Wednesday, April 17, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በመጪው ዓመት ከዳያስፖራ ሐዋላ አራት ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በአዲሱ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ፍሰቱን የሚያሳድጉ ዕርምጃዎችን በመውሰድ፣ ከዳያስፖራው ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ የሚላከውን ገንዘብ አራት ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው በ2013 ዓ.ም. የነበረውን አፈጻጸም አስመልክቶ ማክሰኞ ነሐሴ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመላው ዓለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አራት ቢሊዮን ዶላር በሕጋዊ መንገድ ለማስገባት ቢያቅድም፣ 3.6 ቢሊዮን ዶላር በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት መላኩን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት አስታውቀዋል፡፡

በ2012 ዓ.ም. በጀት ዓመት በአጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ ከገባው 8.8 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ፣ 3.7 ቢሊዮን ዶላር ከዳያስፖራዎች የተላከ መሆኑን ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በ2013 ዓ.ም. ከውጭ አገር በሐዋላ መልክ የተላከ ገንዘብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይታወቃል፡፡

  በኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ታሪክ ከፍተኛ የተባለው የውጭ ምንዛሪ የተገኘበት የ2013 በጀት በዓመት በአጠቃላይ ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች 3.6 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የኤጀንሲው ዳይሬክተር በመግለጫቸው በበጀት ዓመቱ 3.9 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 84 የዳያስፖራ ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ገብተው፣ ለ13,000 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም 7,000 ያህል የዳያስፖራ አባላት የውጭ ምንዛሪ አካውንት በመክፈት 7.5 ሚሊዮን ዶላር ተቀማጭ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡ በአገር ቤት እየተከናወኑ ላሉ አጠቃላይ አገራዊ ፕሮጀክቶችና ወቅታዊ አገራዊ ጥሪዎቹ ከ1.35 ቢሊዮን ዶላር በላይ ብር መሰብሰቡንም አስታውቀዋል፡፡

በአስቸጋሪ ሁኔታ በሳዑዲ ዓረቢያና በሌሎች አካባቢዎች ሕይወታቸውን በአስቸጋሪ ሲመሩ የቆዩ 64,716 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውንም ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች