Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ እንደገና ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ እንደገና ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

ቀን:

የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከወራት በፊት የተሾሙት አንጋፋው ዲፕሎማት ጄፍሪ ፈልትማን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየትና የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ፣ እንደገና ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ልዩ መልዕክተኛው ከነሐሴ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. አንስቶ እስከ ነሐሴ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በሚኖራቸው ቆይታ ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ እንዲሁም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን እንደሚጎበኙና ከአገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በቀጣናው ሰላምና ደኅንነት ስለሚረጋገጥበት ሁኔታ እንደሚወያዩ አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ልዩ መልዕክተኛው ወደ ተጠቀሱት አገሮች እንደሚያቀኑ ከመግለጽ ባለፈ፣ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የጉዟቸው ዋነኛ ማጠንጠኛ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው ወደ ቀጣናው የሚያደርጉትን ጉዞ ባስታወቁበት የትዊተር መረጃቸው የደኅንነት አማካሪው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ፣ ‹‹ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው፤›› የሚል ጥሪም አስተላልፈዋል፡፡ የልዩ ልዑኩ የጉዞ ዓላማም ይህን ለማሳካት ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ የቀድሞ አምባሳደር፣ እንዲሁም የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ በበኩላቸው፣ ለፈልትማን በጉዟቸው የስኬት ምኞት ከማስተላለፍ ባለፈ ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች ጦርነት የሚያደርሰውን ውድመትና መከራ ተረድተው ለሰላም ዝግጁ እንደሚሆኑ፣ ሁሉንም ዓይነ ሥውር ከሚያደርገው ‹ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጥፋ› የፍርድ አካሄድ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከወራት በፊት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት አንጋፋው ዲፕሎማት ወደ ቀጣናው የሚያደርጉት ይህ ጉብኝት ለሦስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ከሚያዝያ ወር ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡

ዲፕሎማቱ በሚያዝያ ወር በሱዳን፣ በግብፅ፣ በኤርትራና በኢትዮጵያ ከሳምንት በላይ የዘለቀ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በተመሳሳይ እንዲሁ በኳታር፣ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ እንዲሁም በኬንያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በእነዚህ ጉብኝቶች ወቅት እየሰፋ ከመጣው የፌዴራል መንግሥትና የሕወሓት ጦርነትና ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚደርስበትን ሁኔታ ከመወያየት በተጨማሪም፣ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ስላለው የድንበር ውዝግብ መወያታቸው ይታወሳል፡፡

ጄፍሪ ፈልትማን ለበርካታ ዓመታት አሜሪካን በዲፕሎማሲ መስክ ያገለገሉ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በሊባኖስ የአሜሪካን አምባሳደር ሆነው ሠርተዋል፡፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የመካከለኛው ምሥራቅ ረዳት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆንም አገልግለዋል፡፡ ከእነዚህ አገልግሎቶች በኋላ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፖለቲካ የፀጥታ ኃላፊ ሆነው አመሥራታቸው አይዘነጋም፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...