ተከታታይ መጻሕፍት በ40 በመቶ ቅናሽ ለሸመታ እንደሚቀርቡም ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...