Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአሸባሪነት ከተፈረጀው ሕወሓት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች መያዛቸው ተገለጸ

በአሸባሪነት ከተፈረጀው ሕወሓት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች መያዛቸው ተገለጸ

ቀን:

በ1,616 የንግድ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን ፖሊስ አስታውቋል

መንግሥት አሸባሪ ብሎ ከፈረጀው ሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ እንደገለጹት፣ ከሕወሓት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሰዎችን በማደን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ እየተደረጉ ናቸው፡፡

እስካሁን ድረስ በተካሄደው የተቀናጀ ምርመራ ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች፣ በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል። 

ከተጠረጠሩት ሰዎች በተጨማሪ ለሕወሓት ቡድን ሕገወጥ ተልዕኮ መጠቀሚያ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ምርምራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ለሕወሓት ቡድን መጠቀሚያ የነበሩ ሆቴሎች፣ ሕንፃዎች፣ መጋዘኖች፣ የኢንቨስትመንት እርሻዎች፣ ፋብሪካዎችና ሪል ስቴቶችን ጨምሮ 1,616 ያህል የንግድ ድርጅቶች እንዲዘጉ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ፖሊስ ባከናወነው ሥራ 58 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ በቁጥጥር ሥር መዋሉንበተጨማሪም 93 የባንክ ሒሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ በማሳገድ የባንክ ሒሳቦቹ ምን ያህል ገንዘብ እንደያዙ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በቀጣይም ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ያላቸውንና ተልዕኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለማደን የተቀናጀ የምርመራ ሥራና ክትትል የሚደረግ መሆኑን የገለጹት ኃላፊውለዚህም ተግባር አገር አቀፍ የሆነ የፖሊስ ምርመራ የጋራ ግብረ ኃይል እንዲቋቋም መደረጉን ተናግረዋል።

ግብረ ኃይሉ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የሚመራ እንደሆነ፣ ሁሉንም ክልሎች ከሌሎች አጎራባች ክልሎች ከሚገኙ የወንጀል ምርመራ ዘርፎች ጋር በአንድ ያጣመረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ግብረ ኃይሉ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚመራና በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሕወሓት ያሰማራቸውን ሽብርተኞች በመያዝ ለሕግ ከማቅረብ ባሻገር፣ በተደራጁ ወንጀሎችና በሌሎች የሕግ ጥሰቶች ላይ የሚሳተፉ አካላትን በመቆጣጠር የሕግ የበላይነት የሰፈነባትን አገር ለማስቀጠል ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...