Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርት​​​​​​​ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቶኪዮ የተጠበቀው ውጤት ያልተሳካው በተለያዩ ተቋማት ጣልቃ ገብነት ምክንያት መሆኑን...

​​​​​​​ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቶኪዮ የተጠበቀው ውጤት ያልተሳካው በተለያዩ ተቋማት ጣልቃ ገብነት ምክንያት መሆኑን ገለጸ

ቀን:

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በነበራት ተሳትፎ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲጠበቅ የነበረውን ያህል ውጤት ማምጣት አልቻለችም። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ሲጠቀሱ ቢከርምም፣ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መካከል የነበረው አለመግባባት የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ እሙን ነው።

የቶኪዮ ኦሊምፒክ ከመዳረሱ አስቀድሞ በውዝግቦች የታጀበው ዝግጅቱ፣ ከአትሌቶች ምርጫና ተያያዥ ጉዳዮች ጥያቄ ሲያስነሳ መቆየቱ ይታወሳል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተለያዩ ጊዚያት መግለጫ ሲሰጥ ቢቆይም፣ በአንፃሩ በኦሊምፒክ ኮሚቴ በኩል ማብራሪያ ማግኘት አልተቻለም ነበር።

ረቡዕ ነሐሴ 12 ቀን 2013 .ም. የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (/)፣ ከጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴና ከቦርድ አባላት እንዲሁም በቶኪዮ ከተገኙ የሕክምና ባለሙያዎች ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዕለቱ የኦሊምፒክ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት፣ ሕዝብና መንግሥት በደከሙት ልክ እንዲሁም በሚጠበቀው ደረጃ ውጤት ባለማግኘቱ ይቅርታ እንጠይቃለን በማለት መግለጫቸውን ጀምረዋል።

ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ላይ ተሳትፎ ማድረግ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ አትሌቶችን በውድድሩ ከማሳተፍ ባለፈ፣ በመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ወቅት በዓለም አደባባይ በአገር ባህል ባጌጡ አትሌቶች አሸብር ባንዲራዋን ማውለብለብ የገጽታ ግንባታ ላይ ስትሰማራ ቆይታለች፡፡ ሆኖም በቶኪዮ ኦሊምፒክ ይሄን ማድረግ ባለመቻሉ፣ በርካቶችን ያስቆጣ አጋጣሚ ሆኖ አልፏልል። የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን በተመለከተ  ለምን ቀድሞ መሰናዳት እንዳልተቻለ ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበለት የኦሊምፒክ ኮሚቴው፣ የተፈቀደለት የሰው ቁጥር ስድስት ብቻ እንደነበርና ቁጥሩ አገር ከማስተዋወቅ አንፃር  ልዩነት እንደሌለው በመጥቀስ  አሸብር (/) ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

‹‹በመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እንድናሳልፍ የተፈቀደልን ስድስት ሰው ነው። በዕለቱ ባንዲራ ይዘው የገቡት ላይ አራት ሰው ብንጨምር፣ 200 ሰው ይዘው ከተጓዙት ጋር እኩል ልንሆን አንችልም። ስለዚህ አገር ዝቅ አለች ማለት አይድለም›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በዕለቱ ባንዲራ ሊይዙ የሚችሉ አትሌቶች ባለመኖራቸውና የቀድሞ አትሌቶች ባንዲራው እንዲይዙ ጥያቄ ቢቀርም ፈቃድ አለመገኘቱን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በቶኪዮ ከተገኙ ልዑካን መካከል መያዝ የሚችሉት በማርፈዳቸው አልተሳካም ብለዋል፡፡

በአንፃሩ የኦሊምፒክ ኮሚቴው ጽሕፈት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ባቀረቡት የሪፖርት ላይ ማንኛውም ኦፊሻልም ሆነ፣ አትሌት ከተቀመጠበት የኦሊምፒክ መንደርና ሆቴል በሕዝብ ትራንስፖርት መንቀሳቀስ እንደማይችል ጠቅሰዋል።

ከዚህ ቀደም ወደ ኦሊምፒክ የሚያመሩ የተመረጡ አትሌቶችና ልዑካን ቡድን መቼ እንደሚያመሩ መግለጽ የተለመደ ነበር። በዘንድሮ ኦሊምፒክ የስም ዝርዝራቸው በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከተጠቀሱ አትሌቶችና የሕክምና ባለሙያዎች ከአየር ማረፊያ መመለሳቸው በርካታዎችን ያነጋገረ ጉዳይ ነበር።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ለምን ወደ ሥፍራው የሚያመራውን አትሌት እንዲሁም ልዑክ አስቀድሞ ማሳወቅ አልተቻለም የሚለው ሌላኛው የሪፖርተር ጥያቄ ነበር። ሆኖም ፕሬዚዳንቱ ከአየር ማረፊያው የተመለሰው የተጠራው አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።

‹‹የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መሥራት የሚገባውን፣ ማስረከብ የሚገባውን ለሚመለከተው የባለድርሻ አካል ቆጥሮ አስረክቧል። እኛ ሯጭ አይደለንም ገብተን አንሮጥም፣ አሠልጣኝ አይደለንም ገብተን አናሠለጥንም። በጉባዔው የተሰጠንን ኃላፊነት ተወጥተናል፤›› በማለት የኦሊምፒክ ኃላፊነት ነው ያሉትን ጉዳይ አብራርተዋል።

ምንም እንኳን ፕሬዚዳንቱ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሚመለከተውን ጉዳይ ቢያብራሩም እንዲሁም የመጨረሻ የተመረጡ አትሌቶችን ዝርዝር (Short list) የመላክ ኃላፊነት የኦሊምፒኩ ቢሉም፣ ማብራሪያቸውን የሚፃረር አስተያየት በኦሊምፒክ ቦርድ አባሉ ተገልጿል።

‹‹አትሌቶችን አዘጋጅቶና መርጦ ማዘጋጀት የኦሊምፒክ ሥራ አይደለም። ኦሊምፒክ ኮሚቴ የድጋፍና የማመቻቸት ሥራ ነው የሚሠራው፤›› በማለት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የቦርድ አባል ፍትሕ ወልደ ሰንበት (/) አስረድተዋል።

ሌላኛው ነጥብ የ3,000 ሜትር መሠናክል ሯጭ ሌሜቻ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ወርቅ ሊያመጣ ይችላል የሚል ጫና ሲደረግ መቆየቱንና የመጨረሻው ስም ዝርዝር ለዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዲተላለፍ መደረጉና ከሚመለከተው አካል ጋር ግልፅ የሆነ አሠራር ባለመኖሩ ለተከሰተው ክፍተት ኃላፊነት ላለመውሰድ የተፈጠረ ክስ እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ተብራርቷል።

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ተጠብቆ ላልመጣው ውጤት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሊምፒክ ኮሚቴ መካከል በነበረው አለመግባባት ምክንያት አይደለም ሲሉ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ውጤቱን ዝቅ ያደረገው ኮቪድ-19 እንደሆነም ጠቁመዋል።

በኦሊምፒኩ የአትሌቲክስ ቡድን መሪ ከተወዳዳሪዎቹ በቅርበት መሆን ቢገባውም፣ አብሮ ባለመሆኑና የሁለቱ ተቋማት አለመግባባት ለውጤቱ አለመሳካት ምክንያት እንደሆነ በተሳታፊ አትሌቶች ጭምር መነሳቱ ይታወሳል።

በመግለጫው የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደነበረና ሒደቱ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ መኖሩ ለውጤቱ መውረድ እንደ ምክንያትነት ተጠቅሷል።

ከዚህም ባሻገር በመግለጫው ወቅት በሪፖርቱ በቀረበው ማብራሪያ መሠረት ግሎባል ማርኬት ሌላኛው ችግር እንደነበር ተነስቷል። ይሄም ወደ ሥፍራው ያመሩ የስፖርቱ ባለሙያዎች በኩል የኦሊምፒክ ተሳትፎን አጋጣሚ በመጠቀም፣ ለግል ፍላጎታቸው ሊጠቀሙበት እንደፈለጉ ተብራርቷል።

በጋዜጣዊ መግለጫው እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ማብራሪያዎች የቀረቡ ሲሆን፣ ሁለቱ ስፖርቱን የሚመሩ አካላት ራሳቸውን መፈተሽ እንደሚገባቸው የሚጠቁም የኦሊምፒክ ጨዋታ መሆኑ ሊሰመርበት የሚገባ ዓብይ ጉዳይ መሆኑም ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...