Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ የቆጣቢዎችን ገንዘብ እንቅስቃሴና ዝውውር መቆጣጠሪያ ረቂቅ መመርያ አዘጋጀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ሁሉም ባንኮች የቁጠባ ደንበኞቻቸውን የባንክ ደብተር አከፋፈት፣ አጠቃላይ የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውንና የገንዘብ ዝውውር በተመለከተ ቁጥጥር የሚያደርጉበትና አንድ ወጥ የሆነ አሠራር እንዲተገብሩ የሚያስችል አዲስ ረቂቅ መመርያ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተዘጋጀው ረቂቅ መመርያ፣ ባንኮች ከዚህ በኋላ ሒሳብ የሚከፍቱ ደንበኞቻቸውን ሙሉ መረጃ መያዝና ደንበኞቻቸውን በሚገባ ማወቅ እንዳለባቸው የሚያስገድድ ጭምር ነው፡፡ ባንኮች የደንበኞች የሒሳብ እንቅስቃሴዎችን መከታተልና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥማቸው ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ረቂቅ መመርያው ያስገድዳል፡፡

አጠራጣሪና ለሕገወጥ ተግባር የገንዘብ ማስተላለፍ ድርጊት የመለየትና የመቆጣጠር ሥራ፣ በዚህ መመርያ መሠረት ኃላፊነቱን ለባንኮች መስጠቱን ብሔራዊ ባንክ አመልክቷል፡፡

ባንኮችም ሥራቸውን በኃላፊነት ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው የሚጠቅሰው ይኸው ረቂቅ መመርያ፣ በመመርያው መሠረት የተቀመጠ ገንዘብ ማውጣትና ማስተላለፍ ገደብ አለመጣሱን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ይላል፡፡

ረቂቅ መመርያውን ለማስፈጸም ባንኮች ራሱን የቻለ ዲፓርትመንትና ኦፊሰር መመደብ እንዳለባቸው ጭምር ተደንግጓል፡፡ ይህ ረቂቅ መመርያ አንድ ደንበኛ በሒሳብ እንቅስቃሴው በሕገወጥ ዝውውር ስለመሳተፉ የሚያመለክት፣ የሚያጠራጥር በቂ ወይም አሳማኝ ሁኔታ ሲገኝ ባንኮች ለፋይናንስ ደኅንነት ማዕከልና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

በዚህ ረቂቅ መመርያ መሠረት ደንበኞች ሊፈርሙ የሚገባቸው አዲስ የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡ ባንኮች ደንበኞቻቸውን ሒሳብ ሲያስከፍቱ በዚህ ስምምነት ውስጥ የተካተቱትን ድንጋጌዎች ሲያሳውቅ፣ ደንበኞችም ለስምምነቱ ተፈጻሚነት ስምምነታቸውን ሲያኖሩ ሒሳብ እንደሚከፍቱ ያመለክታል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው የሒሳብ ደብተር አከፋፈት ባንኮች የተዘበራረቀ አሠራር ስለነበራቸው፣ ይህንን አንድ ወጥ ለማድረግ ታስቦ የወጣው ይህ መመርያ ዋናው ዓላማ ግን ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታትና ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለመከላከል ታስቦ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡

ረቂቅ መመርያውን በተመለከተ የተጠናቀረውን ዝርዝር ሪፖርት በገጽ 14 ይመልከቱ፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች